ባለፋት ዘጠኝ ወራት በህገ ወጥ መንገድ የፓስፓርት አግልግሎት ለማግኘት የሞከሩ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዉለዋል ተብሏል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2018 በጀት አመት ዘጠኝ ወራት ያከናወናቸውን አገልግሎት አፈፃፀም በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እንደተናገሩት ባለፋት ዘጠኝ ወራት 3 ሺህ 6 መቶ 38 ግለሰቦች በህገ ወጥ መንገድ የፓስፓርት አግልግሎት ለማግኘት የተጭበረበረ ሰነድ ይዘው ሲንቀሳቀሱ ነበር።
ከፓስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ 300 የውጭ ዜጎች እና 3ሺህ3 መቶ 38 ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ መንገድ አገልግሎት ለማግኘት የተጭበረበረ ሰነድ ይዞው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እና ትክክለኛ ያልሆነ የዜግነት ማስረጃ ይዘዉ የተገኙ መሆናቸው ተጠቁሟል።
በዚህም መሰረት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጋቸውን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሯ በህግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጭምር ተደረጓል።
እንደዚሁም ህገ ወጥ እንቅስቃሴን ከመቆጣጠር አኳያ ባለፉት 9 ወራት የድንበር ቁጥጥር ስራ መከናወኑን ዋና ዳይሬክተሯ በመግለጫው ላይ ተናግረዋል ።
ከዚህ ውስጥም 4 ሺህ 576 ያህሉ የውጪ ዜጎች መሆናቸውን ተናግረው 5 ሺህ 954ቱ ደግሞ ኢትዮጲያውያን እንደሆኑ አስረድተዋል።
በድምሩ 10 ሺህ 530 የሚሆኑ ሰዎች በህገ ወጥ መንገድ ሊወጡና ሊገቡ ሲሉ ተይዘዉ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
የውጭ ዜጎች ምዝገባና ቁጥጥርን አስመልክቶ 42 ሺህ 809 የውጭ ዜጎች በሀገር ውስጥ በተለያዩ ኩባንያዎች እየሰሩ ያሉትን ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገቡ የማድረግ ስራ ተሰርቷል።