16
Jan
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት እየተደረገ መሆኑን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወርቁ ደስታ እንዳሉት "በሁለተኛው ምዕራፍ እየተከናወነ ባለው የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት በመኪና ማቆሚያዎች የኃይል መሙያ እየተሠራ ነው " ብለዋል።የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ዴዔታ በርኦ ሀሰን በበኩላቸው "ከዚህ በኃላ የተሽከርካሪ አስመጪና የሚገጣጥሙ ድርጅቶች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ሳይተክሉ በሥራ ላይ መሰማራት አይችሉም " ብለዋል።በኢትዮጵያ ከ400 በላይ ተቋማት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ እያስመጡና እየገጣጠሙ ነው የተባለ ሲሆን ሁሉም አስመጪዎች እና ገጣጣሚዎች የኃይል መሙያ እንዳላቸውም ተገልጿል። ኢትዮጵያ ከአንድ ሳምንት በፊት ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሃይል መሙያ ማሽን (ቻርጀር) መትከል የሚፈቅድ መመሪያ ማዘጋጀቷ…