ስፖርት

አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የሮጠበት ማልያ በ2400 ዶላር ተሸጠ

አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የሮጠበት ማልያ በ2400 ዶላር ተሸጠ

በበርካታ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ስኬታማ አትሌት የሆነው ሀይሌ ገብረስላሴ የሮጠበት አንድ ማልያ በ2 ሺህ 400 ዶላር ተሸጧል፡፡ በአዲስ አበባ በተካሄደ በዚህ ጨረታ ላይ የቀረበው ይህ ማልያ አትሌት ሀይሌ በ1992 በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ከተማ በተካሄደው የ10 ሺህ ሜትር ውድድርን ያሸነፈበት ማልያ ነበር፡፡ ይህ ውድድር ለአትሌት ሀይሌ ገብረ ስላሴ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የጀመረበት ወቅት እንደነበርም ተገልጿል፡፡ የታላቁ ሩጫ መስራች እና ባለቤት አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ለጨረታ ቀርቦ 2 ሺሕ 400 ዶላር የተሸጠው ማልያ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለማጠናከር ይውላልም ተብሏል፡፡ በጨረታው የታላቁ ሩጫ ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ፕሮግራም ላይ የኃይሌ ገ/ሥላሴ የሮጠበት ማልያ፤ በእንግሊዛዊ ተጋባዥ እንግዳ አሸንፏል። ይህንን የማልያ ጨረታ እንግሊዛዊ ዜግነት ያለው…
Read More
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ታገዱ፡፡

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ታገዱ፡፡

የአለም አትሌቲክስ እና ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የአበረታች ቅመምች ህግ ጥሰት በፈፀሙ አትሌቶች ላይ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉ ተገልጿል። የቅጣት ውሳኔው ከተላለፈባቸው አትሌቶች መካከል አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ ፣ አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን እና አትሌት ህብስት ጥላሁን አስረስ ሲሆኑ የአበረታች ቅመሞች ህግ ጥሰት መፈጸማቸው ተረጋግጧል ተብሏል። ጥሰቱን ተከትሎም አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ የካቲት 2015 ዓ.ም በተካሄደው ምርመራ ኢፒኦ የተባለውን የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሙ ተረጋግጧል፡፡ በዚህም መሰረት አትሌት ሳሙኤል አባተ ለ2 ዓመታት ማለትም እስከ ሚያዝያ 2018 ዓ.ም ድረስ በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳይሳተፍ ቅጣት ተጥሎበታል፡፡ አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን በተደረገላት የአትሌት ባይሎጂካል ፖስፖርት (ABP) ምርመራ አበረታች ቅመም መጠቀሟ የተረጋገጠባት ሌላኛዋ ኢትዮጵያ አትሌት ስትሆን…
Read More
ኢትዮጵያ የ2029 አፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢትዮጵያ የ2029 አፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት አቅም እንዳላት ገለጸች

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ኢትዮጵያ የ2029 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅ በይፋ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ በ2029 የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ የማዘጋጀት አቅም አላት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ጠይቀዋል፡፡ የፊፋ፣ ካፍ እና ሌሎች የእግር ኳስ አመራሮች በአዲስ አበባ በተካሄደው የካፍ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ለዚህ ጉባኤ ተሳታፊዎች ላይ በተዘጋጀ እራት ግብዣ ላይ ንግግር ደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵያ የ2029 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅ በይፋ ጠይቀዋል። የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሙትሴፔ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል  ምስጋና አቅርበው፣ የኢትዮጵያውያን ባህል፣እሴትና እንግዳ ተቀባይነት ኢትዮጵያ  ቤታችን እንደሆነች እንዲሰማን አድርጎናል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የ2029ኙን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ካፍ ከኮሚቴው…
Read More
የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ለማድረግ ወሰነ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ለማድረግ ወሰነ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰኑ ይፋ ተደርጓል። ጉባዔው ዲሞክራቲክ ኮንጎ ላይ ለማድረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ በተከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ መቀየሩን የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ጉባኤው አዲስ አበባ ላይ እንዲካሄድ ጥያቄ አቅርቦ በካፍ ተቀባይነት ማግኘቱን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል። በዚህም መሰረት የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በቀጣይ ጥቅምት ወር በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል። ካፍ ዛሬ በሰጠው የቅድመ ጠቅላላ ጉባኤ ጋዜጣዊ መግለጫ የ2024 ቻን አፍሪካ ዋንጫ በሚቀጥለው የካቲት ወር በናይሮቢ ፣ ካምፓላ እና ዳሬ ሰላም እንደሚካሄድ አሳውቋል። የ2024 ቻን አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በጥቅምት እና…
Read More
የቀድሞ አትሌቶች በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ላይ ክስ አቀረቡ

የቀድሞ አትሌቶች በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ላይ ክስ አቀረቡ

የኢትዮጵያ ቦክስ እና ቴኒስ ፌዴሬሽን እንዲሁም ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ እና አትሌት ገዛኸኝ አበራ በጋራ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ላይ ክስ መስርተዋል። ክስ ከተመሰረተባቸው አመራሮች መካከል የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ፣ የኮሚቴው ዐቃቤ ነዋይዋ ዶ/ር ኤደን አሸናፊ ፣ ዋና ፀሐፊው አቶ ዳዊት አስፋው እና ምክትል ፀሐፊው አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ዋነኞቹ ናቸው። ክሱን ተከትሎም የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሁሉም የባንክ አካውንቶች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳይንቀሳቀሱ ታግደዋልም ተብሏል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ክስ እንደቀረበባቸውም ይፋ ተደርጓል። በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና በዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ላይ ከተመሰረቱ ክሶች መካከል :- ባልተገባ መልኩ የሰው…
Read More
ኢትዮጵያ በዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ውድድር አራት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

ኢትዮጵያ በዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ውድድር አራት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በደቡብ አሜሪካዋ ፔሩ ሊማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ውድድር ትናንት ጠናቋል፡፡ በዚህ የአትሌቲክ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች፡፡ ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፈው ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን በ6 ወርቅ፣ 2 ብር እና 2 ነሐስ በአጠቃላይ 10 ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ ችሏል። በዚህ ኢትዮጵያ ከዓለም አሜሪካን በመከተል 2ኛ እንዲሁም ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ያጠናቀቀች ሲሆን፤ ውድድሩን 1ኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቀች አሜሪካ በ8 ወርቅ፣ 4 ብር እና 4 ነሃስ በድምሩ 16 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶች በአትሌት መዲና ኢሳ በ5000 ሜትር፣ በአትሌት ሲምቦ አለማየሁ በ3000 ሜትር መሰናክል በአትሌት ጀነራል ብርሃኑ በ800 ሜትር፣ በአትሌት…
Read More
መዲና ኢሳ በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አሸነፈች

መዲና ኢሳ በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አሸነፈች

የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ውድድር ትናንት በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ፔሩ ተጀምሯል፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ላይ እየተሳተፉ ካሉ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ አትሌቶችን ከቀናት በፊት ወደ ሊማ ልካለች፡፡ እስካሁን በሁለቱም ጾታዎች የ5 ሸህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር የተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያዊያን በሁለቱም ጾታ ሜዳሊያ ውስጥ ገብተዋል፡፡ በ5000 ሜትር የሴቶች የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው አሸንፈዋል፡፡ አትሌት መዲና ኢሳ ውድድሩን በ14 ደቂቃ 39 ሰከንድ 71 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። አትሌቷ ውድድሯን ያጠናቀቀችው በገንዘቤ ዲባባ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ28 ሰከንዶች በማሻሻል ነው። ከሁለት ሳምንት በፊት በተጠናቀቀው የፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ ሰባተኛ ደረጃን ይዛ…
Read More
ኢትዮጵያን በፔሩ ከ20 ዓመት በታች ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ የሚወክለው አትሌት በጥይት ተመታ

ኢትዮጵያን በፔሩ ከ20 ዓመት በታች ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ የሚወክለው አትሌት በጥይት ተመታ

የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ውድድር ከአንድ ሳምንት በኋላ በላቲን አሜሪካዋ ፔሩ አዘጋጅነት ይካሄዳል፡፡ ለሶስት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ተመርጠው የመጨረሻ ልምምድ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለውድድሩ ከመረጣቸው አትሌቶች መካከል የ17 አመቱ አትሌት ሰው መሆን ታሪኩ አንዱ ነው፡፡ ይህ አትሌት ባሳለፍነው እሁድ ነሀሴ 5 ቀን 2016 ዓም የከሰዓት በኋላ ልምምድ ለመስራት ወደ ጫካ ወጣ ብሎ ልምምዱን ጨርሶ እያቀዘቀዘ ባለበት ያልታሰበ ሰው ጥቃት አድርሶበታል ተብሏል፡፡ አትሌቱን አንድ ሰው ከቀረበው በኋላ ፓሊስ ነኝ በማለት ራሱን ካስተዋወቀው በኋላ እዚህ አካባቢ ቁማር የሚጫወቱ ታውቃለህ በማለት ሲጠይቀው አላውቅም ብሎ እንደመለሰ ነገር ግን ወዲያው በፎጥነት ይህ ሰው አንገቱን ሲይዘው አትሌቱም…
Read More
የማራቶን አትሌቶች አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ኢትዮጵያ የሸለመቻቸውን 2 ሚሊዮን ብር አልቀበልም አሉ

የማራቶን አትሌቶች አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ኢትዮጵያ የሸለመቻቸውን 2 ሚሊዮን ብር አልቀበልም አሉ

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ልዑክ ቡድን በብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል እና የእራት ግብዣ ተደርጎለታል። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በተካሄደው የአቀባበል እና የአውቅና ስነ ስርዓት ላይም ለአትሌቶች፣ አሰልጣኞች እና ለታሳታፊዎችዎች እንደየ ተሳትፏቸው እና አብርክቷቸው ከ50 ሺህ ብር እስከ 7 ሚሊየን ብር የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቷል። በዚህ ስነ ስርዓት ላይ በማራቶን ለኢትዮጵያ ብቸኛውን ወርቅ ሜዳሊያ ላስገኘው አትሌት ታምራት ቶላ 7 ሚሊየን ብር እና ወርቅ ኒሻን ሽልማት ተበርክቶለታል። የብር ሜዳልያ ላመጡት አትሌት ትግስት አሰፋ፣ አትሌት በሪሁን አረጋዊ እና አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለእያንዳንዳቸው የ 4 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የታምራት ቶላ እና ትግስት አሰፋ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ በስነ ስርዓቶ ላይ የ2 ሚልዮን ብር…
Read More
በፓሪስ ኦሎምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ 

በፓሪስ ኦሎምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ 

ለ17 ቀናት በፓሪስ የተካሄደው 33ኛው ኦሎምፒክ ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል። በፓሪስ ኦሎምፒክ ድል ያስመዘገቡ እና የተሳተፉ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ዛሬ ማለዳ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ገብተዋል። የልኡካን ቡድኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በዛሬው እለት ከሰዓት በኋላ በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ለልዑካን ቡድኑ የክብር ሽልማት፣ የማበረታቻ እና የእራት ግብዣ መርኃ-ግብር የሚካሄድ መሆኑንም ተገልጿል። ኢትዮጵያ በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ 1 የወርቅ እና 3 የብር በአጠቃላይ 4 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከዓለም 47ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 4ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወቃል። ታምራት ቶላ በማራቶን ወርቅ፣ ጽጌ ድጉማ በሴቶች 800 ሜትር ብር፣ በሪሁ አረጋዊ በወንዶች 10 ሺህ…
Read More