15
Jan
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ቀሪ ስራዎች ለማጠናቀቅ 80 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው ተገልጿል፡፡ ከ14 ዓመት በፊት ለግንባታው መሰረት ድንጋይ ሲጣል 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል ተብሎ የተጀመረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ፤ ግንባታው 97.6 በመቶ እንደደረሰና ጥቂት የማጠናቀቂያ ስራዎች ብቻ እንደቀሩት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ የፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ተናግሯል፡፡ ህዝቡ እስካሁን ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ለግእቡ ግንባታ በበጎ ፈቃደኝነት ያዋጣ ሲሆን በዚህ ዓመት 1.6 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የዚህ አካል የሆነና ባንኮችን፣ ኢንሹራንስ ተቋማትንና የብድርና ቁጠባ ተቋማትን ያሳተፈ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ባሳለፍነው ዓርብ አካሂዷል፡፡ በመርሃ ግብሩ 110 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ የታሰበ ቢሆንም በወቅቱ ከተቋማቱ መሰብሰብ የተቻለው 25.9 ሚሊዮን ብር ብቻ…