EVs

የቻይናው ጓንዡ አውቶሞቢል ግሩፕ በኢትዮጵያ መኪና ማምረት እንዲጀምር ተጠየቀ

የቻይናው ጓንዡ አውቶሞቢል ግሩፕ በኢትዮጵያ መኪና ማምረት እንዲጀምር ተጠየቀ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ኩባንያው ከሽያጭ ማዕከል መክፈት በተጨማሪ የማምረቻ እና መገጣጠሚያ ማዕከልም እንዲከፍት ጠይቀዋል። GAC JUNTU አዲስ ዘመናዊና ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሠራ የትራንስፖርት ሥርዓት በማስተዋወቅ፣ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ቀዳሚ የኤግዚቢሽን ማዕከሉን በአዲስ አበባ በይፋ መርቋል። የኩባንያው  የምርት ማሳየ 2,300 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው  ሲሆን ከማሳያነት ባለፈ  ከሽያጭ በኋላ  አገልግሎት፣  መለዋወጫ እና በአምራች የተደገፈ ዋስትና የሚሰጥበት አካቷል ተብሏል። ተቋሙ የተሽከርካሪ ሽያጭን፣ የተረጋገጠ የድኅረ-ሽያጭ አገልግሎትን፣ ኦሪጅናል የመለዋወጫ ዕቃዎችን እና ከአምራቹ የሚሰጥ ዋስትናን ያካተተ የተሟላ የ4S-ደረጃ ሥርዓት (4S-standard ecosystem) በማቅረብ በኢትዮጵያ ለታማኝነትና ለደንበኞች አገልግሎት አዲስ መለኪያ ያስቀምጣል። GAC JUNTU የኢትዮጵያን ገበያ  አራት ዘመናዊ  የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ይዞ መቅረቡን…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛውን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ አስመረቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛውን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ አስመረቀ

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ ከመገናኛ ወደ ቦሌ  በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ እጅግ ፈጣን ያለውን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ሁለተኛውን ጣቢያ በይፋ ሥራ አስጀምሬያለሁ ብሏል። ኩባንያው ከዚህ ቀደም ከቦሌ ወደ መገናኛ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ 16 መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል የኤሌክትሪክ መኪና መሙያዎችን የያዘ ጣቢያ ገንብቼ ወደ ስራ አስገብቻለሁ ማለቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም ከየካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ14 ሺህ 280 የኤሌክትሪክ መኪኖች አገልግሎት መስጠት ችሏል ተብሏል። ለዚህም 376,574.72 ኪሎዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ጥቅም ላይ ውሏል የተባለ ሲሆን በተጨማሪም 521,074.23 ኪሎግራም ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር እንዳይለቀቅ መከላከል የተቻለ ሲሆን፣ ይህም ከ2,622 በላይ ዛፎችን ከመትከል ጋር እንደሚነጻጸር ተገልጿል። በምራፍ ሁለት…
Read More
ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ባትሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ልታቋቁም መሆኗ ተገለጸ

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ባትሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ልታቋቁም መሆኗ ተገለጸ

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ለሚኒስትሩ ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል በኢትዮጵያ  የኤልክትሪክ መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የመለዋወጫ አካላት ፍላጎትን እንዴት ሊሸፈን ታስቧል? የሚለው ዋነኛው ነበር፡፡ ከኤሌክትሪክ መኪና ውስጥ የባትሪ ጉዳይ ዋናው በመሆኑ ወደ ፊት ለባትሪ የሚወጣው ውጪ ምንዛሪ ፈታኝ እንዳይሆን በሃገር ውስጥ ለማምረት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ምን እየሰራ ነው ሲሉም የምክር ቤቱ አባላት ጠይቀዋል፡፡ አቶ መላኩ በምላሻቸው የኤሌክትሪክ መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች በክልሎችም ጭምር እየጨመረ መምጣቱን መልካም ነው ምክንያቱም ሃገሪቱ በየአመቱ ለነዳጅ የምታወጣውን 4 ቢልዮን ዶላር ያስቀራል ብለዋል፡፡ የኤሌክትሪክ መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች እየበረከቱ…
Read More
ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ የሌላቸው ድርጅቶች መኪና ወደ ሀገር ውስጥ እንዳያስገቡ ከለከለች

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ የሌላቸው ድርጅቶች መኪና ወደ ሀገር ውስጥ እንዳያስገቡ ከለከለች

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት እየተደረገ  መሆኑን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወርቁ ደስታ እንዳሉት  "በሁለተኛው ምዕራፍ እየተከናወነ ባለው የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት በመኪና ማቆሚያዎች የኃይል መሙያ እየተሠራ ነው " ብለዋል።የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ዴዔታ በርኦ ሀሰን በበኩላቸው "ከዚህ በኃላ የተሽከርካሪ አስመጪና የሚገጣጥሙ ድርጅቶች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ሳይተክሉ በሥራ ላይ መሰማራት አይችሉም " ብለዋል።በኢትዮጵያ ከ400 በላይ ተቋማት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ እያስመጡና እየገጣጠሙ ነው የተባለ ሲሆን ሁሉም አስመጪዎች እና ገጣጣሚዎች የኃይል መሙያ እንዳላቸውም ተገልጿል። ኢትዮጵያ ከአንድ ሳምንት በፊት  ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሃይል መሙያ ማሽን (ቻርጀር) መትከል የሚፈቅድ መመሪያ ማዘጋጀቷ…
Read More