21
Aug
ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን እንዳያስገቡ እገዳ ጥላለች፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ዲፕሎማቲክ እና ሚሲዮኖች የነዳጅ መኪናዎችን እንዳያስገቡ እገዳ የጣለች ሲሆን በምትኩ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ማስመጣት ብቻ እንዳለባቸው አሳስቧል። የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በአዲስ አበባ ለሚገኙ የዲፕሎማቲክ እና የቆንስላ ሚስዮኖች፣ ለቀጠናው እና ለአለም አቀፍ ድርጅቶች በፃፈው ደብዳቤ " የተወሰደው እርምጃ ኢትዮጵያ የበካይ ጋዝ ልዕቀት ቅነሳና ወደ ታዳሽ ኃይል ለመሸጋገር ካላት ቁርጠኝነት የተነሳ መሆኑን" አስረድተዋል ። በዚህም የዲፕሎማሲ መብት ያላቸው ሁሉ ተሽከርካሪዎችን ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የተሰጠውን አቅጣጫ አክብረዉ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ብቻ ማስመጣት ይጠበቅባቸዋል ብሏል። ኢትዮጵያ ከመጋቢት 2016 ዓ.ም ጀምሮ በነዳጅ የሚሰሩ የግል አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ወደ…