03
Jun
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተራዘመው የብድር አቅርቦት ፕሮግራም አምስተኛ ግምገማ ላይ በባለሙያዎች ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል። ይህ ስምምነት በሚቀጥሉት ሳምንታት በድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሙሉ በሙሉ ሲጸድቅ፣ ኢትዮጵያ የ468 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍ እንድታገኝ ያደርጋታል። ይህም ሀገሪቱ በ4 ዓመታት ውስጥ ከምታገኘው የ3.4 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ ድጋፍ ውስጥ እስካሁን የተለቀቀላትን የገንዘብ መጠን ወደ 2.65 ቢሊዮን ዶላር ከፍ የሚያደርገው ሲሆን፣ ስምምነቱ ሊደረስ የተቻለው ከአልቫሮ ፒሪስ የተመራው የድርጅቱ ልዑክ ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ባደረገው የሁለት ሳምንታት ጉብኝትና ተከታታይ የሥራ ውይይቶች ማጠናቀቂያ ላይ ነው። በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት መግለጫ ላይ እንደተመለከተው…