የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቹ ከነዓን ማርክነህ የኦማን ክለብን ተቀላቀለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወይም (ዋልያዎቹ) የፊት መስመር እና የመሐል ሜዳ ተጫዋች ከንአን ማርክነህ ወደ አዲስ ክለብ ለማምራት መስማማቱ ተገልጿ።

ከንአን ማርከነ በአዲሱ የውድድር ዘመን ወደ ኦማን ሊግ በማቅናት አል ሸባብ ክለብ ለመጫወት ከስምምነት መድረሱ ታውቋል።

ከብሔራዊ ቡድን ጨዋታ መልስ ወደ ኦማን ያቀናው ከንአን ማርክነህ በትላንትናው ዕለት የህክምና ምርመራውን በተሳካ ሁኔታ አልፏል።

ከንአን ከህክምና ምርመራ በኃላ በክለቡ የሚያቆየውን የአንድ አመት ኮንትራት ሲፈራረም ክለቡ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጎታል።

ከንአን ያለፈውን የውድድር ዓመት በሊቢያ ሊግ ስኬታማ ጊዜን ሲያሳልፍ ለአል መዲና እና ሸባብ አል ጋሂር እግር ኳስ ክለቦች መጫወቱ ይታወሳል።

ከንአን ማርከነ በሊቢያ ቆይታው በ14 ጨዋታዎች ስድስት ጎሎችን አስቆጥሯል።

የከንአን አዲሱ ክለብ አል ሸባብ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የሱፐር ካፕ ዋንጫ ማሸነፍ ችሎ ነበር።

ከንአን ለአዲሱ ክለቡ በሳምንቱ መጨረሻ በሚኖረው የሊጉ ሶስተኛ መርሐ ግብር ላይ ተሰልፎ እንደሚጫወት ይጠበቃል።

የከንአን ማርክነ አዲሱ ክለብ አል ሸባብ በ እስያ ቻሌንጅ ካፕ ላይ ተሳታፊ መሆኑ ታውቋል።

በተያያዘ የስፖርት ዜና አዲስ አበባ ስታዲየም ከአምስት ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል።

የባህልና ስፖርት ሚንስቴር እንደገለጸው የኢትጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ በሚመለሱበት ጉዳይ ላይ ከክለብ ሀላፊዎች ተወካዮች እና ከደጋፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከተደረጉበት አምስት አመት አልፈዋል፡፡

ስታዲየሙ እድሳት ላይ መሆኑ እና ሌሎች ምክንያቶች እግር ኳስ ከከተማው እንዲርቅ ቢያደርግም ዋናው ምከንያት ግን የስፖርታዊ ጨዋነት  መሆኑ ዛሬ በነበረው የውይይት መድረክ ላይ ተነስቷል፡፡

በተለይ ደግሞ የፖለቲካ ፍላጎትን ወደ ስፖርት ሜዳ ለማምጣት መሞከር እግር ኳሱን በብዙ እንደጎዳው ተገልጿል፡፡

አዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታዎችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚንስትር ሸዊት ሻንካ ተናግረዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *