ከ300 በላይ የአውሮፓ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መሰማራታቸው ተገለጸ

የኢትዮጵያ- የአውሮፓ ህብረት የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ሲሆን ነገ ፍጻሜውን ያገኛል ተብሏል።

የኢትዮጵያን እና አውሮፓን ንግድ እና ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀው ይህ ጉባኤ መሪዎች፣ የንግድ አማካሪዎች፣ የኩባንያ ባለቤቶች እና ሌሎችም ተገኝተውበታል፡፡

በጉባኤው ላይ የተገኙት የአውሮፓ ህብረት የአለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽር ጆሴፍ ሲኬላ እንዳሉት 300 የሚጠጉ የአውሮፓ ሀገራት ኩባንያዎች በተለያዩ ዘርፎች በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በኢንቨስትመንት ላይ ናቸው ብለዋል።

በሌላ በኩል የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ የንግድ ቀጠናን ተግባራዊት ለማፍጠን የሚያግዝ 1.2 ቢሊዮን ዮሮ ድጋፍ ስምምነትም በፎረሙ ላይ ተፈርሟል።

ከዚህ በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት አቋርጦት የነበረውን የበጀት ድጋፍ ዳግም መጀመሩ ተገልጿል።

በዚህም ህበረቱ ለኢትዮጵያ መንግስት የበጀት ድጋፍ 140 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት መወሰኑን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የበጀት ድጋፍ መስጠቱን ያቋረጠው ከስድስት አመት በፊት እ.አ 2020 እንደነበር ተጠቅሷል።

ህብረቱ የበጀት ድጋፍ ማድረጉን ዳግሞ ያስጀመረው የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰዳቸው ያሉ ሪፎርሞች ላይ እምነት ስለሳደረ ነው ሲሉ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

የቢዝነስ ፎረሙ የአውሮፓ እና የኢትዮጵያ የንግድ ተቋማት፣ ባለሀብቶች እና ተቋማት በአንድ ላይ ያገናኘ ሲሆን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነቶችን ለማጠናከር እንደሚያግዝ ተጠቅሷል።

በዚህም የግብርና ንግድ ፣ ንፁህ ኢነርጂን፣ ጤናን እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ጨምሮ እድሎችን ፎረሙ ያጎላል ተብሎ ተገምቷል።

በአሁኑ ገዜ በኢትዮጵያ ወደ 300 የሚጠጉ የአውሮፓ ኩባንያዎች በሀገሪቱ ውስጥ መዋዕለንዋያቸውን ፈሰሱ እያደረጉ ሲሆን ይህም የአውሮፓ ህብረት እና የኢትዮጵያ የንግድ ግንኙነት ከ 2014 ዓ.ም ወዲህ በአሁኑ ጊዜ በጣም ጠንካራ ነው ሲባል ሰምተናል።

ኢትዮጵያ 30 በመቶ የወጪ ንግድ ምርቶቿን ወደ አውሮፓ የምትልክ ሲሆን ጀርመን ፣ሆላንድ እና ጣልያን ዋነኛ የንግድ አጋሮች ናቸው።

ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ሀገራት ከምትልካቸው ምርቶች ውስጥ ቡና፣ አበባ፣ የቅባት እህሎች እና ጥራጥሬዎች ዋነኞቹ ናቸው።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *