12
Feb
ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ 43.3 በመቶ ወይም 18.9 ቢሊዮን ብር እድገት አሳይቷል ብሏል። ገቢውም የእቅዱን 90.7 መሆኑን ተናግሯል። በዘንድሮ የበጀት ዓመት ስድስት ወር ውስጥ ምንም አይነት የሳይበር ጥቃት አልደረሰብኝም ነው ያለው። በዚሁ የስራ አፈፃፀም የግዜ ማዕቀፍ 6 ሚሊዮን ገደማ ደንበኞች አፍርቻለሁ ያለው ኩባንያው በአጠቃላይ የደንበኞቼ ቁጥርም 80.5 ሚሊየን ደርሰዋል ተብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌኮም አገልግሎት ብዛት ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም ደግሞ 17ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን ዓለም አቀፉ የቴሌኮም አገልግሎት ድርጅት ወይም ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ (GSMA) ጥናት ተረጋግጧል ተብሏል። የደንበኛን ቁጥር ለመጨመር ከተሰሩት ስራዎች መካከል በግማሽ አመቱ 202 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች ተጠናቀው ወደ እንደገቡም ተገልጿል። በሞባይል ኔትዎርክ በተከናወኑ የፕሮጀክት ስራዎች ተጨማሪ…