FDI

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፍሰት የሁለት ቢሊዮን ዶላር ጉድለት አሳየ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፍሰት የሁለት ቢሊዮን ዶላር ጉድለት አሳየ

ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ አቅዳ እንደነበር ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርቱ ላይ እንደገለጸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር አግኝታለች፡፡ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ እንዳሉት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 4.5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ወደ አገር ውስጥ ለመሳብ ታቅዶ 2.67 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ የኮሚሽኑ አፈጻጸም የዕቅዱን 61 በመቶ ብቻ ያሳካ ሲሆን በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት፣ በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያለው አለመረጋጋት እንዲሁም በዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ምክንያት ያጋጠመው የዓለም ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ለአፈጻጸሙ መቀነስ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል፡፡ ወደ…
Read More