EthioNegari

መንግስት በቀጣዩ ዓመት 1 ነጥብ 8 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ

መንግስት በቀጣዩ ዓመት 1 ነጥብ 8 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ

የፌደራል መንግሥት በአዲሱ 2019 በጀት ዓመት አንድ ነጥብ 817 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የ2019 በጀት ዓመት የበጀት መግለጫ ማብራሪያ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ በ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት በጥቅሉ አንድ ነጥብ 8 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡ ይህ የገቢ ዕቅድ በ2018 በጀት ዓመት ይሰበሰባል ተብሎ ከተገመተው ጠቅላላ ገቢ አንጻር የ17 ነጥብ 4 በመቶ ዕድገት ያለው ሆኗል። እቅዱ ከዓመታዊ በጀት  ውስጥ የ89  በመቶውን ከታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ለመሰብሰብ መታቀዱንም ሚንስትሩ አቶ አህመድ ጠቁመዋል። የታክስ ገቢ ዕቅዱን ለማሳካትም በታክስ ፖሊሲና በታክስ አስተዳደር ረገድ የተያዙ ማሻሻያዎችን፣ የታክስ ዲጂታላይዜሽንና የኤክሳይዝ ስታምፕ…
Read More
በኢትዮጵያ የሚኖሩ የስሪላንካ ዜጎችን ያገቱ ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኢትዮጵያ የሚኖሩ የስሪላንካ ዜጎችን ያገቱ ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኢትዮጵያ የስሪላንካ ኤምባሲ ተወካይ ግንቦት 23/2026 ለስራ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሦስት ዜጎቹ እንደተሰወሩ እና ሲሪላንካ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ተደውሎ እያንዳንዳቸው 30 ሺ ዶላር እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን ግንቦት 26 ቀን 2026  በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ሪፖርት አደረጉ። በአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትልና የምርመራ ቡድን በማዋቀር ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደገለጸው ከሌሎች የፀጥታ ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ባሰባሰበው መረጃ ሦስቱ ግለሰቦች በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C- 40463/AA በሆነች ሱዚኪ ዲዛየር  መኪና ከኤርፖርት ተሳፍረው መሄዳቸውን አረጋግጧል። የክትትል ቡድኑ አባላት አሽከርካሪውን  ጨምሮ 2 ኢትዮጵያውያንን እና 4 የፓኪስታን…
Read More
ስምረት ፓርቲ በትግራይ “አዲስ ሕዝባዊ የፖለቲካ ትግል” እንዲጀመር አሳሰበ

ስምረት ፓርቲ በትግራይ “አዲስ ሕዝባዊ የፖለቲካ ትግል” እንዲጀመር አሳሰበ

የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ስምረት (ስምረት)፣ በትግራይ ፖለቲካ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ህወሀት በሀይል ስልጣን መቆጣጠሩን አስታውቋል። በትግራይ ክልል ስልጣን በሀይል የተቆጣጠረው ሀይል ክልሉን ወደ ከፋ የጦርነት ድባብና “ሰው አልባ” መዋቅር እየመራው መሆኑንም አስታውቋል። ፓርቲው የድርጅቱ ምክር ቤት ከግንቦት 29 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ያካሄደውን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ማጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ በትግራይ ክልል እየተባባሰ መጥቷል ያለው “የኋላ ቀር ቡድን” ውሳኔ የህልውና አደጋ እየደገነ መሆኑን አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ ውስጥ የወጣቶች እፈሳ፣ ከፍተኛ የስደት ፍሰት፣ የምሁራን መበተን እና ከባድ የኑሮ ውድነት መንገሱን ድርጅቱ በዝርዝር አስረድቷል።የስምረት ምክር ቤት በመግለጫው፣ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ሥልጣን ላይ ያለው “ኋላ ቀር ቡድን የኤርትራን መንግሥት የወታደራዊ…
Read More
ከ10 ዓመት በፊት ለተፈጸመ ታክስ ማጭበርበር ቅጣት እንዲጣል የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ተዘጋጀ

ከ10 ዓመት በፊት ለተፈጸመ ታክስ ማጭበርበር ቅጣት እንዲጣል የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ተዘጋጀ

ማንኛውም ደረሰኝ ሳይቆርጥ የተገበያየ አካል በወንጀል እስከመጠየቅ የሚያደርሰው የተሻሻለው የታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ረቂቁ የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ለ10 ዓመታት ወደኋላ በመሄድ ሂሳቡን በመመርመር ወይም ሂሳብ ኦዲት በማድረግ ተጨማሪ ግብር ማስከፈልን ለገቢ ሰብሳቢው የሚፈቅድ ነው፡፡ ዛሬ ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ የግብር አስተዳደር አዋጅ በተለይ ደረሰኝ ባለመቁረጥ የሚደረግ ግብይት ላይ ከፍ ያለ ቅጣትን የሚያስከትሉ አንቀፆችን የያዘ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ህጋዊ ደረሰኝ ያልሰጠ እንደሆነ በእያንዳንዱ ባልሰጠው ደረሰኝ ልክ 100 ሺህ ብር አስተዳደራዊ ቅጣት በገንዘብ ይቀጣል ይላል የማሻሽያ አዋጁ ማብራሪያ፡፡ በተጨማሪ ይሄንኑ አስተዳደራዊ ቅጣት በዓመት ሁለት ጊዜ የተቀጣ እንደሆነ እና ሆን ብሎ ድርጊቱን መፈፀሙን ከቀጠለ ድርጊቱ እንደ ወንጀል ጥፋት…
Read More
ኢትዮጵያና አይ ኤም ኤፍ የ468 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ላይ ደረሱ

ኢትዮጵያና አይ ኤም ኤፍ የ468 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ላይ ደረሱ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተራዘመው የብድር አቅርቦት ፕሮግራም አምስተኛ ግምገማ ላይ በባለሙያዎች ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል። ይህ ስምምነት በሚቀጥሉት ሳምንታት በድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሙሉ በሙሉ ሲጸድቅ፣ ኢትዮጵያ የ468 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍ እንድታገኝ ያደርጋታል። ይህም ሀገሪቱ በ4 ዓመታት ውስጥ ከምታገኘው የ3.4 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ ድጋፍ ውስጥ እስካሁን የተለቀቀላትን የገንዘብ መጠን ወደ 2.65 ቢሊዮን ዶላር ከፍ የሚያደርገው ሲሆን፣ ስምምነቱ ሊደረስ የተቻለው ከአልቫሮ ፒሪስ የተመራው የድርጅቱ ልዑክ ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ባደረገው የሁለት ሳምንታት ጉብኝትና ተከታታይ የሥራ ውይይቶች ማጠናቀቂያ ላይ ነው። በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት መግለጫ ላይ እንደተመለከተው…
Read More
በ947 ምርጫ ጣቢያዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት በፊት ድምጽ መሰጠት መጀመሩ ተገለጸ

በ947 ምርጫ ጣቢያዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት በፊት ድምጽ መሰጠት መጀመሩ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኅብረት እንደገለጸው ምልከታ ካደረገባቸው 2 ሺህ 258 ምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ በ947 ወይም 42 በመቶዎቹ ላይ ከንጋቱ 12 ሰዓት በፊት ድምጽ መሰጠት መጀመሩን ማረጋገጡን ገልጿል፡፡ ድርጅቱ ዛሬ ግንቦት 24፣ 2018 በመካሄድ ላይ ባለው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫን አስመልክቶ ምልከታ ባደረገባቸው የምርጫ ጣቢያዎች የተስተዋሉ ክስተቶችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የኅብረቱ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳህለሥላሴ አበበ በመግለጫው ላይ እንዳሉት ከትግራይ ክልል ውጪ በቀሪዎቹ ሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተካሄደ ባለው ምርጫ የግማሽ ቀን ምልከታ ሪፖርት ይፋ አድርገዋል፡፡ በዚህም የህብረቱ ታዛቢዎች ከተገኙባቸው 2 ሺህ 258 ምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ1 ሺህ 276 ወይም 57 በመቶዎቹ ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ…
Read More
ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድንን እንዲመሩ ተመረጡ

ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድንን እንዲመሩ ተመረጡ

የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ 73 አባላትን ያቀፈ የአፍሪካ ኅብረት ግንቦት 24 ቀን 2018 በሚካሄደው የኢትዮጵያ ምርጫ 2018 ታዛቢ ልዑካን ቡድን ይመራሉ ተብሏል። በቀድሞው የኬኒያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራው፣ የአፍሪካ ኅብረት የታዛቢዎች ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ መግባቱን ኅብረቱ አስታውቋል። ታዛቢ ቡድኑ ከ37 አገራት የተውጣጡ 73 አባላትን ያቀፈ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ ከታዛቢዎቹ ውስጥ 61 በመቶዎቹ ሴቶች እንደሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኅብረት የታዛቢዎች ቡድን የሚሰማራው ለአጭር ጊዜ ታዛቢነት ሲሆን፣ ጊዜያዊ ጽ/ቤቱን በስካይላይት ሆቴል እንደሚያደርግ አሳውቋል። ታዛቢዎቹ በሁሉም ምርጫ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች እንደሚሰማሩም ተገልጿል። ሰባተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅቴን ጨርሻለሁ ያለው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአማራ ክልል በ8 የምርጫ ክልሎች ሊካሄድ የታሰበው ምርጫ መራዘሙን አስታውቋል። ቦርዱ…
Read More
ብሔራዊ ባንክ አስመጪዎች እና ላኪዎች ያለ ባንክ ቅድመ እውቅና እቃ እንዲያዙ ፈቀደ

ብሔራዊ ባንክ አስመጪዎች እና ላኪዎች ያለ ባንክ ቅድመ እውቅና እቃ እንዲያዙ ፈቀደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ሥርዓት እያደረገ ያለውን ሽግግር ለማጠናከር፣ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደርን የሚያቀሉ አዳዲስ መመሪያዎችን ይፋ አድርጓል።ባንኩ ባወጣው መግለጫ ማሻሻያው የውጭ ምንዛሬ አስተዳደርን ይበልጥ ለማቅለልና በንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት የሆኑ የቢሮክራሲ ሰንሰለቶችን የሚያሳጥሩ ናቸው።በአዲሱ መመሪያ መሰረት የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ እና የውጭ ምንዛሬ ተመላሽ ሂሳብ  ላላቸው ደንበኞች የብድር ደብዳቤ እና የሰነድ መክፈያ ፈቃዶችን ያለ ብሔራዊ ባንክ ቅድመ ሁኔታ ማጽደቅ እንዲችሉ ሙሉ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል።ይህ ማሻሻያ በተለይ በገቢና ወጪ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ነጋዴዎች የጊዜና የቢሮክራሲ ጫናን ያቀላል ተብሎ ይጠበቃል።በተጨማሪም የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ ያላቸው ተቋማት የባንኮችን ቅድመ ፈቃድ ሳይጠብቁ በሰነድ መክፈያ ስምምነት መሠረት የሸቀጦችን የጭነት ትዕዛዝ መስጠት…
Read More
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ አነሳ

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ አነሳ

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ ጥሎት የነበረውን የቪዛ ገደብ ከሁለት ዓመት በኋላ አንስቻለሁ ብሏል፡፡ ህብረቱ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ሚያዝያ 2016 ወደ አውሮፓ በሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ  አመልካቾች ላይ ገደቦችን ጥሎ እንደነበር ገልጾ ገደቡ መነሳቱን አስታውቋል፡፡ ህብረቱ የቪዛ ገደቦቹን የጣለው በተለያዩ ጊዜያት ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት የገቡ እና የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያዊያንን የኢትዮጵያ መንግስት ለመመለስ እየተባበረ አይደለም በሚል ምክንያት ነበር፡፡ ከሁለት ወራት በፊት በአዲስ አበባ በተካሄደው የኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት የሁለትዮሽ ውይይት ላይ በአውሮፓ ሀገራት የመኖሪያ ፈቃድ ያላገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ከመመለስ አንጻር የኢትዮጵያ መንግስት ያሳየውን መሻሻል አድንቆ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ከጣላቸው የቪዛ ገደቦች መካከልም የቪዛ ማመልከቻ ጊዜ…
Read More
ደረሰኝ የማይሰጡ ነጋዴዎች የ100 ሺህ ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተባለ

ደረሰኝ የማይሰጡ ነጋዴዎች የ100 ሺህ ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተባለ

በግብይት ወቅት ማናቸውም ግብር ከፋይ ነጋዴ ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲያከናውን ወይም ዋጋ አሳንሶ የተገኘ በእያንዳንዱ ደረሰኝ የአንድ መቶ ሺህ ብር ቅጣት መጣል የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። ያለ ደረሰኝ ሲገበያይ የተገኘ ማንኛውም ግብር ከፋይ ለገዢ ባልሰጠው በእያንዳንዱ ደረሰኝ ብዛት ከዚህ ቀደም 50 ሺህ ብር ይቀጣ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ማሻሻያ በተደረገለት የታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ መሰረት ወደ አንድ መቶ ሺህ ብር ቅጣት ከፍ ብሏል።የገንዘብ ሚኒስቴር እንደ ዋና ማሻሻያዎች ካነሳቸው መካከል የታክስ የምስክር ወረቀት አሰጣጥን ማሻሻል፣ የታክስ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ በማስታረቅ ሥርዓት መፍታት፣ የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ የሚታረምበትን ሥርዓት ግልጽ ማድረግ፣ እንዲሁም የውሳኔ ማስታወቂያ ማሻሻያና የይግባኝ ማቅረቢያ የጊዜ ገደቦችን በግልጽ ማስቀመጥ የሚሉት ይገኙበታል።እነዚህ…
Read More