11
Sep
ራስ ገዟ ሶማሊላንድ በሀርጌሳ ያለው የግብጽ ባህላዊ ቤተ መጽሃፍት በቋሚነት እንዲዘጋ መወሰኗን ገልጻለች፡፡ የሶማሊላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤክስ አካውንቱ ለይ እንዳስታወቀው በሀርጌሳ ያለው የግብጽ ቤተ መጽሃፍት እንዲዘጋ የተወሰነ ሲሆን የቤተ መጽሀፍት ቤቱ ሰራተኞችም በ72 ሰዓት ውስጥ ሀርጌሳን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል፡፡ እንደ ሚኒስቴሩ መግለጫ ሶማሊላንድ ይህንን እርምጃ የወሰደችው ከደህንነት ጋር በተያያዘ ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኢሳ ክዛ ሞሀሙድ ተቀማጭነታቸው በሀርጌሳ ላደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ስለ ሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ የወደብ ስምምነት ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል ተብሏል፡፡ ሚኒስትሩ ለዲፕሎማቶቹ ከኢትዮጵያ ጋር ያደረጉት የወደብ መግባቢያ ስምምነት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱን እና በቅርቡ የትግበራ ስምምነት እንደደረግ መናገራቸው ተገልጿል፡፡ ሚኒስትሩ አክለውም “የግብጽ ጦር በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ መግባቱ…