Russia

ኢትዮጵያ 5000 ዘመናዊ ሩሲያ ሰራሽ ተሽከርካሪዎችን ልታስግባ ነው

ኢትዮጵያ 5000 ዘመናዊ ሩሲያ ሰራሽ ተሽከርካሪዎችን ልታስግባ ነው

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደተናገሩት፤ ተሽከርካሪዎቹ ከሀገሪቱ መልክዓ ምድር ጋር አብረው የሚሄዱ እና የዩሮ 5 የሞተር የተገጠመላቸው በመሆኑ የአየር ብክለት ተፅእኗቸው አነስተኛ ነው። በኢትዮጵያ ያሉ አብዛኛዎቹ ተሽከርካሪዎች ዩሮ 2 እና ዩሮ 3 የሞተር ብቃት ያላቸው ሲሆኑ፤ ሩሲያ ሰራሾቹ ካማዝ ተሽከርካሪዎች ግን በዚህ ረገድ አዲስ ምዕራፍን የገለጡ ናቸው ብለዋል። ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ የንግድ አጋጣሚዎችን ለመፍጠር እንዳገዛቸውም ነው የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንቱ የተናገሩት። ተሽከርካሪዎቹን ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገባው የባዝራ ሞተር ድርጅት ማናጀር ያይራድ አስናቀ በበኩላቸው፤ ተሽከርካሪዎቹ በ2025 የመጀመሪያ አጋማሽ ወር ወደ ኢትዮጵያ መግባት ይጀምራሉ ብለዋል። በቀጣይ የሕዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችንም ጭምር ለማስገባት እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሆነም…
Read More
ኢትዮጵያዊው ቅጥረኛ ወታደር ከዩክሬን ጎን ሆኖ እየተዋጋ እንደሆነ ተገለጸ

ኢትዮጵያዊው ቅጥረኛ ወታደር ከዩክሬን ጎን ሆኖ እየተዋጋ እንደሆነ ተገለጸ

ለአንድ ሳምንት በሚል የተጀመረው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ሁለት ዓመት ያለፈው ሲሆን ጦርነቱ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል። ሩሲያ ከዩክሬን ጎን ቆመው እየተዋጉ ያሉ ቅጥረኛ ወታደሮችን ማንነት ይፋ አድርጋለች። እንደ ሩሲያ መከላከያ ሚንስቴር መረጃ ከሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ከዩክሬን ጎን ሆኖ ሩሲያን እየወጋ ይገኛል ተብሏል። ይህ ኢትዮጵያዊ እስካሁን በህይወት እንዳለ የተገለጸ ሲሆን ወታደሩ ኢትዮጵያዊ ከመሆኑ ውጪ ማንነቱ ይፋ አልተደረገም። በአጠቃላይ ይህ ጦርነት ከተጀመረበት የካቲት 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከ89 ሀገራት የተውጣጡ 13 ሺህ 387 ቅጥረኛ ወታደሮች ከዩክሬን ጎን ተሰልፈዋል። ከጠቅላላው ቅጥረኛ ወታደሮች ውስጥም 5 ሺህ 962 ያህሉ በሩሲያ ጦር መገደላቸው ተገልጿል። ፖላንድ ቅጥረኛ ወታደሮችን በማዋጣት ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን 2 ሺህ 960 ዎቹ ተገድለዋል ተብሏል። ከፖላንድ በመቀጠል…
Read More
የብሪክስ መሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ መካሄድ ጀመረ

የብሪክስ መሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ መካሄድ ጀመረ

ከ15 ዓመት በፊት በብራዚል፣ ሩሲያ፣ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የተመሰረተው ብሪክስ የዘንድሮውን ጉባኤ በጆሀንስበርግ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ፒንግ፣ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ተገኝተዋል፡፡ ሩሲያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጊ ላቭሮቭ የተወከለች ሲሆን ፕሬዝዳንት ፑቲን በበይነ መረብ ታግዘው ንግግር አድርገዋል፡፡ የጉባአው አዘጋጅ ደቡብ አፍሪካ ለ60 ሀገራት ግብዣ ያቀረቡ ሲሆን ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በጉባኤው ላይ እንዲገኙ መጋበዛቸውን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ40 በላይ የዓለማችን ሀገራት የብሪክስ አባል ለመሆን ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ሳውዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ የተባበሩት አረብ አምሬት፣ ግብጽ፣ አልጀሪያ እና ሌሎችም ሀገራት ብሪክስን ለመቀላቀል በይፋ…
Read More
ሩሲያ ለአፍሪካ ገበያ በግብጽ የላዳ መኪና ፋብሪካ ልትገነባ መሆኗን ገለጸች

ሩሲያ ለአፍሪካ ገበያ በግብጽ የላዳ መኪና ፋብሪካ ልትገነባ መሆኗን ገለጸች

የሩሲያ ምርት የሆነው ላዳ መኪና በኢትዮጵያ እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተመራጭ ነበሩ። ለዓመታት ገበያውን ተቆጣጥረውት የቆዩት የሩሲያ ላዳ መኪኖች ቀስ በቀስ ከዓለም እና አፍሪካ ገበያዎች እየጠፉ መጥተዋል። ኩባንያው ምርቶቹን ወደ አፍሪካ ገበያዎች ማቅረብ ያቆመው ከቀዝቃዛው ጦርነት ጋር በተያያዘ የሩሲያ ተጽዕኖ እየቀነሰ በመምጣቱ እና በገበያ ውድድር ምክንያት እንደሆነ ድርጅቱ ገልጿል። ሩሲያ ወደ አፍሪካ ገበያዎች ዳግም የመመለስ ፍላጎት ማሳየቷን ተከትሎ ኩባንያው ከወራት በፊት በኢትዮጵያ እና ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ምቹ ሁኔታዎችን ተመልክቶ ተመልሷል። የኩባንያው ሀላፊዎች በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገውም ነበር። ይሁንና በፒተርስግበርግ ከየማ እየተካሄደ ባለው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ መካሄዱን ተከትሎ ኩባንያው ዋና ሙቀመጫውን ግብጽ ለማድረግ መወሰኑን…
Read More
አዲስ አበባ የሩሲያዊ ደራሲ አሌክሳንደር ፑሽኪንን ሐውልት ዳግም ወደ አደባባይ ልትመልስ መሆኗን ገለጸች

አዲስ አበባ የሩሲያዊ ደራሲ አሌክሳንደር ፑሽኪንን ሐውልት ዳግም ወደ አደባባይ ልትመልስ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ የታዋቂውን ሩሲያዊ ደራሲ ፑሽኪን ሐውልትን ወደ አደባባይ ልትመልስ መሆኗን ገለጸች የሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ በፈረንጆቹ 2002 ላይ ነበር የታዋቂውን የሩሲያዊ የስነ ጽሁፍ ሰው አሌክሳንደር ፑሽኪንን ሀውልት በስጦታ መልኩ ለአዲስ አበባ የሰጠችው። ይህ ሀውልት ለረጅም ዓመታት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ስር ባለ አንድ አደባባይን የፑሽኪን አደባባይ በሚል የሰየመችው። በዚህ አደባባይ ላይም የፑሽኪን ሐውልት ተተክሎ የቆየ ቢሆንም የትራፊክ መጨናነቅን ለማስቀረት በሚል አደባባዩ ፈርሷል። የአሌክሳንደር ፑሽኪን ሀውልትም ወደ ኢትዮጵያ ሙዚየም ግቢ ውስጥ እንዲቀመጥ ተደርጎ ቆይቷል። የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለአልዐይን እንዳሉት የፑሽኪን ሀውልት ወደ አደባባይ ወጥቶ ይተከላል ብለዋል። "ሀውልቱ የሩሲያን እና ኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ክብር…
Read More
ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ

ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ

ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ የዓለማችን ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ እና ብዙ ህዝብ ያላቸው ሩሲያ እና ቻይና የኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ የሆነው አማርኛ ቋንቋ ለዜጎቻቸው እንዲሰጥ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ሩሲያ ከቀጣዩ መስከረም ወር ጀምሮ በሞስኮ በሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጻለች፡፡ ትምህርቱ ከቀጣዩ መስከረም 2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል የተባለ ሲሆን በሳምንት ሁለት ክፍለ ጊዜ እንደሚሰጥ በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ገልጸዋል፡፡ ሌላኛዋ አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቿ ለማስተማር የወሰነችው ሀገር ቻይና ስትሆን ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ይሆናል ተብሏል፡፡ ለዚህ እንዲረዳም አማርኛን ለቻይናዊያን ተማሪዎች ለማስተማር የሚያግዘው መጽሀፍ በቤጂንግ…
Read More
በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የግድያ ሙከራ ተፈጸመ

በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የግድያ ሙከራ ተፈጸመ

በሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መኖሪያ በሆነው የክሪምሊን ቤተ መንግስት ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን አርቲ ዘግቧል፡፡ የድሮን ጥቃቱ ያነጣጠረው በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ ሲሆን ጥቃቱ ሲፈጸም ፕሬዝዳንቱ በቦታው አልነበሩም ተብሏል፡፡ የቤተ መንግስቱ ቃል አቀባይ ድሚትሪ ፔስኮቭ እንዳሉት አደጋው በሁለት ድሮኖች የታገዘ ሲሆን የየት ሀገር ስሪት እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም፡፡ በድሮኖቹ ጥቃት የተጎዳ ሰው አለመኖሩን የተናገሩት ቃል አቀባዩ ሞስኮ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ መጀመሯንም አክለዋል፡፡ የሞስኮ ከተማ ከንቲባ በበኩላቸው በከተማዋ ከተፈቀደላቸው የደህንነት ተቋማት ውጪ የድሮን እንቅስቃሴ መታገዱን ገልጸዋል፡፡ ፊንላድን እየጎበኙ ያሉት የዩክሬን ፕሬዝዳንት ከሄልስንኪ እንዳሉት በክሪምሊን ቤተ መንግስት ላይ ተፈጸመ ስለተባለው የድሮን ጥቃት መረጃ የለኝም ብለዋል፡፡
Read More
የሩሲያ መኪና አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሊያደርጉ መሆኑን ገለጹ

የሩሲያ መኪና አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሊያደርጉ መሆኑን ገለጹ

የሩሲያ  የመኪና አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ሲሆኑ በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ ከሩሲያ የላዳ እና ጋዝ ግሩፕ መኪና አምራች ኩባንያዎች የመጡ ተወካዮች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ለተወካዮቹ  በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ፣ ስለዘርፉ ማበረታቻዎች እንዲሁም በአፍሪካ ግንባር ቀደም ስለሆነው የድሬዳዋ የነጻ ንግድ ቀጠና አጠቃላይ ገለጻ ተደረገላቸዋል፡፡ የመኪና አምራች ኩባንያ ኃላፊዎቹ ከድሬዳዋ በተጨማሪ የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የስራ እንቅስቃሴና የምርት ሂደት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡ ኩባንያዎቹ በአውሮፓ፣ በደቡብ አሜሪካና የአፍሪካ ገበያዎች ለጤና ተቋማት፣ ለፀጥታ አካላት፣ ለጭነት አገልግሎት እንዲሁም ለግልና ለህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ…
Read More