Blog

ጦርነቶች እንዲቆሙ በማደራደር የሚታወቁት ዲፕሎማት በ100 ዓመታቸው ህይወታቸው አለፈ

ጦርነቶች እንዲቆሙ በማደራደር የሚታወቁት ዲፕሎማት በ100 ዓመታቸው ህይወታቸው አለፈ

የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሄንሪ ኪሲንገር   በመቶ አመታቸው  አረፉ ታዋቂው ዲፕሎማት እና ተፅዕኖ ፈጣሪ የውጭ ፖሊሲ አሳቢ በኮነቲከት በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ትናንት ለሊት መሞታቸውን የአማካሪ ድርጅታቸው ኪሲንገር አሶሺየትስ በመግለጫው ገልጿል። በፈረንጆቹ በ1969 የፕሬዝዳንት ሪቻርድ ኒክሰን ከፍተኛ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ከመሆናቸው በፊት በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ አግኝተው አለም አቀፍ ግንኙነቶችን አስተምረዋል። የፕሬዚዳንት ጄራልድ ፎርድ የመንግስት ፀሀፊም ሆነው አገልግለዋል። ጎበዝ ተደራዳሪ ተብለው የተወደሱ ሲሆን በ1970ዎቹ አሜሪካ ከሶቪየት ኅብረት ጋር ያለውን ግንኙነት እንድትሻሻል  ኪስንገር ትልቅ ሚና ነበራቸው። አሜሪካ  ከቻይና ጋር ያላትን ግንኙነት የተሻለ ለማድረግ መንገድ ጠርገዋል። እ.ኤ.አ. በ 1973 ኪሲንገር የፓሪስ የሰላም ስምምነትን በማሳካታቸው  ከዲፕሎማት ለዱክ ቶ…
Read More
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቫሌንሺያ ማራቶን እንደሚሳተፍ ገለጸ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቫሌንሺያ ማራቶን እንደሚሳተፍ ገለጸ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሕዳር 23 ቀን 2016 ዓ.ም በሚካሄደው የቫሌንሺያ ማራቶን እንደሚሳተፍ አስታውቋል፡፡ አትሌቱ በፌስቡክ ገጹ እንዳለው "ከብዙ ጊዜ ጉዳት በኋላ በቫሌንሺያ ማራቶን እሳተፋለሁ" ብሏል። "ከብዙ ጉዳት በኋላ ወደ ውድድር በመመለሴ ደስተኛ ነኝ" ያለው አትሌት ቀነኒሳ አኤኤንቲኤ የተሰኘው ኩባንያ ስፖንሰሬ ነው፣ ላደረገልኝ ድጋፍ አመሰግናለሁ " ሲልም ገልጿል። ውድድሩ የፊታችን ሕዳር 23 ቀን 2016 ዓ.ም በስፔኗ ቫሌንሲያ እንደሚካሄድ ተገልጿል። አትሌት ቀነኒሳ በአምስት እና አስር ሺህ ውድድሮች ላይ ለዓመታት ሳይረታ የቆየ ውጤታማ አትሌት ሆኖ ቆይቷል። በሁለቱም ርቀቶች የዓለም ሪከርዶችን ለ16 ዓመታት ይዞ የቆየው አትሌት ቀነኒሳ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ፊቱን ወደ ማራቶን ውድድር አዙሯል። የማራቶን ውድድርን ከሁለት ሰዓት በታች ይገባል ተብሎ ከሚጠበቁት…
Read More
በአዲስ አበባ 100 ሺህ ሰዎች የሚሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ

በአዲስ አበባ 100 ሺህ ሰዎች የሚሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ

የኢትዮጰያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ እንደገለጸው መነሻውን አራት ኪሎ ያደረገ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለከንቲባ ቢሮ ማስገባቱን ገልጿል፡፡ ሰላማዊ ሰልፉ "ጦርነት ይቁም! ሠላም ይስፈን፣ መከላከያ ሰራዊቱ ባስቸኳይ ወደ ካምፕ ይግባ!" በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄደውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማስቆም በሚል የተዘጋጀው ይህ ሰላማዊ ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ. ም በሀገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሏል፡፡ የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች ደብዳቤውን ጦርነት እንዲቆም፣ መከላከያ ሠራዊቱ ከዘመተባቸው ክልሎች ወጥቶ ወደ ጦር ካምፑ እንዲመለስና ፖለቲካዊ ውይይቶች እንዲከፈቱ በሰልፉ ላይ እንጠይቃለንም ብለዋል፡፡ የኢትዮጰያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ /ኢህአፓ/ እና ሌሎች ዜጎች አስተባባሪነት የተጠራው ይህ ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት…
Read More
የፈረንሳዩ ኩባንያ የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ ለመግዛት የጀመረውን ጥረት እቅድ ሰረዘ

የፈረንሳዩ ኩባንያ የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ ለመግዛት የጀመረውን ጥረት እቅድ ሰረዘ

ኦሬንጅ የተሰኘው የፈረንሳይ የቴሌኮም ኩባንያ ከኢትዮቴሌኮም 45 በመቶ አካባቢ ድርሻ ለመግዛት ዕቅድ የነበረው ቢሆንም ኃሳባችንን በፍጥነት ለመተግበር እና ውጤት ለማግኘት የሚያስችል ሁኔታ ባለመኖሩ ራሴን አግልያለሁ ብሏል። ኢትዮጵያ ከመንግስታዊው ኢትዮቴሌኮም እና በቅርቡ ገበያውን ከተቀላቀለው ከሳፋሪኮም በተጨማሪ ሦስተኛ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ስራ እንዲጀምር ፈቃድ ለመስጠት ገበያውን እየገመገመ የቆየች ሲሆን በቅርቡ የገበያው ሁኔታ የታሰበውን ያህል አመርቂ ባለመሆኑ ሐደቱ ተቋርጧል ማለቷ ይታወሳል። ከዚህ ጎን ለጎን ከኢትዮቴሌኮም ከግማሽ ያነሰ ድርሻ ለመሸጥም እየጣረች ሲሆን ኦሬንጅ ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት ካሳዩት ዓለምአቀፍ ግዙፍ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ነበር። ኩባንያው ሞባይል ለዎርልድ ላይቭ እንደገለፀው ከ2021 ጀምሮ የነበረውን ፍላጎት አሁን መግታቱን ይፋ አድርጓል። ኦሬንጅ ግሩፕ በጉዳዩ ላይ ትንተና ከሠራ በኋላ “ስትራቴጂያችንን…
Read More
በጦርነት በተጎዳችው ትግራይ የ6 ቢሊዮን ብር ብረት ማምረቻ ፋብሪካ ሊገነባ እንደሆነ ተገለጸ

በጦርነት በተጎዳችው ትግራይ የ6 ቢሊዮን ብር ብረት ማምረቻ ፋብሪካ ሊገነባ እንደሆነ ተገለጸ

በ6 ቢሊዮን ብር ወጪ በኢትዮጵያ እና ቻይና ባለሃብቶች ትብብር የብረታ-ብረት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በመቐሌ ከተማ ሊገነባ ነው። በአስር ወራት ውስጥ የሚገነባው ይህ ኢንዱስትሪ የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ ይፋ ተደርጓል። በዚህ ወቅት የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ፤ የሌጀንድ ብረታብረት ኢንዱስትሪ ሃላፈነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ አስፈጊው ድጋፍ ይደረግለታል ብለዋል። ሌሎች በግልና በማህበር የተደራጁ ባለሃብቶችም የዚህን የልማት ፕሮጀክት አርአያ ተከትለው በማልማት  ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ መልእክት አስተላልፈዋል። የብረታብረት ማምረቻው 75 በመቶ በኢትዮጵያዊው ባለሃብት ኢንጅነር ያሬድ ተስፋይ የተሸፈነ ሲሆን ቀሪው 25 በመቶ ደግሞ በቻይናዊው ባለሃብት ሚስተር ሊ ዮን መሸፈኑን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ሳምሶም ገብረመድህን ገልጸዋል።…
Read More
ኢትዮጵያ 28 የመስኖ ግድቦችን በመገንባት ላይ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ 28 የመስኖ ግድቦችን በመገንባት ላይ መሆኗን ገለጸች

የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር እንደገለጸው ኢትዮጵያ 28 የመስኖ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በግንባታ ላይ ካሉት የመስኖ ግድቦች ውስጥም 13ቱን በተያዘው የ2016 ዓመት በከፊል ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ በዚህ ዓመት እንዲጠናቀቁ በሚል እየተገነቡ ላሉ ግድቦችም 8 ነጥብ 03 ቢሊዮን ብር መመደቡ ተመልክቷል፡፡ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብዙነህ ቶልቻ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጀት እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ 28 የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታቸው በመከናወን ላይ ነው፡፡ 13 የመስኖ ፕሮጀክቶች በከፊል ሲጠናቀቁ 2 ሺህ 450 ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችሉ እንደሆኑም ሃለፊው ተናግረዋል፡፡ እየተገነቡ ካሉት ግድቦች በተጨማሪም 27 አዲስ የመስኖ ግድቦችን ለመገንባት የጥናትና ዲዛይን…
Read More
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ስለባህር በር አስተያየት ሲሰጡ እንዲጠነቀቁ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ስለባህር በር አስተያየት ሲሰጡ እንዲጠነቀቁ ተጠየቀ

ባለስልጣናት ስለ ባህር በር ጉዳይ የሚሰጡት መግለጫ የተጠናና ጥንቃቄ የተሞላበት መሆን እንዳለበት ምሁራን አሳስበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የባህር በር ዙሪያ የምሁራን ውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ በዚህ የምሁራን መድረክ ላይ ጥናት ያቀረቡና ውይይት ያደረጉ ምሁራን፣ መንግሥት ስለባህር በር የሚሰጣቸው መረጃዎች የጎረቤት አገሮችን የማያሠጉና ጥንቃቄ የተሞላባቸው እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡ ‹‹ፍትሐዊ የወደብ አጠቃቀም ለአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና ልማት›› በሚል ርዕስ በተስተናገደው በዚህ ዓውደ ጥናት ላይ፣ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ባለቤት መሆን ስለምትችልባቸው አማራጮች ሰፊ ምሁራዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በጥናት መድረኩ ላይ ለኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄን በማስመለስ ታሪካዊ ድል ያስመዘገቡ ያለፈው ትውልድ ምርጥ ተሞክሮ ታሪካዊ ድል እንደነበር ተገልጿል፡፡ በሰላማዊ መንገድ ኤርትራን በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር…
Read More
በሀሪ ማጓየር ላይ ትችት የሰነዘሩት ጋናዊ የፓርላማ አባል ይቅርታ ጠየቁ፡፡

በሀሪ ማጓየር ላይ ትችት የሰነዘሩት ጋናዊ የፓርላማ አባል ይቅርታ ጠየቁ፡፡

የአፍሪካዊቷ ጋና ህግ አውጪ ምክር ቤት አባል የሆኑት አይዛክ አዶንጎ ከአንድ ዓመት በፊት የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንትን ከማንችስተሩ ተከላካይ ተጫዋች ሀሪ ማጓየር ጋር ተመሳሳይ እንደሆኑ ተናግረው ነበር፡፡ የፓርላማ አባሉ በወቅቱ “የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት እንደ ማጓየር በራሱ ላይ ግብ የሚያስቆጥር፣ ጠንካራ የስራ አጋሮቹን መትቶ የሚጥል እና እንዲቀጡ ለዳኛ አቤት የሚል ነው” ሲሉ ተናግረው ነበር፡፡ ግለሰቡ ይህን ንግግር ያደረጉበት ተንቀሳቃሽ ምስል በተለያዩ ማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ ለብዙ ሰዎች መድረስ ችሏል፡፡ እኝህ የህግ አውጪ አባል “ስለ ማጓየር ከዚህ በፊት የተናገርኩት አስተያየት ስህተት ነበር፣ ማጓየርን ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ ተጫዋቹ አሁን ላይ ምርጥ ተከላካይ መሆኑን አስመስክሯል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ይሁንና ለጋና ምክትል ፕሬዝዳንትን ግን ይቅርታ አልጠይቅም ያሉት…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስራኤል አቋርጦት የነበረውን በረራ እንደሚጀምር ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስራኤል አቋርጦት የነበረውን በረራ እንደሚጀምር ገለጸ፡፡

ሃማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ እና ያለተጠበቀ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ከተጀመረ 47ኛ ቀኑን ይዟል። ከሁለቱም ወገን 15 ሺህ ገደማ ሰዎች የተገደሉበት ይህ ጦርነት እንዲቆም በርካቶች ሲያሳስቡ ቢቆዩም ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ በጦርነቱ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን አየር መንገዶች ወደ እስራኤል ሲያደርጉት የነበረውን በረራ አቋርጠው ቆይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን በረራ ዳግም እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡ አየር መንገዱ አክሎም በሳምንት አምስት ቀናት ከአዲስ አበባ-ቴልአቪቭ ከተማ የቀጥታ በረራውን እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡ የደርሶ መልስ ትራንስፖርት አገልግሎቱን በበረራ መስመር ኢት 404 እና 405 አውሮፕላኖቹ  እንደሚሰጥ የገለጸው አየር መንገዱ ሁሉንም የሳምንቱ ቀናት…
Read More
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቡርኪናፋሶ አቻው 3 ለ 0 ተሸነፈ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቡርኪናፋሶ አቻው 3 ለ 0 ተሸነፈ

ዋልያዎቹ በዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣርያ ጨዋታ በቡርኪና ፋሶ አቻቸው 3 ለ 0 ተሸንፈዋል፡፡ የቡርኪናፋሶን የማሸነፊያ ግቦች ብላቲ ቱሬ በ69 ኛው፣ በርትራንድ ትራኦሬ በ78ኛው እንዲሁም ዳንጎ ኦታትራ 90ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም በ2026 ካናዳ ሜክሲኮ እና አሜሪካ በጥምረት ለሚያዘጋጁት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አንድ የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድቡ 1 ነጥብ በመያዝ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ የአለም ዋንጫ የምድቡን ሶስተኛ እና አራተኛ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከጊኒ ቢሳኦ እና ጅቡቲ ጋር የሚያደርግ ይሆናል፡፡
Read More
የአሜሪካው ራክሲዮ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የዳታ ማዕከሉን በኢትዮጵያ ከፈተ

የአሜሪካው ራክሲዮ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የዳታ ማዕከሉን በኢትዮጵያ ከፈተ

የዳታ ማዕከሉ 30 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት ሲሆን በአፍሪካ 2ኛዉን የዳታ ማዕከል በአዲስ አበባ ከፍቷል። በአፍሪካ ገለልተኛ የመረጃ ማዕከል የሆነዉ ራክሲዮ ግሩፕ በኢትዮጵያ 2ኛዉን የዳታ ማዕከል በ30 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ኢንቨስትመንት በመገንባት አስጀምሯል። ኩባንያው የዳታ ማዕከሉን በአዲስ አበባ በአይሲቲ ፓርክ ውስጥ መክፈቱን የገለጸ ሲሆን የዳታ ፍሰትን ሙሉ በሙሉ በአገር ዉስጥ በማድረግ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ድርጅቶች ለኢንተርኔት የሚያወጡትን ወጪ ለመቀነስ ይረዳል ተብላል። በኢትዮጵያ የተከፈተዉ አዲሱ የደረጃ III የመረጃ ማዕከል 800 ራኮች እና እስከ 3MW የአይቲ ሃይል አለዉ ተብሏል። በ2018 የተቋቋመዉ ራክሲዮ በአፍሪካ የመጀመሪያውን የዳታ ማዕከል በኡጋንዳ እንደከፈተ ገልጿል። ኩባንያው ሁለተኛውን የዳታ ማዕከል በኢትዮጵያ ዛሬ ያስጀመረ ሲሆን እስከ ሚቀጥለው ዓመት ድረስም በኮንጎ  ፣…
Read More
ኢትዮጵያ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ዶላር መገኘቱ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በአራት ዓመታት ውስጥ ወደ ውጪ ሀገራት ከተላኩ ምርቶች አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ። በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በዓመት 17 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የሚያስገኙ የተለያዩ የፕላስቲክ ቱቦዎችን የሚያመርት ፋብሪካ ተመርቆ ሥራ ጀምሯል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ታደሠ፤ ኮርፖሬሽኑ ከሚያስተዳድራቸው 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮች የተለያዩ ምርቶች ለውጭ ገበያ እየቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል። ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ለተለያዩ ሀገራት ገበያ ከሚያቀርቧቸው ምርቶች በአራት ዓመታት ውስጥ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ሀላፊው ተናግረዋል፡፡ ከውጭ ሀገራት ይገቡ የመበሩ ምርቶችን በሀገር…
Read More
የኦሮሚያ ክልል ከአንድ ሺህ በላይ ሃኪሞችን ለመቅጠር ቢፈልግም ተቀጣሪ ማጣቱን ገለጸ

የኦሮሚያ ክልል ከአንድ ሺህ በላይ ሃኪሞችን ለመቅጠር ቢፈልግም ተቀጣሪ ማጣቱን ገለጸ

የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ 1ሺህ 1መቶ ሀኪሞችን ለመቅጠር ባለፈዉ ዓመት ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም ማስታወቂያ ቢያወጣም ተቀጣሪዎችን ባለማግኘቱ በጀቱን ወደ ሌላ ዘረፍ ማዛወሩን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቋል፡፡ የቢሮዉ ምክትል ሃላፊ ዶ/ር ጉሻ በለኮ በሰኔ 2015 ላይ 1ሺህ 1መቶ ሀኪሞችን ለመቅጠር ማስታወቂያ የወጣ ቢሆንም ተቀጣሪዎችን ባለማግኘቱ ቢሮዉ በጀቱን ለሌላ ጉዳይ ማዋሉን ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡ ለ 2 ወራት ያክል ማስታወቂያዉን ክፍት ባደርግም ገበያ ላይ ተቀጣሪዎችን አላገኘሁም ብሏል ቢሮዉ፡፡ በየአንዳንዱ ጤና ተቋም ሀኪሞች መኖር ስላለባቸዉ ያንን ለማሟላት ማስታወቂያ ብናወጣም ሀኪሞችን ባለማግኘታችን በምትኩ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን፣ አዋላጆችን እና ነርሶችን ለመቅጠር ተገደናል ነዉ ያሉት፡፡ ከዚህ በፊት ለመላዉ ኦሮሚያ አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር 72ሺህ ነበር ያሉት…
Read More
ኢትዮጵያ ረጅም ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ልታግድ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ ረጅም ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ልታግድ መሆኗን ገለጸች

በአዲስ አበባ ከፍተኛ ጭስ የሚለቅ መኪና ያላቸው አሽከርካሪዎች አስቀድመው መፍትሄ እንዲያዘጋጁ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ ተሸከርካሪዎች የሚለቁትን ጭስ የሚለካ መሳሪያ እና ጥራት ማስጠበቂያ ወይም ስታንዳርድ በመዘጋጀት ላይ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ድዳ ድሪባ እንደተናገሩት የመኪና ጭስ ስታንዳርድ እየተዘጋጀ ነው የተባለ ሲሆን እያንዳንዱ መኪና የሚያስወጣው ጪስ ይለካል ተብሏል። መኪናው ከተቀመጠው መለኪያ በላይ ጪስ የሚያመነጭ ከሆነ አገልግሎት እንዳይሰጥ ይደረጋል ብለዋል። አብዛኛውን ጊዜ ከፍተኛ ጭስ የሚለቁ ተሽከርካሪዎች ከተመረቱ 23 ዓመትና ከዚያ በላይ ያገለገሉ ናቸው ያሉት ኃላፊው፤ ስለዚህ አሮጌ መኪና ያላቸው አሽከርካሪዎች ከአሁኑ መፍትሄ ሊያዘጋጁ ይገባል ብለዋል። በመዲናዋ አሮጌና ከፍተኛ ጭስ የሚለቁ በርካታ መኪኖች መኖራቸውን…
Read More
ኖህ ሪል ኢስቴት 754 መኖሪያ ቤቶችን አስመረቀ

ኖህ ሪል ኢስቴት 754 መኖሪያ ቤቶችን አስመረቀ

ኖህ ሪል እስቴት አስረኛ ዓመቱን 754 አዳዲስ መኖሪያ ቤቶችን በማስረከብ አክብሯል ኖህ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር 10ኛ አመት የምስረታ በአሉን  754 አዳዲስ የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በማስረከብ አክብሯል። በኢትዮጵያ የከተማ ልማት ከፍተኛ እድገት አበርክቶ ያለው ኖህ ሪል ኢስቴት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ደንበኞቹና የሚዲያ አባላት ጋር አክብሯል። ኖህ ሪል እስቴት ባለፉት አስርት አመታት 8,000 በላይ ለሆኑ ቤተሰቦች በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ ቤቶችን በታማኝነት፣ በሰዐቱ እና በቃሉ መሰረት አስረክቧል። ይህ ጉዞ ኩባንያውን በኢትዮጵያ የቤቶች ልማት ዘርፍ ቁልፍ ተዋናይ ሆኖ እንዲቀጥል አስችሎታል።  ለአገራዊ የልማት ግቦች ስኬትም ትልቅ አስተዋፅዖ እያደረገ ይገኛል። የኖህ ሪል ኢስቴት ዋና ስራ አስፈፃሚ ንፁህ አዉግቸዉ “በዛሬው ዕለት በኖህ ግሪን ፓርክ ሳይት አዲስ የተገነባውን …
Read More
አቦል ቴሌቪዥን “ዳግማዊ” እና “ቁጭት” የተሰኙ አዲስ ተከታታይ ድራማዎችን ማስተላለፍ ሊጀምር ነው

አቦል ቴሌቪዥን “ዳግማዊ” እና “ቁጭት” የተሰኙ አዲስ ተከታታይ ድራማዎችን ማስተላለፍ ሊጀምር ነው

አቦል ቴሌቪዥን ከሰኞ ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሁለት አዳዲስ “ሀገርኛ” ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማዎችን ለተመልካቾቹ ላቀርብ ነው ብሏል፡፡ ለተመልካቾች የሚቀርቡት “ቁጭት” የተሰኘው ረጅምና ወጥ ሀገርኛ ተከታታይ ቴሌኖቬላ እና “ዳግማዊ” የተሰኘው በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው ድራማ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ይዘቶች አቦል ቴሌቪዥን ለደንበኞቹ ምርጥ ወጥ ሀገርኛ ይዘቶችን ለማቅረብ የወጠነውን ጅምር በተግባር የሚያረጋግጡና ቻናሉ የላቁ መዝናኛዎችን ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ናቸው። “ቁጭት” የተሰኘው ሀገርኛ ቴሌኖቬላ ታሪኩ የሚያጠነጥነው በሕይወት ጥቂት ወራት ብቻ እንደሚቀረው ከተነገረው በኋላ የናፈቀውን ልጁን ዮናስን ለማግኘት ፍለጋ በጀመረ አባት ነው፡፡ ድርጊቱ በተስፋ ማጣት እና በድህነት ውስጥ ያለን የሕይወት ውጣውረድም የሚያስቃኝ ሲሆን ዮናስ የአባቱን ህልውና እና ባለጸጋነት ታሪክ ሳያውቅ ሕይወቱ…
Read More
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ግጭት ውስጥ መግባቷን አመነች

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ግጭት ውስጥ መግባቷን አመነች

የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥታል። የሚንስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በተለያዩ የዲፕሎማሲ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ ማብራሪያ ከሰጡባቸው ጉዳዮች መካከል ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ልማት ባንክ መክፈል ያለባትን ብድር ከመክፈል ጋር በተያያዘ አለመግባባት ተፈጥሯል የሚለው ጉዳይ ነው። አለመግባባቱ በኢትዮጵያ ገንዘብ ሚንስቴር እና በአዲስ አበባ ካለው የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ቢሮ ጋር መካከል ነው የተባለ ሲሆን በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያትም ባንኩ ቢሮውን ዘግቶ ሆዷል የሚል ነበር። በሁለቱ አካላት መካከል የተፈጠረው ግጭት ምንድን ነው? ባንኩስ የኢትዮጵያ ቢሮውን ዘግቶ ወጥቷል? በሚል ለአምባሳደር መለስ ዓለም ጥያቄ ከጋዜጠኞች ቀርቦላቸው ነበር። አምባሳደር መለስ በምላሻቸውም "ከአፍሪካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ…
Read More
አሜሪካ በኢትዮጵያ ያቋረጠችውን እርዳታ ልትጀምር መሆኗን ገለጸች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያቋረጠችውን እርዳታ ልትጀምር መሆኗን ገለጸች

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ከመጪው ወር ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ አጀምራለሁ ብሏል፡፡ የአሜሪካ  መንግስት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ካሳለፍነው ሰኔ ወር ጀምሮ በምግብ እርዳታ ስርቆት ምክንያት እርዳታ መስጠቱን ማቆሙ ይታወሳል፡፡ በለጋሾች የተገዛ የምግብ እርዳታ ለገበያ መቅረቡና ወደ ውጪ አገራት ጭምር መላኩን የጠቀሰው የተራድኦ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የእርዳታ ስርጭቱን በተመለከተ ተከታታይ ውይይት ማድረጉን ገልጿል። በዚህም ባለፈው ወር በሀገሪቱ ለሚገኙ ስደተኞች የምግብ እርዳታ ማቅረብ የጀመረ ሲሆን ከመጪው ወር ጀምሮ ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እርዳታ ማቅረብ እንደሚጀምር ገልጿል። ኢትዮጵያ የምግብ ድጋፍ ስርጭት ስርአቷን በመሰረታዊነት የሚያስተካክል ስራ መከወኗንና ለጋሽ ድርጅቶች እርዳታው ለተገቢው አካል መድረሱን እንዲከታተሉ መስማማቷን ድርጅቱ አስታውቋል። ለጋሽ…
Read More
ስድስት ዩንቨርሲቲዎች የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ ተገለጸ

ስድስት ዩንቨርሲቲዎች የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ ተገለጸ

ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎችን እንደሚመድብ ገልጿል፡፡ ይሁንና ስድስት የመንግስት ዩንቨርሲቲዎች የሬሚዲያል ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ አስታውቋል፡፡ የሬሚዲያል ተማሪዎችን ከማይቀበሉ ዩንቨርሲቲዎች መካከልም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ አርሲ ዩኒቨርሲቲ እና ኮተቤ የትምህርት ዪኒቨርሲቲዎች ናቸው፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር እነዚህ ዩንቨርሲቲዎች ለምን የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ ምክንያታቸውን አልጠቀሰም፡፡ በ2015 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ 845 ሺሕ 099 ተማሪዎች ውስጥ፤ 817 ሺሕ 838 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች የሆነ ውጤት ማምጣታቸው ይታወሳል፡፡ የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ከአጠቃላይ 845 ሺሕ 099 ተፈታኞች ውስጥ…
Read More
የሱዳን ጦር አዛዥ ጀነራል አልቡርሃን ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

የሱዳን ጦር አዛዥ ጀነራል አልቡርሃን ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

የሱዳን ሉአላዊ ምክርቤት ፕሬዝዳንትና የሀገሪቱ ጦር አዛዥ ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ጀነራል አልቡርሃን በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታና በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ይወያያሉ ተብሏል። ሰባተኛ ወሩን የያዘው የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ጦርነት ከ9 ሺህ በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል። ከ5 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ያፈናቀለው ጦርነት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲቆም የሚደረገው ጥረትም ቀጥሏል። ሁለቱ ሃይሎች በሪያድ በተደጋጋሚ ለድርድር ቢቀመጡም እስካሁን ከስምምነት ላይ አልደረሱም። በአዲስ አበባም በቅርቡ በሱዳን የሽግግር መንግስት ለማቋቋም ያለመና ከ80 በላይ የሀገሪቱ የፖለቲካና ሲቪል ድርጅቶች የተሳተፉበት ምክክር መደረጉ አይዘነጋም። በካርቱም የሚገኘው ኤምባሲዋ በአየር የተደበደበባት ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት…
Read More
ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ጥምረትን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ተገለጸ

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ጥምረትን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ተገለጸ

ከ24 ዓመት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን የኢኮኖሚ ትስስር ለማሳለጥ የተቋቋመው የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ጥምረት በየጊዜው አዳዲስ አባላትን በመሳብ ላይ ይገኛል። ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ከአንድ ዓመት በፊት ይህን ጥምረት ለመቀላቀል በይፋ መጠየቋ ይታወሳል። ጥምረቱም የመቋዲሾን ጥያቄ ለመመለስ ባለሙያዎቹን አሰማርቶ የተለያዩ ግምገማዎችን ሲያደርግ ቆይቶ ሶማሊያን ስምንተኛዋ አባል ሀገር አድርጎ እንደሚቀበል አስታውቋል። ዋና መቀመጫውን አሩሻ ታንዛኒያ ያደረገው ይህ የኢኮኖሚ ጥምረት በሚቀጥለው ሳምንት በሚያደርገው ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ሶማሊያን በይፋ በአባልነት እንደሚቀበል ገልጿል። የጥምረቱ ዋና ጸሀፊ ፒተር ማቱኪ በሞሮኮ ማራካሽ በተካሄደው የኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ እንዳሉት "ሶማሊያ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አባል ትሆናለች" ብለዋል። ዋና ጸሀፊው አክለውም "የጥምረቱ ቀጣይ አባል ሀገር ኢትዮጵያ ልትሆን ትችላለች፣ ኢትዮጵያ…
Read More
የማራቶን ባለ ሪከርዷ አትሌት ትግስት አሰፋ ለዓለም ምርጥ የዓመቱ አትሌቶች ሽልማት የመጨረሻውን ዙር ተቀላቀለች

የማራቶን ባለ ሪከርዷ አትሌት ትግስት አሰፋ ለዓለም ምርጥ የዓመቱ አትሌቶች ሽልማት የመጨረሻውን ዙር ተቀላቀለች

አትሌት ትግስት አሰፋ ለአለም አትሌቲክስ በዓለም ምርጥ የዓመቱ አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱ ምርጥ 10 የዓለም አትሌቶች መካከል አንዷነበረች። የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2023 ዓመት በተካሄዱ የተለያዩ ውድድሮች ላይ ስኬታማ የሆኑ አትሌቶችን ዝርዝር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በመጀመሪያው ዙር 11 ምርጥ የዓለማችን አትሌቶች ዝረዝር ውስጥም የ5 ሺህ ሜትር ባለ ሪከርዷ ጉዳፍ ጸጋዬ እና የማራቶን ባለሪከርዷ አትሌት ትግስት አሰፋ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ አትሌቶች ነበሩ። ዎርልድ አትሌቲክስ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በውድድሩ ለመጨረሻ ዙር ያለፉ አትሌቶችን ዝርዝር አውጥቷል። በዚህም የማራቶን ባለሪከርዷ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት አሰፋ ለመጨረሻ ዙር ውድድር ከቀረቡ አትሌቶች መካከል እንዷ ሆናለች። ከአትሌት ትግስት አሰፋ በተጨማሪ ኬንያዊቷ አትሌት ፋይዝ ኪፕዬጎን፣ ጃማይካዊቷ ሸሪካ ጃክሰን፣ የኔዘርላንዷ…
Read More
የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ጃል መሮ ፊት ለፊት ተገናኙ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ጃል መሮ ፊት ለፊት ተገናኙ

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራር እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መሪው ጃል መሮ ፊት ለፊት መገናኘታቸው ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛኒያ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር መጀመራቸው ተሰምቷል። ቢቢሲ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ የሰላም ንግግሩ ጥቂት ቀናትን እንዳስቆጠረና ከሁለቱም ወገኖች የተወጣጡ የጦር አባላት ተወካዮች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል። ከዚህ ቀደም ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው ዛንዚባር የተካሄደውን ድርድር የምሥራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ)፣ አሜሪካ፣ ኖርዌይ እና ኬንያ አስተባባሪ እና አሸማጋይ ሚና መውሰዳቸው ይታወሳል። አሁን የተጀመረውን ንግግር ማን እንደሚያደራድር ግልጽ ባይሆንም፣ ኢጋድ ከዚህ ቀደም የነበረውን ሚና ሳያስቀጥል እንዳልቀረ ተጠቅሷል። ከዚህ በተጨማሪ አዲስ…
Read More
አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ዋልያዎቹን በአሰልጣኝነት ተረከቡ

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ዋልያዎቹን በአሰልጣኝነት ተረከቡ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሐየራዊ ቡድን አሰልጣን የነበሩት ገብረመድህን ሀይሌ በድጋሚ ዋልያዎቹን እንዲያሰለጥኑ ተመርጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው የኢትዮጵያ መድን እግር ኳ ክለብን በማሰልጠን ላይ የነበሩት አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ በአንድ ዓመት ውል ብሔራዊ ቡድኑን እንዲያሰለጥኑ ተመርጠዋል፡፡ አሰልጣኙ የብሔራዊ ቡድን ስራቸውን ከኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ክለብ ጋር ደርበው እንዲያካሂዱ ከፌዴሬሽኑ ጋር እንደተስማሙም ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ የሚያደርጋቸውን ሁለት ቀጣይ የሜዳው ጨዋታዎችን ወደ ሞሮኮ ተጉዘው ያካሂዳሉም ተብሏል። የመጀመርያው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከሴራሊዮን ኅዳር 5 እንዲሁም ሁለተኛው ጨዋታ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ኅዳር 11 የሚደረግ ሲሆን ሁለቱም ጨዋታዎች በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ይደረጋሉ፡፡ ብሄራዊ ቡድኑን በኢንተርናሽናል ውድድር ተፎካካሪ ማድረግ የሚጠብቅባቸው አሰልጣኝ ገብረመድህን…
Read More
የጸጋ ተስፋዎች እና በህይወት የመኖር ትግል

የጸጋ ተስፋዎች እና በህይወት የመኖር ትግል

ጸጋ ትባላለች በትግራይ ክልል ደንጎላት በተባለ አካባቢ የተወለደች ሲሆን እድገቷም ሆነ የትዳር ሕይወቷን በዚያው ያደረገች ወጣት እናት ናት። ጸጋ ወደ ትዳር ስትገባ የ16 ዓመት ታዳጊ ነበረች በወቅቱ በቤተሰብ ስምምነት በተፈጸመው በዚህ ትዳር 2 ሴት እና 2 ወንድ በአጣቃላይ 4 ልጆችን አፍርተውበታል። በወቅቱ በነበሩበት አካባቢ በቆሎ በማምረት እና በመሸጥ ከባለቤቷ ጋር ጥሩ ኑሮ ይኖሩ የነበሩ ሰዎችም ነበሩ። ነገር ግን ይህ ጥሩ የሚባለው ኑሮ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ የተገላቢጦች እየሆነ መጣ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተፈጠረው ጦርነት ነገሮች መስመራቸውን እየለቀቁ መጡ... በወቅቱ የንግድ እንቅስቃሴዎች እየቀነሱ መምጣታቸው መሠረታዊ የሚባሉ ነገሮች በተለይም ምግብ ነክ ሸቀጦች ዋጋቸው የማይቀመስ ሆነ እንደ ቡና፣ ጨው፣ ስኳር እና መሰል ነገሮችን ማግኘት…
Read More
ኢትዮጵያ ሶስተኛዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ማምጠቂያ ጊዜን አራዘመች

ኢትዮጵያ ሶስተኛዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ማምጠቂያ ጊዜን አራዘመች

ኢትዮጵያ ETRSS-02 የሚል ስያሜ የተሰጣትን ሶስተኛዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት በወራት ውስጥ እንደምትመጥቅ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም መራዘሙ ተገልጿል፡፡ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከሶስት ወራት በፊት በሰጠው መግለጫ በቅርቡ ሶስተኛዋን ሳተላይት አመጥቃለሁ ሲል ገልጾ ነበር፡፡ ይሁንና ETRSS-02 የተሰኘችው ሳተላይት በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ እንደምትመጥቅ አስታውቋል፡፡ ከዚህ በፊት በቻይና አጋዥነት ወደ ሕዋ የመጠቁት ሳተላይቶች የተቀመጠላቸውን የአገልግሎት ጊዜ በመጨረስ ተልዕኳቸውን በስኬት ማጠናቀቃቸውም ኢንስቲትዩቱ ገልጿል። የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ፤ ሶስተኛውን ሳተላይት መምጠቅን በተመለከተ መንግስት የፋይናንስና የኢኮኖሚ አዋጪነት ጥናት ማድረጉን ገልጸዋል። ጥናቱ ከዚህ በፊት ወደ ሕዋ ከመጠቁት ሳተላይቶች ተሞክሮ በመውሰድ የቀጣዩን ሳተላይት መረጃ ከመጠቀም አልፎ ሌሎች ተልዕኮዎችን በግልጽ ማስቀመጡንም አመልክተዋል። የሳተላይቱን ጨረታ…
Read More
የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ አንድ ዓመት ሞላው

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ አንድ ዓመት ሞላው

ህወሀት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝን ማጥቃቱን ተከትሎ ነበር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተቀሰቀሰው። ለሁለት ዓመት የዘለቀው ይህ ጦርነት 800 ሺህ ገደማ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን እንዲያጡ ሲያደርግ 26 ቢሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ ኪሳራም አድርሷል። ለዚህ ጦርነት መቆም ምክንያት የሆነው የሰላም ስምምነት ከአንድ ዓመት በፊት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተፈርሟል። የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ስለ ስምምነቱ እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በፌደራል መንግሥት እና ትግራይ ሀይሎች መካከል የተካሄደው የሰላም ስምምነት ለኢትዮጵያ ምን ጥቅም አስገኘ? በሚል ከጋዜጠኞች ጥያቄ ለቃል አቀባዩ ተነስቶላቸዋል። አምባሳደር መለስ በምላሻቸውም " ስምምነቱ በሁለቱ ወገኖች መካከል ጦርነት እንዲቆም ከማድረግ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ላይ…
Read More
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ የቴሌኮም አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ የቴሌኮም አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ

ሳፋሪኮም በትግራይ ክልል የኔትወርክ እና መሠረት ልማት ዝርጋታ በሚቀጥሉት ሳምንታት እንደሚጀምር ገልጿል ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ የገባው ሳፋሪኮም ከትግራይ ክልል ውጪ በመላው አገሪቱ የቴሌኮም አገልግሎቱን ለደንበኞቹ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት የቴሌኮም አገልገሎቱን ማቅረብ ያልቻለው ይህ ኩባንያ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ አገልግሎት እጀምራለሁ ብሏል፡፡ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሔለፑት ወደ ትግራይ ክልል አምርተው ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳድር አመራሮች ጋር መምከራቸውን ድርጅቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡ በሚቀጥሉት ሳምንታት በትግራይ ክልል የኔትወርክ እና የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ለማካሄድ በሚያስችለውን ውይይት ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር አድርጓል፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው እና ሌሎች ሰራተኞች ወደ መቀሌ ከተማ ተጉዘው ከጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው…
Read More
በኢትዮጵያ የአህያ ቁጥር በፍጥነት እየቀነሰ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የአህያ ቁጥር በፍጥነት እየቀነሰ መሆኑ ተገለጸ

በአህያ ደህንነት ዙሪያ የሚሰራው ብሩክ ኢትዮጵያ የተሰኘው የእንስሳት መብት ተሟጋች ድርጅት የአህያ ቁጥር እየቀነሰ መሆኑን ገልጿል፡፡ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የአህያ ስጋን ወደ ውጪ ሀገራት መላክ የተጀመረ ሲሆን ዓላማውም የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት እንደሆነ ይገለጻል፡፡ በዚህ የአህያ እርድ3 እና ንግድ ምክንያት የአህያ ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን እና ይህም እንዳሳሰበው ብሩክ ኢትዮጵያ የተሰኘ የአህያ መብት ተሟጋች ድርጅት አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ አህያ እንዲታረድ እና ስጋና ቆዳው ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ መደረጉ እንደ አገር የአህያ ቁጥር እየተመናመነ እንዲመጣ ማድረጉን የብሩክ ኢትዮጵያ ድርጅት አማካሪ ይልማ አበበ ለመናኃሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ በኢትጵያ የአህያ እርድ በቻይና ባለሃብቶች በመስፋፋቱ ለአገር የውጭ ምንዛሪን ቢያስገኝም፤ እንደ አገር የአህያ መኖር ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ ደረጃ ላይ…
Read More
አየርላንድ ለኢትዮጵያ የምግብ ደህንነት 8.4 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ተስማማች

አየርላንድ ለኢትዮጵያ የምግብ ደህንነት 8.4 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ተስማማች

የገንዘብ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር እና የአየርላንድ መንግሥት በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል። የ8 ሚሊየን 400 ሺሕ ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቱን የፈረሙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ እና የአየርላንድ የዓለም አቀፍ ልማትና ዳያስፖራ ሚኒስትር ዴዔታ ሾን ፍሌሚንግ ናቸው፡፡ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቱ ሦስት ክፍሎች ያሉት ሲሆን፤ የመጀመሪያው 5 ሚሊየን ዩሮ ለሴፍቲ ኔት ፕሮግራም እንዲሁም 3 ሚሊየን ዩሮ በጤና ላይ ያተኮሩ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለመደገፍ እንደሚውል ተገልጽልል። እንዲሁም 400 ሺሕ ዩሮ ደግሞ ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ድጋፍ እንደሚውል በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ ከፊርማ ሥነ- ሥርዓቱ በኋላ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ባደረጉት ንግግር፤ አየር ላንድ ለኢትዮጵያን የልማት ሥራዎች ቀጣይነት እያደረገችው ላለው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡ ሦስቱም ስምምነቶች በመንግሥት…
Read More
በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የሚፈጸሙ ግድያዎች መቀጠላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የሚፈጸሙ ግድያዎች መቀጠላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል በቀጠለው ጦርነት ዙሪያ ያደረገውን የምርመራ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ኮሚሽኑ እንዳለው በአማራ ክልል ባለው ጦርነት የደረሱ ጉዳቶችን ለመመርመር መንግሥታዊ ኃላፊዎችን፣ በግጭቱ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን፣ የዐይን ምስክሮችን፣ ተጎጂዎችንና የተጎጂዎች ቤተሰቦችን በማነጋገር መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ማሰባባቡን ገልጿል፡፡ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በመንግስት የጸጽታ ሀይሎች እና በተለምዶ ፋኖ በመባል ከሚታወቀው አካል ጋር ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ ይህ ጦርነት በአንዳንድ አካባቢዎች በከባድ መሣሪያ እና አልፎ አልፎ በአየር/ድሮን ድብደባ ጭምር የታገዘ ነው ያለ ሲሆን በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በረኸት ወረዳ፣ መጥተህ ብላ ከተማ፣…
Read More
በአማራ እና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ 300 ዜጎች በታጣቂዎች ተገደሉ

በአማራ እና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ 300 ዜጎች በታጣቂዎች ተገደሉ

የኦሮሚያ እና አማራ ክልል የሚዋሰኑበት የሰሜን ሸዋ ዞን ስራ የሚገኙ ወረዳዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ ደራ የተሰኘው ወረዳ ደግሞ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃት የሚደርስበት አካባቢ ሲሆን በሶስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ 300 ንጹሃን ዜጎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል፡፡ ኦነግ ሸኔ ከሶስት ዓመት በፊት  በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ተፈርጆ መንግስት ይህን የሽብር ቡድን ለማጥፋት እርምጃ እየወሰድኩ ነው ቢልም ቡድኑ ጥቃት ማድረሱን ቀጥሏል፡፡ አንድ ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የደራ ወረዳ ነዋሪ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንዳሉት "በሦስት ሳምንታ ውስጥ ከ300 በላይ ንጹሐን በሸኔ ታጣቂዎች ተገድለዋል።" ያሉ ሲሆን፤ ይህ እርሳቸው ያላቸው ትክክለኛ መረጃ እንደሆነ በመግለጽ፤ የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችል እርግጠኛ መሆናቸውን…
Read More
በኦሮሚያ ክልል በጉንፋን መሳይ ወረርሽኝ በሽታ የ78 ሰዎች ህይወት አለፈ

በኦሮሚያ ክልል በጉንፋን መሳይ ወረርሽኝ በሽታ የ78 ሰዎች ህይወት አለፈ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ወረዳ በተቀሰቀሰ ጉንፋን መሳይ ወረርሽኝ በአንድ ቀበሌ ብቻ የ78 ሰዎች ህይወት አልፏል። የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ በበኩሉ የወረርሽኙን መከሰት አረጋግጦ አፋጣን ምላሽ ለመስጠት እየጣረ መሆኑን አስታውቋል። ወረርሽኙ ከምዕራብ ወለጋ በተጨማሪ ቄለም ወለጋ ውስጥ መከሰቱንም ዶይቼ ቬለ ከነዋሪዎች አረጋግዐጫለሁ ብሏል፡፡ በምዕራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ወረዳ የሌሊስቱ ሎጲ ቀበሌ ነዋሪ እንደሚሉት በአካባቢው መቋጫ የታጣለት የጸጥታ ችግር ነዋሪውን ለረሃብ እና የወረርሽኝ በሽታ አጋልጦ በርካቶችን ለህልፈት እየዳረገ ነው። “አሁን እኛ ጋ ከፍተኛ የምግብ እጦት ይስተዋላል፡፡ ይህም መነሻው ድርቅ አጋጥሞን አሊያም በፋጣሪ ቁጣ ሳይሆን ሰው በፈጠረው ግጭት ወጥቶ ማረስ አይደለም ወጥቶ መግባቱ ፈተና ሆኖ በመሆኑ ነው ብሏል፡፡ በኦሮሚያ ክልል…
Read More
ከፓስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ሙስና ፈጽመዋል የተባሉ 42 ተጠርጣሪዎች ታሰሩ

ከፓስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ሙስና ፈጽመዋል የተባሉ 42 ተጠርጣሪዎች ታሰሩ

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኞች ህዝብን ከማማረራቸው ባለፈ ለውጭ ሀገራት ዜጎች ፓስፖርት ሲሰጡ ነበርም ተብሏል፡፡ በሙስና ተጠርጥረው በፖሊስ ከታሰሩ ሰዎች መካከል የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተሩ ይገኙበታል፡፡ 42 የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኞች ባሳለፍነው ሰኞ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ የመንግሥት አስተዳደር ለውጥ ከተደረገ ጀምሮ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት ተቋም ውስጥ የተለያዩ ለውጦች (ሪፎርም) የተደረገ ቢሆንም፣ አንዳንድ የተቋሙ ሠራተኞች በድለላ ሥራ የተሰማሩ አካላት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይ ፓስፖርት ፈላጊ ኢትዮጵያዊያን መንገላታታቸውን ተከትሎ የተቋሙን አመራሮች ከስልጣን አግደው ነበር፡፡ ሰላማዊት ዳዊት ደግሞ…
Read More
ኢትዮጵያ ያቀረበችው የባህር በር ጥያቄ በጎረቤት ሀገራት ውድቅ ተደረገ

ኢትዮጵያ ያቀረበችው የባህር በር ጥያቄ በጎረቤት ሀገራት ውድቅ ተደረገ

ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አህመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የህዝቧን የመልማት ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት የባህር በር ያስፈልጋታል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ የጣላቁ ህዳሴ ግድብን ስትገነባ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ሀገራት ጠይቀዋል፣ እኛም የባህር በር እንዲኖረን መጠየቅ አለብን ሲሉም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል ያበሉ እንጂ ስለየትኛው የባህር በር ግን ስም አልጠቀሱም ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆኑት እና የባህር በር ያላቸው ኤርትራ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ ሲሆኑ ሶስቱም ሀገራት የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ አስቀድሞ መግለጫ ያወጣው የኤርትራ መንግስት ሲሆን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ባወጣው መግለጫ ሀገሪቱ ሀብቷን ለማንም አሳልፋ እንደማትሰጥ፣ እስካሁንም የተጀመረ ምንም…
Read More
የእብድ ውሻ በሽታ በየዓመቱ ከ2700 በላይ ኢትዮጵያዊያን እንደሚገድል ተገለጸ

የእብድ ውሻ በሽታ በየዓመቱ ከ2700 በላይ ኢትዮጵያዊያን እንደሚገድል ተገለጸ

የግብርና ሚንስቴር እንደገለጸው በኢትዮጵያ የእብድ ውሻ በሽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባበሳ እና ስጋት እየሆነ በመምጣቱ  በዓመት እስከ 2 ሺህ 7 መቶ የሚደርሱ ሰዎች ይሞታሉ። በሚኒስቴሩ የእንስሳት ጤናና ፐብሊክ ሄልዝ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር  ውብሸት ዘውዴ እንደተናገሩት ሁኔታው አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልል ከተሞች ትልቅ ስጋት ሆኗል፡፡ በከተሞች አካባቢ ባለቤት አልባ ውሾች በየመንገዱና በየጎዳናው የሚስተዋሉ በመሆናቸው  በርካታ ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ ተጠቂ እየሆኑ ነው ተብሏል። እድሜያቸው ከ15 አመት በታች የሆኑ ህጻናት በበሽታው በስፋት እንደሚጠቁም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። በሽታውን ለመከላከል እስከ 70 በመቶ የሚደርሱ ውሾች ቢከተቡ በሽታው ከውሻው ወደ ሰዎች እንዳይተላለፍ ማድረግ እንደሚቻልም ተገልጿል። አስቀድሞ በሽታው በሰዎች ህይወትና ደህንነት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል  ኢትዮጵያ…
Read More
ኢትዮጵያ ለታንዛኒያ ኤሌክትሪክ ሀይል እንደምትሽጥ ገለጸች

ኢትዮጵያ ለታንዛኒያ ኤሌክትሪክ ሀይል እንደምትሽጥ ገለጸች

የኤሌክትሪክ ኃይል በተያዘው ዓመት ከሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገራት ከተሸጠ የኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ 30 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በተያዘው በጀት ዓመት ሁለት ሺህ ከ993 በላይ ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት ይደረጋል፡፡ ለሦስት ጎረቤት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ለሱዳን፤ ኬንያ እና ጅቡቲ 2 ሺህ 993 ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት በማድረግ 182 ሚሊዮን ዶላር ወይም 10 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል ብለዋል፡፡ ለሀገር ውስጥ ደንበኞች በሚሸጥ የኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ 20 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት መታቀዱንም አቶ ሞገስ ተናግረዋል፡፡ ባሳለፍነው የ2015 በጀት ዓመት ከሀገር ውስጥ እና ለጎረቤት ሀገራት…
Read More
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ቻይና አመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ቻይና አመሩ

የቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ዓመታዊ ጉባኤ ከሁለት ቀናት በኋላ በቤጂንግ ይካሄዳል፡፡ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን መሪዎች በዚህ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ቤጂንግ በማምራት ላይ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዚሁ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ቻይና ማምራታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ ቻይና ለኢትዮጵያ ብድር ከሚሰጡ ሀገራት መካከል ዋነኛዋ ስትሆን በተለይም ለኤርፖርት ማስፋፊያ፣ ለመንገድ እና ለደረቅ ወደብ ልማት ግንባታዎች በቻይና ብድር ተገንብተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በጦርነት እና በኮሮና ቫይረስ መጎዳቱን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት የብድር ጫና ውስጥ በመግባቱ የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምለት በመጠየቅ ላይ ነው፡፡ ቻይና የኢትዮጵያን የብድር መክፈያ ጊዜ በአንድ ዓመት ማራዘሟ የተገለጸ ሲሆን ከዓለም ባንክ…
Read More
በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከፍተኛ ስጋት መኖሩን ተመድ አስታወቀ

በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከፍተኛ ስጋት መኖሩን ተመድ አስታወቀ

በኢትዮጵያ በፌደራል መንግሥት የጸጥታ ሀይሎች እና በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ውጊያ ምክንያት፤ የዘር ማጥፋት እና ተያያዠ አሰቃቂ ወንጀሎች እንዲፈጸሙ የሚያስችል ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካሪ ገለጹ። የድርጅቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል መከላከል ልዩ አማካሪ አሊስ ዋይሪሙ በኢትዮጵያ ስላለው ኹኔታ አስመልክተው ባወጡት መግለጫ፤ በትግራይ፣ አማራ፣ አፋር እና ኦሮሚያ ክልሎች እየተካሄዱ ባሉ ውጊያዎች ምክንያት በአገሪቱ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት እና ተያያዠ አሰቃቂ ወንጀሎች የመፈጸም ኹኔታዎች እንዲኖሩ ማድረጉን ጠቁመዋል። "በኢትዮጵያ እየተፈጸሙ ስላሉት ወንጀሎች የተመለከቱ የሚደርሱን ሪፖርቶች እጅግ የሚረብሹ ናቸው" ያሉት ልዩ አማካሪዋ፤ "በአፋጣኝ ኹኔታውን ለመከላከል እርምጃ ሊወሰድ ይገባል።" ብለዋል። አክለውም፤ "እየደረሱን ካሉ ሪፖርቶች መካከል የአንድ ቤተሰብ አባላት በሙሉ ግድያ እንደተፈጸመባቸው፣ ቤተሰቦች…
Read More
ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጎን እንድትቆም ተጠየቀች

ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጎን እንድትቆም ተጠየቀች

ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጎን እንድትቆም በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ጥሪ አቀረበ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ተቋማት፣ በሐማስ የተፈጸመውን ጥቃት እንዲያወግዙ፣ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ በሰጡት መግለጫ ጠይቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት እስከ አሁን ስለጥቃቱም ይኹን ስለ ግጭቱ በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም፡፡ ኾኖም፣ ኢትዮጵያ ገለልተኛ አቋም እንዳላትና ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ እንደምትፈልግ፣ በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ ትላንት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ ሃማስ በእስራኤል ላይ መጠነ ሰፊ  ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኙ ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያዉያን ሰለባ መሆናቸዉን በኢትዮጵያ እስራኤል ኤምባሲ  አስታዉቋል፡፡ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለሊ አደማሱ እንዳሉት በወቅታዊ የጉዳቱን መጠን አሁን ላይ መግለጽ ባይቻልም ከተጎጂዎች መካከል ግን ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያዉያን እንደሚኖሩ ተናግረዋል፡፡ በጥቃቱ ከ1200 በላይ እስራኤላዉያን መሞታቸዉን አምባሳደር አለሊ…
Read More
ኢትዮጵያ ከሱዳን ሽንኩርት ልታስመጣ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ ከሱዳን ሽንኩርት ልታስመጣ መሆኗን ገለጸች

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠመውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ የመሰረታዊ ምግብ አቅርቦቶች እጥረት አጋጥሟል፤፡ የምርት እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎም ህዝቡ በዋጋ ንረት እየተጎዳ እንደሆበነም ተገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በከተማዋ ያጋጠመውን የሽንኩርት እጥረት ለመፍታት ከሱዳን ለማምጣት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ ከበዓላቱ ጋር ተያይዞ የሽንኩርት ዋጋ ጭማሪ በማሳየቱ እና በየጊዜው በአትክልት ላይ  ለሚደረገው የዋጋ ጭማሪ መፍትሄ ተብለው እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መኖራቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ እንደተናገሩት በመደበኛ ገበያው ላይ ለተከሰተው  የዋጋ ንረት መፍትሄ ተብለው እየተሰሩ ያሉ ስራዎች  መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ በተለይ የእሁድ ገበያ ላይ ከሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ጋር በተያያዘ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን እና ሱዳንን ጨምሮ…
Read More
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሲቪል ሥራ በተያዘው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሲቪል ሥራ በተያዘው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ከሁለት ወራት የእረፍት ጊዜ በኋላ ተከፍቷል፡፡ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በምክር ቤቶቹ የመክፈቻ ንግግራቸው ላይ የመንግስትን የአንድ ዓመት የትኩረት መስኮች ይፋ አድርገዋል፡፡ ፕሬዝዳንቷ በንግግራቸው ላይ ያለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ ግድብ 4ኛ ዙር የውኃ ሙሌት መጠረናቀቁ ትልቁ ስኬት ነበር ብለዋል፡፡ 90 በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀው የህዳሴው ግድብ የሲቪል ምህንድስና ስራ ሙሉ ለሙሉ በዚህ ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል፡፡ ይህ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ብቻ የሚያመነጭ ግድብ ሳይሆን የቱሪዝምና የውሃ ሀብት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የሞራል ልዕልና ነው ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቷ አክለውም መንግስት በተያዘው ዓመት የሕግ የበላይነትን ማስከበር፣ የኑሮ ውድነትን መቀነስ፣ የስራ እድል ፈጠራ ፣ የምግብ ዋስትና እና መልካም አስተዳድር ልዩ ትኩረት…
Read More
ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውስጥ 817 ሺህ ተማሪዎች መውደቃቸው ተገለጸ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውስጥ 817 ሺህ ተማሪዎች መውደቃቸው ተገለጸ

1ሺህ 328 ትምህርት ቤቶች ደግሞ አንድም ተማሪ እንዳላሳለፉ ተገልጿል።በ2015 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ 845 ሺሕ 099 ተማሪዎች ውስጥ፤ 817 ሺሕ 838 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች የሆነ ውጤት ማምጣታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የ2015  የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ከአጠቃላይ 845 ሺሕ 099 ተፈታኞች ውስጥ 27 ሺሕ 267 ተማሪዎች ወይንም (ሦስት ነጥብ ኹለት በመቶ ብቻ) 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት አምጥተዋል። በተፈጥሮ ሳይንስ ከተፈተኑ 356 ሺሕ 878 ተማሪዎች ውስጥ 19 ሺሕ 017 ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ሲመጡ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከተፈተኑ 488 ሺሕ 221 ተማሪዎች ውስጥ 7…
Read More
በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያውያን መጎዳታቸው ተገለጸ

በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያውያን መጎዳታቸው ተገለጸ

ሃማስ በእስራኤል ላይ መጠነ ሰፊ  ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኙ ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያዉያን ሰለባ መሆናቸዉን በኢትዮጵያ እስራኤል ኤምባሲ  አስታዉቋል፡፡ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለሊ አደማሱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በወቅታዊ የጉዳቱን መጠን አሁን ላይ መግለጽ ባይቻልም ከተጎጂዎች መካከል ግን ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያዉያን እንደሚኖሩ ተናግረዋል፡፡ በጥቃቱ ከ700 በላይ እስራኤላዉያን መሞታቸዉን አምባሳደር አለሊ አስታዉቀዋል፡፡ በተጨማሪም ከ2 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዉ በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይ የእስራኤል ጦር ኃይል የሃማስን ጥቃት በመመከት  ጎን ለጎን የሞቱ ዜጎችን እየቀበረ እንደሚገኝ ኤምባሲዉ አስታዉቋል፡፡ ሃማስ የጀመረዉ ጥቃት በቀላሉ የሚታልፍ እንዳልሆነም አምባሳደር አለሊ ገልጸዋል፡፡ እስራኤል አንድ መቶ ሺህ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ ማሰመራቷንም አስታዉቃለች፡፡…
Read More
ቻይና በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ለመገንባት ተስማማች

ቻይና በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ለመገንባት ተስማማች

ይህ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ግንባታ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ይፈጃል ተብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የቻይናው ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የቴክኖሎጂ ልኅቀት ማዕከል ለመገንባት የውል ስምምነት ሠነድ ተፈራርመዋል፡፡ የልህቀት ማዕከል ግንባታው ኮተቤ በሚገኘው የተቋሙ ግቢ ውስጥ ይገነባል የተባለ ሲሆን ለፕሮጀክቱ 9 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ተመድቧል ተብሏል፡፡ ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሽፈራው ተሊላና የቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ኤክስኪዩቲቭ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ው ጁይ ናቸው፡፡ ማዕከሉ ሲጠናቀቅ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር የተጣጣመና ለደንበኞች የሚሰጠውን አገልግሎት አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና ዘመናዊ የሚያደርግ እንደሆነ አቶ ሽፈራው ገልጸዋል፡፡ ው ጁይን  በበኩላቸው የማዕከሉን ግንባታ በተያዘለት ጊዜ በጥራት  አጠናቅቀው እንደሚያስረክቡ አረጋግጠዋል፡፡ ማዕከሉ የኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ ሙያ የሰው ኃይል…
Read More
የሆቴል ባለቤቶች የባንክ ዕዳ መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ጠየቁ

የሆቴል ባለቤቶች የባንክ ዕዳ መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ጠየቁ

የኢትዮጵያ የሆቴል እና ቱሪዝም አሠሪዎች ፌዴሬሽን እንደገለጸው በኢትዮጵያ የሆቴል እና ቱሪዝም ስራ በየጊዜው እየተዳከመ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍትህ ወልደሰንበት ለቪኦኤ እንዳሉት የሆቴል እና ቱሪዝም ቢዝነስ በዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተዳክሞ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ወደ ቀድሞ አቋሙ ተመልሷል ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያም የሆቴል ኢንዱስትሪ ከኮሮና ቫይረስ ጉዳት እንዲያገግም ለመንግስት በቀረቡለት ምክረ ሀሳቦች መሰረት እርምጃ መውሰዱ ዘርፉን ከባሰ ጉዳት ታድጎታል ብለዋል። የኮቪድ ፕሮቶኮል በሚል ወደ ስራ የተተገበረው አሰራር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ስራ አቁመው የነበሩ ሆቴሎችን ወደ ስራ እንዲመለሱ ማድረጉን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። ይሁንና በኢትዮጵያ ግን በየጊዜው እየተዳከመ እና በርካታ የሆቴል ቢዝነስ ባለሀብቶች እና ባለሙያዎች ወደ ሌላ ቢዝነስ እየገቡ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡…
Read More
ኢትዮጵያ በእርዳታ ስርጭት ላለመሳተፍ መስማማቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በእርዳታ ስርጭት ላለመሳተፍ መስማማቷ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ካሳለፍነው ግንቦት ወር ጀምሮ የመጋዝን ስርቆት ተፈጽሞብናል በሚል እርዳታ መስጠት አቁመው ነበር፡፡ እርዳታ መቆሙን ተከትሎም ስደተኞች እና የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ረሀብን ጨምሮ ተረጂዎች ህይወታቸውን እስከማጣት መድረሳቸው በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ በእርዳታ እህል ስርቆቱ ላይ የፌደራል እና የክልል መንግስታት ባለስልጣናት እጃቸው እንዳለበት በወቅቱ በረድኤት ድርጅቶቹ በኩል ተገልጾም ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለተረጂዎች የተቀመጠን እህል ወደ ጎረቤት ሀገር ይላክ እንደነበርም የተገለጸ ሲሆን የፌደራል መንግስት በወቅቱ የቀረበበትን ክስ ውድቅ አድርጓል፡፡ የአሜሪካ የልማት ተራድዖ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ያቋረጠውን የምግብ እርዳታ ዳግም ለማስጀመር መወሰኑን አስታውቋል፡፡ እርዳታው የተጀመረው የኢትዮጵያ መንግስት ከእርዳታው ጋር በተያያዘ በስርጭቱ ላይ እጁን እንደማያስገባ ከተስማማ በኋላ…
Read More
የአሜሪካ የልማት ተራድዖ ድርጅት በኢትዮጵያ ያቋረጠውን የምግብ እርዳታ ዳግም አስጀመረ

የአሜሪካ የልማት ተራድዖ ድርጅት በኢትዮጵያ ያቋረጠውን የምግብ እርዳታ ዳግም አስጀመረ

እርዳታው የተጀመረው የኢትዮጵያ መንግስት ከእርዳታው ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ስምምነት እንደማይኖረው ከተስማማ በኋላ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) በኢትዮጵያ ያቋረጠውን የምግብ እርዳታ ለስደተኞች ብቻ መልሶ ለማስጀመር መወሰኑን አስታውቋል። ድርጅቱ የእርዳታ እህል አቅርቦቱን የሚጀምረው በኢትዮጵያ ለሚገኙ ለኹሉም የእርዳታ ፈላጊዎች ሳይሆን፤ በአገሪቱ ተጠልለው ለሚገኙ የጎረቤት አገራት ስደተኞች ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የረድኤት ድርጅቱ የኢትዮጵያ መንግሥት እና አጋሮቹ የስደተኞች የምግብ እርዳታ አቅርቦት መዋቅር ላይ ለውጦችን በማድረጋቸው እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱን የገለጸ ሲሆን፤ “የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሪቱ ለሚገኙ ስደተኞች የምግብ እርዳታን በማጓጓዝ፣ በማከማቸት እና በማከፋፈል ዙሪያ ምንም አይነት ተሳትፎ እንደማይኖረው ስምምነት ላይ በመደረሱ የእርዳታ እህል አቅርቦቱን ለመስጀመር መወሰኑን ተገልጿል፡፡ በዚህም በኢትዮጵያ…
Read More
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወጣት አፍሪካውያን መሪዎች ሽልማትን አሸነፉ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወጣት አፍሪካውያን መሪዎች ሽልማትን አሸነፉ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ በChoiseul100Africa በአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ ትልቅ ሚና ከሚጫወቱ 100 ወጣት አፍሪካዊ መሪዎች መካከል በአንደኛ ደረጃ ተመረጡ። "Choiseul 100 አፍሪካ" ልዩ የሆነ በሿዘል ኢንስቲትዩት የሚደረግ ጥናት ሲሆን አፍሪካን ወደ ከፍተኛ የኢኮኖሚ፣ የማህበረሰብ እና የባህል እድገት ደረጃ የማድረስ አላማ ያነገበና እድሜያቸው 40 እና ከዚያ በታች የሆኑትን 200 ወጣት የአፍሪካ መሪዎችን በመለየት እውቅና የሚሰጥ በፈረንሳይ የሚገኝ ተቋም ነው። ኩባንያው ሽልማቱን አስመልክቶ ባሰራጨው መግለጫ "...የሞባይል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን፣ የዲጂታል እና የፋይናንስ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ  ላከናወኗቸውናእና እያከናወንን ላለናቸው ስራዎችና ስለጥረታችን  የተሰጠ አበረታች እውቅና መሆኑን በመገንዘብ ታላቅ ኩራት ይሰማናል" ብሏል። ፍሬህይወት ታምሩ ከ2018 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ንብረት…
Read More
የአፍሪካ ከተማ ከንቲባዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

የአፍሪካ ከተማ ከንቲባዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

ከነገ ጀምሮ የአፍሪካ ከንቲባዎች የሊደርሺፕ ኢኒሼቲቭ መድረክ በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ ተገልጿል። የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ እናትአለም መለሰ እንዳሉት ከተማዋ ከነገ ጀምሮ ዓለም አቀፍ፣ አሕጉር አቀፍ እንዲሁም አገር አቀፍ ልዩ ልዩ መድረኮች እንደምታስተናግድ አመልክተዋል። ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የአፍሪካ ከንቲባዎች የሊደርሺፕ ኢኒሼቲቭ መድረክ፣ ከ28 እና 29 የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም የልህቀት ማዕከልን ለማቋቋም የሚረዳ ዓለም አቀፍ የምክክር መድረክ እንዲሁም ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም የሀገር አቀፍ መሪዎች የልምድ ልውውጥ መድረኮች ይካሄዳሉ ብለዋል፡፡ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም አበረታች ውጤት ማስመዝገብ የቻለ መሆኑን በመግለጽ አስተዳደሩ 9 ሺህ 500 ለሚሆኑ ሕጻናትና ወላጆች በከተማዋ አልሚ ምግብ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ መድረኮቹ በሁሉም…
Read More
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ድል አደረጉ

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ድል አደረጉ

የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ በላቲቪያ ሪያ በመደረግ ላይ ሲሆን የወንዶች እና የሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ፍጻሜውን አግኝቷል። በወንዶች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት ውድድሩን አጠናቀዋል። አትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት 12:59 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ደግሞ በ13:02 በመግባት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ኢትዮጵያዊው አትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ የወንዶች 5ኪ.ሜ ውድድርን ማሸነፍ የቻለ የመጀመሪያው አትሌት ሆኗል። በሴቶች ተመሳሳይ ርቀት ውድድር ኬንያዊያኑ አትሌት ቺቤት አንደኛ እንዲሁም ናሬንጉሩክ ሁለተኛ ሆና ስታጠናቅቅ ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች እጅጋየሁ ታዬ እና መዲና ኢሳ ደግሞ ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። በሌላ የ1 ማይል ርቀት ውድድር ደግሞ አትሌት ድርቤ ወልተጂ ኬንያዊቷን የ 1500ሜ…
Read More
ሶስተኛው የህዳሴው ግድብ ድርድር በካይሮ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ሶስተኛው የህዳሴው ግድብ ድርድር በካይሮ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ በሱዳን ለተከሰተው ጦርነት እልባት ለመፈለግ በሚል በካይሮ በተካሄደው የጎረቤት ሀገራት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድርን ለማስቀጠል መስማማታቸው ተገልጾ ነበር፡፡ በዚህ ስምምነት መሰረት ከሶስት ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የግድቡ ተደራዳሪ የቴክኒክ ባለሙያዎች በግብጽ ካይሮ ተገናኝተው ተወያይተዋል። እንዲሁም ሁለተኛው ዙር የቴክኒክ ባለሙያዎች ውይይት ደግሞ ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የግድቡ ተደራዳሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ዲፕሎማቶች የተሳተፉበት ይህ ውይይት ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱም ሀገራት በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ የግብጽ ውሃ እና መስኖ ሚኒስትር ሀኒ ስዌለም እንዳሉት በአዲስ አበባ የተካሄደው ድርድር…
Read More
ስድስት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በአበረታች መድሀኒት ምክንያት ለዓመታት ከውድድሮች ታገዱ

ስድስት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በአበረታች መድሀኒት ምክንያት ለዓመታት ከውድድሮች ታገዱ

የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በተጠረጠሩ አትሌቶች ላይ ጊዜያዊ እገዳ በመጣል ጉዳዩን ሲያጣራ መቆየቱን አስታውቋል። እገዳ የተላለፈባቸው አይሌቶች አትሌት ሹሜ  ጣፋ ደስታ እና  አትሌት መንግስቱ በቀለ ተዴቻ  የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግ በመጠቀም የህግ ጥሰት የፈፀሙ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብላል። በዚህም መሠረት የረጅም ርቀት ሯጭ የሆነዉ አትሌት  ሹሜ ጣፋ ደስታ 5-methylhexan-2-amine የተባለውን የተከለከለ ንጥረ-ነገር ተጠቅሞ በፈፀመው  የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት በውድድሩ ያስመዘገበው ውጤት እንዲሰረዝ እና  እ.ኤ.አ ከግንቦት 25/2023  ጀምሮ ለአራት (4) አመታት በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ  የቅጣት ውሳኔ እንደተላለፈበት ተገልጿል። በተመሳሳይ መልኩ አትሌት መንግስቱ በቀለ ተዴቻ ቻይና አገር ውስጥ በነበረው ውድድር ላይ Erythropoietin (EPO) የተባለዉን የተከለከለ አበረታች ቅመም ተጠቅሞ በመገኘቱ የፀረ-…
Read More
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እየተባባሰ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳሳሰበው ገለጸ

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እየተባባሰ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳሳሰበው ገለጸ

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እየተባባሳ ነው ያለው ወንጀልና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳስጨነቀው ተናግሯል። የህብረቱ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፍ ቦሬል የኢትዮጵያ መንግስት አፋጣን እርምጃ መውሰድ አለበት ብለዋል። ፍትህና ተጠያቂነት የህብረቱና የኢትዮጵያ ግንኙነት ቀስ እያለ ወደ መደበኛነት ለሚመጣው ግንኙነት ሁኔታዎች ናቸውም ሲሉ ሀሳባቸውን በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ገልጸዋል። ከሰሞኑን በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ የቀረበ ሲሆን፤ ሀገሪቱ ከፍተኛ ክስ ቀርቦባታል። በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የኢትዮጵያ መሪማሪ ሪፖርቱን አቅርቧል። የመርማሪ ቡድኑ ባለሞያ የሆኑት መሀመድ ቻንዴ ኦቶማን ባለፈው ዓመት ለተመድ የሰብዓዊ ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሁኔታ ከገለጽን ወዲህ ሰብዓዊ መብት በሀገሪቱ በእጅጉ ተባብሶ ቀጥሏል ብለዋል። በትግራይ ክልል…
Read More
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የሶስትዮሽ ድርድር በአዲስ አበባ ተጀመረ

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የሶስትዮሽ ድርድር በአዲስ አበባ ተጀመረ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይ ግብጽ በሱዳን መረጋጋት ዙሪያ ባዘጋጀችው የጎረቤት ሀገራት የመሪዎች መድረክ ላይ በተገኙበት ወቅት ከግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር በግድቡ ዙሪያ መምከራቸው ይታወሳል፡፡ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ መወያየታቸው ሲገለጽ የግድቡ ውሀ አሞላል ዙሪያ ተወያይተው እስከ መስከረም ወር ድረስ ተቋርጦ የነበረውን የሶስትዮሽ ውይይት ለማስጀመር ተስማምተው ነበር፡፡ በዚህ ስምምነት መሰረት ከሁለት ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የግድቡ ተደራዳሪ የቴክኒክ ባለሙያዎች በግብጽ ካይሮ ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡ ሁለተኛው የሶስትዮሽ ውይይትም ዛሬ በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የግድቡ ተደራዳሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት በሁለት ተርባይኖቹ ሀይል ማመንጨት የጀመረው የሕዳሴው ግድብ…
Read More
ብሪታንያ ከመቅደላ የዘረፈቻቸውን ቅርሶች ለኢትዮጵያ አስረከበች

ብሪታንያ ከመቅደላ የዘረፈቻቸውን ቅርሶች ለኢትዮጵያ አስረከበች

ከመቅደላ ተዘርፈው የተወሰዱ የተለያዩ የኢትዮጵያ ቅርሶች በለንደን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተመለሱ በ1868 በአጼ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት በብሪታንያ ተዘርፈው የተወሰዱ የኢትዮጵያ ቅርሶች መመለሳቸውን በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡ ከተመለሱት ቅርሶች መካከል በ1868 ዓ.ም ከመቅደላ የተዘረፈ የመድሃኒያለም ታቦት፣ የልኡል አለማየሁ የጸጉር ዘለላ፣ ከብር የተሰሩና በነሃስ የተለበጡ ሦስት ዋንጫዎች እንዲሁም በዘመኑ ጦርነት ላይ የዋለ የጦር ጋሻ እንደሚገኙበት ገልጿል፡፡ ለንደን በሚገኘው የአቴናየም ክለብ በተካሄደው የቅርሶቹ ርክክብ ሥነ ስርዓት ላይ፤ በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልኡካን ቡድን፣ የብሄራዊ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ተወካይ፣ የብሪታኒያ ፓርላማ አባላት፣ ቅርሶቹን ለማሰመለስ የተባበሩ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይም አምባሳደር ተፈሪ መለሰ፤ የተመለሱት የተለያዩ…
Read More
በአማራ ክልል አራት ሚሊዮን ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት አለመመለሳቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል አራት ሚሊዮን ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት አለመመለሳቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ለ2016 የትምህርት ዘመን 3 ነጥብ 9 ሚሊዮን ገደማ ተማሪዎች እስካሁን አልተመዘገቡም ተባለ በአማራ ክልል ለ2016 የትምህርት ዘመን ይመዘገባሉ ተብሎ ከተያዘው ከ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች መካከል እስከ  ሰኞ መስከረም 07/2016 ድረስ የተመዘገቡት ተማሪዎች ቁጥር 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብቻ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጌታቸው ቢያዝን፤ ለ2016 የትምህርት ዘመን ከነሐሴ 23/2015 ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የተማሪዎች ምዝገባ እስከ ሰኞ ድረስ የተመዘገቡት ተማሪዎች 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። የተማሪዎችን የምዝገባ ጊዜ እስከ ሚቀጥለው ሳምንት ድረስ ነው ያሉት ኃላፊው “በተያዘው ዓመት ከ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ በእቅድ ተይዞ…
Read More
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ የታሰሩ ሰዎች ህይወት በተስቦ በሽታ ማለፉ ተረጋገጠ

በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ የታሰሩ ሰዎች ህይወት በተስቦ በሽታ ማለፉ ተረጋገጠ

190 እስረኞች ታመው ህክምና ሲወስዱ ሶስት ሰዎች ደግሞ በጽኑ ህክምና ክትትል ውስጥ መሆነቸውን ኢሰመኮ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ወይም ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳድር ስር ባለ ሲዳሞ አዋሽ የታሰሩ ሰዎችን አስመልክቶ ያደረገውን ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ኮሚሽኑ ነሐሴ 24 እንዲሁም በጳጉሜን 2 እና 3 ቀን 2015 ዓ.ም. በዚህ ማቆያ ማእከል/ቦታ ባደረገው ጉብኝት እንዲሁም፣ በማቆያ ማእከሉ የሚገኙ ሰዎችን እና የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮን ጨምሮ የሚመለከታቸውን የመንግሥት የጸጥታ አካላት በማነጋገር ክትትል አካሂጃለሁ ብሏል። በተጨማሪም የማቆያ ማእከሉ አስተባባሪዎች እና ጥበቃ ሲያደርጉ የነበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትን፣ በቦታው የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ የሕክምና ባለሞያዎችን እና ተጨማሪ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኝ የነበረውን የጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ኃላፊዎችን እና ባለሞያዎችን በማነጋገር…
Read More
ተመድ ኢትዮጵያ ወደ ሀገር አቀፍ ግጭት እያመራች ነዉ ሲል አስጠነቀቀ

ተመድ ኢትዮጵያ ወደ ሀገር አቀፍ ግጭት እያመራች ነዉ ሲል አስጠነቀቀ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ኢትዮጵያ ወደ ሀገር አቀፍ ግጭት እያመራች ነዉ ሲል አሳዉቋል። በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ያለዉም ግጭት ተበራክቷል ያለው ተመድ የግጭቶች መበራከት ኢትዮጵያን ወደ ሀገር አቀፍ መጠነ ሰፊ ግጭት ሊወስዳት ይችላል ሲልም አስጠንቅቋል። ከዚህ በተጨማሪም በአማራ ክልል ያለዉን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት ፤ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የጅምላ እስር እና እንግልት እየተፈጸመ እንደሆነም አስታውቋል። ድርጅቱ በመግለጫው አክሎም በክልሉ ፤ በመንግስት ቢያንስ አንድ ጊዜ የሰዉ አልባ አዉሮፕላን ጥቃት መፈጸሙን የደረሱኝ ሪፖርቶች ያመለክታሉ ሲልም ጠቅሷል። በአማራ ክልል በርከታ ከተሞችም ከሲቪል አስተዳደር ዉጪ በመሆን በወታደራዊ ስርዓት ስር ወድቀዋል ተብሏል። በአማራ ክልል የተፈጠረውን ጦርነት ተከይሎ ካሳለፍነው ሀምሌ ወር ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን ተከትሎ…
Read More
በአማራ ክልል ንጹሀን ዜጎች ከፍርድ ውጪ እየተገደሉ መሆኑን ኢሰመኮ ገለጸ

በአማራ ክልል ንጹሀን ዜጎች ከፍርድ ውጪ እየተገደሉ መሆኑን ኢሰመኮ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሚያዝያ ወር 2015 ጀምሮ በአማራ ክልል የሚታየውን የጸጥታ ችግር እንዳሉ አስታውቋል። ኮሚሽኑ እንዳለው በክልሉ የነበረው የጸጥታ ችግሩ ወደ ትጥቅ ግጭት ማምራቱን ተከትሎ የንጹሀን ዜጎች ግድያ እና እንግልት ቀጥሏል ብሏል። በተለይም ከነሐሴ 19 እስከ ነሐሴ 30/2015 ድረስ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ንጹሃን መሞታቸውን እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ኢሰመኮ በመግለጫው አስታውቋል። "በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማ፣ በሰሜን ጎጃም ዞን አዴትና መራዊ፣ በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረ ታቦር፣ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ደልጊ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ፣ ሸዋ ሮቢት እና አንጾኪያ ከተሞች እና በአካባቢዎቻቸው በሚገኙ አንዳንድ የገጠር ቀበሌዎች በግጭቱ በርካታ ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል ተብላል። እንዲሁም ለአካል ጉዳት እና የንብረት…
Read More
ዩኔስኮ የኢትዮጵያን ሁለት ቅርሶች በዓለም ቅርስነት መዘገበ

ዩኔስኮ የኢትዮጵያን ሁለት ቅርሶች በዓለም ቅርስነት መዘገበ

የባሌ ተራሮች እና የጌድኦ መልክዓምድር በዩኔስኮ ተመዝግበዋል። ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቅርሶቿን ብዛት ወደ 11 ከፍ በማድረግ ከአፍሪካ በአንደኝነት ተቀምጣለች። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅትወይም ዩኔስኮ 45ኛ ጉባኤውን በሳውዲ አረቢያ ሪያድ እያካሄደ ይገኛል። በደቡብ ኢትዮጵያ ጌዴኦ ዞን የሚገኘው የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር እና የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የዓለም ቅርስ ሆነው መመዝገቡ ተገልጻል። ዩኔስኮ በድረገጹ እንዳስታወቀው የጌድኦ ባህላዊ መልከዓ ምድር እና የብርቅዬ የዱር እንስሳት መገኛ የሆነው የባሌ ብሔራዊ 10ኛ እና 11ኛ ቅርስ ሆነው መመዝገባቸውን ለዓለም አብስሯል። ኢትዮጵያ በአጠቃላይ 11 ቅርሶችን በዩኔስኮ መዝገብ ስር በዓለም ቅርስነት ያስመዘገበች ሲሆን ከአህጉሪቱ ደቡብ አፍሪካን በመብለጥ በአንደኝነት ትመራለች። ደቡብ አፍሪካ 10 ቅርሶችን ስታስመዘግብ ሞሮኮ ከደቡብ አፍሪካ…
Read More
ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ የፋው ምርት የሆኑ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ አቀረበ

ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ የፋው ምርት የሆኑ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ አቀረበ

የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ ገበያዎች በማምጣት የሚታወቀው ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ አሁን ደግሞ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ማስመጣቱን ገልጿል። ኩባንያው የቻይናው ፋው ሰራሽ የሆኑ የተለያዩ መጠን የመጫን አቅም ያላቸው አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከባድ እቃዎችን ሙጫን እሚችሉ የጭነት ተሽከርካሪዎችን አስመጥቷል። ፈርስት አውቶሞቲቭ ዎርክስ ወይም ፋው በመባል የሚታወቀው የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ ዋና መቀመጫውን ቻይና በማድረግ ከፈረንጆቹ 1950ዎቹ ጀምሮ በማምረት ላይ ይገኛል። ድርጅቱ በ2021 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎችን ለዓለም በመሸጥ ቀዳሚ የዓለማችን ኩባንያ እንደሆነ ተገልጿል። ይህ የቻይና ኩባንያ ከኢትዮጵያው ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ጋር አብሮ መስራቱን የገለጸ ሲሆን እስከ 20 ቶን እቃ የመጫን አቅም ያላቸው ተሽኩርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረቡን አስታውቋል። ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች…
Read More
የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ከ200 ሄክታር በላይ መሬት ደን ወደመ

የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ከ200 ሄክታር በላይ መሬት ደን ወደመ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የሚገኘው የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ለእርሻ ኢንቨስትመንት በመሰጠቱ ከ200 ሄክታር በላይ የፓርኩ መሬት ደን ሙሉ ለሙሉ መውደሙን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የብሔራዊ ፓርኮች አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አዳነ ጸጋዬ፤ የባቢሌን የዝሆኖች መጠለያ ፓርክ በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን በኩል ለእርሻ ኢንቨስትመንት ተሰጥቶ ፓርኩ እየታረሰ በመሆኑ፣ በፓርኩ የሚገኙ ዝሆኖች ለአደጋ ተጋልጠዋል ብለዋል፡፡ የባቢሌን የዝሆኖች መጠለያ በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች ድንበር ላይ የሚገኝ ሲሆን "በኦሮሚያ ክልል በኩል ያለው የፓርኩ ክፍል ለኢንቨስትመንት በመሰጠቱ አሁንም ድረስ እየታረሰ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። የፓርኩ መሬት ለኢንቨስትመንት የተሰጠው ፓርኮችን ለመጠበቅና ለማስተዳደር ኃላፊነት የተሰጠው የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን…
Read More
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የ104 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የ104 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ

የአፍሪካ ልማት ባንክ በምስራቅ ኢትዮጵያ የሃይል አቅርቦትን ለማሻሻል የሚያግዝ የ104 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ ማጽደቁን ገልጿል። የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ያጸደቀው የገንዘብ ድጋፍ 52 ሚሊዮን ዶላሩ ከአፍሪካ ልማት ፈንድ የተገኘ መሆኑም ተመላክቷል። ቀሪው የገንዘብ ድጋፍ ደግሞ የባንኩ የብድር አጋር ከሆነው በኮሪያ-አፍሪካ የኢነርጂ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ስምምነት ከኮሪያ የኢኮኖሚ ልማት ትብብር ፈንድ የተገኘ እንደሆነ ተገልጿል። የባንኩ የኃይል ሥርዓት ልማት ዳይሬክተር ባቺ ባልዴህ፤ ፕሮጀክቱ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ያለውን የኃይል ቋት አቅም በማሳደግ ታዳሽና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦትን የሚያሳድግ ነው ብለዋል። መንግሥት በምሥራቅ ኢትዮጵያ የሚያደርጋቸውን የኃይል አቅርቦት ጥረቶች የሚያግዝ ሲሆን፤ አርብቶ አደሮች፣ አነስተኛ ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮችና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል። ፕሮጀክቱ 157 ኪሎ ሜትር እርዝማኔ…
Read More
የታላቁ ህዳሴ ግድብ አምስት ተርባይኖች በቅርቡ ሀይል ማመንጨት እንደሚጀምሩ ተገለጸ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ አምስት ተርባይኖች በቅርቡ ሀይል ማመንጨት እንደሚጀምሩ ተገለጸ

በ2016 በሕዳሴው ግድብ አምስት ተጨማሪ ዩኒቶችን ሥራ ለማስጀመር እየተሠራ መሆኑን፤ የታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ አስታውቀዋል፡፡ የሕዳሴ ግድቡ አራተኛ ዙር የውኃ ሙሌት መጠናቀቁን ተከትሎ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የሙሌቱ መጠናቀቅ በይፋ ተበስሯል፡፡ በሥፍራው ለተገኙ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማብራሪያ የሰጡት የታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ፤ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 93 በመቶ መጠናቀቁን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ግድቡ፤ ግራ፣ ቀኝ እና መካከለኛ አካል እንዳለው የተናገሩት ኢንጂነር ክፍሌ፤ ግራና ቀኙ የግድቡ ክፍል ከ635 እስከ 645 ደረጃ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ የግራና ቀኙን ክፍል ለማጠናቀቅ ከዘጠኝ እስከ አሥር ሜትር ድረስ ብቻ እንደሚያስፈልግም አስታውቀዋል፡፡…
Read More
ጋዜጠኛ የኋላሸት ዘሪሁን መታሰሩ ተገለጸ

ጋዜጠኛ የኋላሸት ዘሪሁን መታሰሩ ተገለጸ

የትርታ ኤፍ  ኤም መስራች ጋዜጠኛ የኋላሸት ዘሪሁን በፌደራል ፖሊሶች ተይዞ መወሰዱን ባለቤቱ ገልፃለች። ጋዜጠኛ የኋላሸት ዘሪሁን ዛሬ ምሳ ሰዓት ላይ ባልዳራስ ኮንዶሚኒየም ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በፌደራል ፖሊስ አባላት ተይዞ  ሜክሲኮ የቀድሞው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ወደሚገኘው ጊዜያዊ ማቆያ ቦታ መወሰዱን ባለቤቷ ገልፃለች ። ባለቤቱ የታሰረበት ቦታ ሄዳ የጠየቀች ሲሆን በምን ምክንያት እንደታሰረ እንዳላወቀና ለጥያቄም እንዳልቀረበ አሳውቋታል ። ጋዜጠኛ የኋላሸት ትኩረቱን በኪነ ጥበባዊ ጉዳዮች ላይ ያደረገው ኪነ ብስራት የተሰኘ የሬድዮ ሾው ለዓመታት በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 በማቅረብ ይታወቃል። ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ጥበቃ ቡድን ወይም ሲፒጂ ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች እስር መቀጠሉን እና የታሰሩት እንዲፈቱ ማሳሰቡ ይታወሳል።
Read More
የፌዴራል ቤቶች ኮርፓሬሽን ለዲያስፓራ ኢትዮጵያውያን ቤት መሸጥ ሊጀምር መሆኑን ገለጸ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፓሬሽን ለዲያስፓራ ኢትዮጵያውያን ቤት መሸጥ ሊጀምር መሆኑን ገለጸ

ባለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ ሀይል እና እቅድ ወደ ስራ መግባቱን የገለጸው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሃገር ውስጥ ካለው ነዋሪ ባሻገር በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን ኘሮጀክት ለመጀመር ዝግጅት እያደረኩ ነው ብሏል። ስለ ኘሮጀክቱ እና ስለተቋሙ ገለፃ ለማድረግም በኮርፓሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ረሻድ ከማል የተመራ ልዑክ ወደ ብሪታንያ በማምራት በዚያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የማህበረሰብ አመራሮች ጋር ተወያይቷል። በውይይቱ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውንን ተጠቃሚ ለማድረግ በአዲስ መልክ ያቀደውን የቤት ልማት ፕሮጀክት ስኬታማ እንዲሆን ከዲያስፖራው ማህበረሰብ ተጨማሪ ሀሳበችንና ተሞክሮዎችን መሰብሰቡ ተገልጻል። ከዚሁ ጎን ለጎን በዋና ስራ አስፈፃሚው የሚመራው የልዑካን ቡድኑ በለንደንና አካባቢው በሚገኙ ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት…
Read More
የሕዳሴው ግድብ አራተኛ ዙር የውሀ ሙሌት ተጠናቀቀ

የሕዳሴው ግድብ አራተኛ ዙር የውሀ ሙሌት ተጠናቀቀ

የግድቡ አራተኛ እና ና የመጨረሻ ሙሌት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  "የሕዳሴው ግድብን አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ሳበስር በታላቅ ደስታ ነው፤  ኢትዮጵያውያን ተባብረን በመሥራታችን ፈጣሪ ረድቶናል። " በማለት የግድቡ የመጨረሻ ሙሌት መጠናቀቁን አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በጸሎታቸው በስራው ውስጥ የተሳተፋችሁ ሁሉ  እንኳን ደስ አላችሁ፤ ይህ ኅብረታችን በሌሎች ጉዳዮቻችንም ሊደገም ይገባዋል" ብለዋል። ከ12 ዓመት በፊት የተጀመረው የታላቂ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ ግንባታው 91 በመቶ ደርሷል ተብሏብ። ኢትዮጵያዊያን በሚያዋጡት ገንዘብ እነ በመንግስት ወጪ እየተገነባ ያለው ይህ ግድብ በ5ሺህ 200 ሜጋ ዋት ሀይል በማመንጨት ከአፍሪካ ትልቁ ፕሮጀክት ነው። የህዳሴው…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም በመላው አዲስ አበባ የ5G ኔትወርክ አገልግሎቱን ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም በመላው አዲስ አበባ የ5G ኔትወርክ አገልግሎቱን ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ (5G) የሞባይል አገልግሎትን በአዲስ አበባ በወዳጅነት አደባባይ በተካሄደ መርሃ ግብር በይፋ አስጀምሯል። በመርሃ ግብሩም ተቋሙ ከዚህ ቀደም በቅድመ ገበያ ሙከራ ደረጃ በአዲስ አባባ እና አዳማ ከተሞች አስጀምሮት የነበረውን የ5G የሞባይል አገልግሎት፤ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ በ145 ጣቢያዎች ማስጀመሩን አብስሯል። ይህ የ5G የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት እስከ 10 ጊጋ ባይት በሰከንድ የሚደርስ ፍጥነት እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፤ ዳታ የማስተላለፍ መዘግየትን እጅግ በላቀ ኹኔታ በመቀነስ ወደ 1 ሚሊ ሰከንድ ያደርሳል ተብላል። የ5G አገልግሎት በተለይም በተመሳሳይ ወቅት መከናወን የሚፈልጉ እንደ የማምረቻ ፋብሪካዎች፣ ግብርና፣ ሕክምና ለመሳሰሉ ዘርፎች የላቀ ፋይዳ እንዳለውም ተገልጿል። የ5G አገልግሎት ሥራ ላይ መዋል የማህበረሰቡን ሕይወት የሚያቀሉ ዲጂታል መፍትሄዎችን በቀላሉ…
Read More
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ አራዘመች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ አራዘመች

አሜሪካ ከሁለት ዓመት በፊት የተቀሰቃሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የአሜሪካንን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ይጎዳል በሚል ነበር ጦርነቱ እንዲቆም ጫና ስታደርግ የቆየችው፡፡ ይህ ጦርነት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ምስራቅ አፍሪካን ይጎዳል የምትለው አሜሪካ ጦርነቱ እንዲቆም የተለያዩ ጫናዎችን ያደረገች ሲሆን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈጽሟል በሚል የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች፡፡ በዋሸንግተን ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል በኢትዮጵያ ላይ ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ማዕቀብ የሚባል ሲሆን በፈረንጆቹ መስከረም 2021 ላይ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ማዕቀብ ተጥሏል፡፡ ይህ ማዕቀብ ከአንድ ሳምንት በኋላ የሚጠናቀቅ ቢሆንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማዕቀቡ ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲራዘም መፈረማቸውን አስታውቀዋል፡፡ አሜሪካ ማዕቀቡን ለአንድ ዓመት ያራዘመችው በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሁንም ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለምስራቅ አፍሪካ እና ለአሜሪካ የውጭ ጉዳዮች ፖሊሲ…
Read More
ኢትዮጵያ የመዳረሻ ቪዛን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መስጠት እንደምትጀምር ገለጸች

ኢትዮጵያ የመዳረሻ ቪዛን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መስጠት እንደምትጀምር ገለጸች

ኢትዮጵያ የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት ለውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ከሁለት ዓመት በፊት መስጠት የጀመረች ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ እና በሌሎች ምክንያቶች ተቋርጦ ቆይቷል፡፡ የጎብኚዎችን ቁጥር ከፍ እንደሚያደርግ የሚገለጸው የመዳረሻ ቮዛ አገልግሎት ከመስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ኢትዮጵያ 190 ሺህ ፓስፖርት ከውጪ ሀገር በማሳተም ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቷን ገልጻለች፡፡ የኢምግሬሽን እና ዝግጅት አገልግሎት ከሙስና ጋር በተያያዘ ሁሉንም ከፍተኛ አመራሮች ከሀላፊነት በማንሳት አዲስ አመራር ከአንድ ወር በፊት ተሾሞለታል። ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይ ተቋሙን በሀላፊነት እንዲመሩ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተሾሙት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሯ በመግለጫቸው 300 ሺህ ዜጎች ፓስፖርት ለማግኘት ተመዝግበው እየተጠባበቁ መሆኑን…
Read More
በአማራ ክልል በአንድ ቀን ብቻ ከ49 በላይ ንጹሃን ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል በአንድ ቀን ብቻ ከ49 በላይ ንጹሃን ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ከትናንት በስቲያ ሰኞ ነሐሴ 29 ቀን 2015 የመንግሥት የጸጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ እንዲሁም በድሮን ጥቃት ከ49 በላይ ንጹሃን መገደላቸውን እናት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ፓርቲው በመግለጫው ሰኞ ነሐሴ 29 ቀን 2015 በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ ከተማ የመንግሥት ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ 29 ንጹሃን ዜጎች በየመኖሪያ ቤታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ብሏል፡፡ "ከሟቾች ውስጥም ሕጻናት፣ ወጣቶች እና አረጋውያን እንዳሉበት ከመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠናል።" ያለው ፓርቲው  "በተመሳሳይ ነሐሴ 29 ቀን 2015 በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ፣ ሞሰባ ሽሜ አቦ ቀበሌ አዳራሽ ጎጥ ላይ መንግሥት በፈጸመው የድሮን ጥቃት ከ11 በላይ ንጹሐን ዜጎች ተጨፍጭፈዋል።" ብሏል። በዚሁ ቀን በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ…
Read More
ሸራተን ሆቴል የድምጻዊ ሬማ አዲስ ዓመት ዋዜማ ኮንሰርትን ሰረዘ

ሸራተን ሆቴል የድምጻዊ ሬማ አዲስ ዓመት ዋዜማ ኮንሰርትን ሰረዘ

የ2016 አዲስ ዓመትን አስመልክቶ በሸራተን አዲስ ሆቴል የሙዚቃ ድግስ መዘጋጀቱን የሚገልጹ ማስታወቂያዎች ሲተላለፉ ሰንብተዋል፡፡ በዚህ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ድምጻዊያን የማስታወቂያው አንድ አካል የነበሩ ሲሆን ናይጀሪያዊው ዲቫይን ኢኩቦር ወይም በቅጽል ስሙ ሪማ በመባል የሚታወቀው ድምጻዊ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ድምጻዊያን ጋር በመድረኩ ላይ እንደሚዘፍኑ ተገልጾም ነበር፡፡ ይሁንና ድምጻዊ ሬማ ከክርስትና ሀይማኖት ጋር በተያያዘ ያልተገባ ነገር አድርጓል በሚል ይህን የአዲስ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ድግስ ላይ ላለመገኘት በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ ቅስቀሳ ሲደረግ ሰንብቷል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንም በይፋ የቤተ ክርስቲያን በዓላት ሲደርሱ ከሥርዓቷ እና ከአስተምሮዋ ውጪ በ ሆነ መልኩ የተለያዩ አካላት የዳንኪራ ጥሪ በማዘጋጀት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አግባብነት የሌለው መሆኑን…
Read More
አርቲስቶች እና ስፖንሰሮች የአዲስ ዓመት ዋዜማ ሙዚቃ ኮንሰርቶችን ሰረዙ

አርቲስቶች እና ስፖንሰሮች የአዲስ ዓመት ዋዜማ ሙዚቃ ኮንሰርቶችን ሰረዙ

ኢትዮጵያ የ2016 አዲስ ዓመትን ከአምስት ቀናት በኋላ የምታከብር ሲሆን በበዓሉ ዋዜማ የሙዚቃ ኮንሰርቶች ተዘጋጅተዋል። የአዲስ ዓመት ዋዜማ ዕለት ከሚዘጋጁ የሙዚቃ ድግሶች መካከል በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል የተዘጋጀው አንዱ ነበር። በዚህ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ የውጭ ሀገራት እና ኢትዮጵያዊያን ሙዚቀኞች ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ማስታወቂያዎች በሚዲያዎች በመተላለፍ ላይ ናቸው። ናይጀሪያዊው ዲቫይን ኢኩቦር ወይም በቅጽል ስሙ ሪማ በመባል የሚታወቀው ድምጻዊ ፣ ከሀገር ውስጥ ደግሞ ልጅ ሚካኤል፣ ኩኩ ሰብስቤ እና ሌሎችን ድምጻዊያን በዚህ የአዲስ ዓመት ኮንሰርት ላይ የሙዚቃ ስራቸውን እንደሚያቀርቡ ተገልጾ ነበር። ይሁንና ድምጻዊ ሬማ የክርስትና እምነት ላይ ከዚህ በፊት አሹፏል በሚል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች በዚህ ኮንሰርት ላይ እንዳይገኙ መልዕክት ማስተላለፏን ተከትሎ በርካቶች…
Read More
በኢትዮጵያ የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተም ወንጀል የተጠረጠሩ ቻይናዊያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኢትዮጵያ የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተም ወንጀል የተጠረጠሩ ቻይናዊያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

በርካታ መጠን ያላቸው የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተምና ጥቁር ገበያን በማስፋፋት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ። ተጠርጣሪዎቹ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል። በኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ቻይናዊያን ባለሀብቶች ንብረት የሆነው ፀሃይ ሪል ስቴት በዚህ ወንጀል እጁ እንዳለበት ፖሊስ ገልጿል። ፖሊስ የሪል ኢስቴቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ኪያ ዦንግን ጨምሮ ዘጠኝ የውጭ ሀገራት ዜጎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። ፖሊስ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች ውስጥ ሶስት ኢትዮጵውያን ተጠርጣሪዎችም ተይዘዋል። ፖሊስ ሁሉንም ተጠርጣሪዎችን ፍርድ ቤት አቅርቦ ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድረግ የ14 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ፖሊስ…
Read More
የመጀመሪያው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በናይሮቢ መካሄድ ጀመረ

የመጀመሪያው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በናይሮቢ መካሄድ ጀመረ

ከድርቅ ጀምሮ እስከ በርሃማነት በተደቀነባት የአፍሪካ አህጉር የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ የሚመክር የአየር ንብረት ጉባኤ በናይሮቢ መካሄድ ጀምሯል። በኬንያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት ይካሄዳልብተብሏል። በጉባኤው ላይ ከ20 ቡላይ የአፍሪካ መሪዎች፣ የበርካታ ሀገራት ሚንስትሮች፣ ልዑኮችና የአየር ንብረት ተሟጋቾች ይሳተፋሉ። በአህጉሪቱ እንደ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ኬንያ ባሉ ሀገራት ከ40 ዓመታት ወዲህ የከፋ የተባለ ድርቅ ተከስቷል። በዚህም በአፍሪካ ቀንድ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ዋስትና ቀውስ የተከሰተ ሲሆን፤ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ እንስሳት ሞተዋል። የአፍሪካ ልማት ባንክ እንደሚለው እየጨመረ ከመጣው የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በሚከሰቱ አደጋዎች ሀገራት በየዓመቱ ከሰባት እስከ 15 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብታቸውን ያጣሉ። የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ካልተቻለ…
Read More
እስራኤል ሁከት የፈጠሩ ኤርትራዊያንን ለማባረር ወሰነች

እስራኤል ሁከት የፈጠሩ ኤርትራዊያንን ለማባረር ወሰነች

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በቴላቪቭ በሃይለኛ ግጭት ውስጥ የተሳተፉ ኤርትራውያን በአስቸኳይ እንዲባረሩ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። የሀገሪቱን አፍሪካውያን ስደተኞች በሙሉ ለማስወገድ እቅድ ማውጣታቸውን አስታውቀዋል። ይህንን አስተያየት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት በደቡባዊ ቴል አቪቭ በኤርትራ ተቀናቃኝ ቡድኖች መካከል በነበረ ደም አፋሳሽ ግጭት በርካታ ሰዎች ላይ ጉዳት ከደረሰ  ከአንድ ቀን በኋላ ነበር። ኔታንያሁ የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ በትላንትናው እለት በተጠራው ልዩ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ “በሁከት ፈጣሪዎች ላይ ከባድ እርምጃዎችን እንፈልጋለን ፣ የተሳተፉትን ወዲያውኑ ወደ መጡበት መመለስ እንፈልጋለን” ብለዋል ። ሚኒስትሮቹ “ሌሎች ህገወጥ ሰርጎ ገቦችን ለማስወገድ” እቅድ እንዲያቀርቡላቸው የጠየቁ ሲሆን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ስደተኞቹን ለቀው እንዲወጡ ለማስገደድ የታቀዱ አንዳንድ እርምጃዎችን መተላለፉን በንግግራቸው አስታውቀዋል። በአለም አቀፍ ህግ…
Read More
በአሶሳ ዞን የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ

በአሶሳ ዞን የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ

በአሶሳ ዞን በመንጌ ወረዳ ሸጎል ቀበሌ  አሚር ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ገልጿል። ነሃሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 7 ሰዓት ገደማ በአካባቢው ለወርቅ ማዕድን ማውጣት ስራ ጉድጓድ በመቆፈር ላይ ከነበሩ ዘጠኝ ግለሰቦች መካከል የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የመንጌ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር አሳድቅ አብዱልፈታህ ተናግረዋል። ቀሪ ሶስት ሰዎች ደግሞ በአደጋው ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባለ ሲሆን ተጎጂዎች በመንጌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል ብለዋል። በወቅቱ ግለሰቦችን በህይወት ለመታደግ በሰውና በመኪና የታገዘ ጥረት ቢደረግም ቦታው አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሳ መታደግ እንዳልተቻለ ተናግረዋል።…
Read More
በትግራይ ክልል የኤች አይ ቪ ቫይረስ ሥርጭት አስደንጋጭ መሆኑ ተገለጸ

በትግራይ ክልል የኤች አይ ቪ ቫይረስ ሥርጭት አስደንጋጭ መሆኑ ተገለጸ

በትግራይ ክልል ከ100 ሰዎች ውስጥ 10ሩ የኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ አለባቸው ተብሏል፡፡ በትግራይ ክልል ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ የኤች አይ ቪ ቫይረስ ሥርጭት በአስደንጋጭ ሁኔታ ጨምሯል የተባለ ሲሆን ስርጭቱ በ10 ነጥብ 5 በመቶ መጨመሩን የክልሉ ጤና ቢሮ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል፡፡ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ርእየ ኢሳያስ በሰሜኑ ጦርነት ወቅትም ሆነ ከጦርነቱ በኋላ ልቅ በሆኑ ወሲባዊ ጥቃቶች ምክንያት የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡ በዚህም በክልል በሚገኙ 37 የጤና ተቋማት በተደረገ የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ፤ እስከ ጦርነቱ ጅማሮ 1 ነጥብ 8 በመቶ የነበረው የቫይረሱ ስርጭት አሁን ላይ 10 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱን አስረድተዋል፡፡ በክልሉ ከ120 ሺሕ በላይ…
Read More
ኢትዮጵያ በአማራ ክልል ያለውን ሁኔታ ለተመድ የሰብዓዊ ድርጅቶች ማብራሪያ ሰጠች

ኢትዮጵያ በአማራ ክልል ያለውን ሁኔታ ለተመድ የሰብዓዊ ድርጅቶች ማብራሪያ ሰጠች

ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ላደረጉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ተቋማትተወካዮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ተሰጠ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካና ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስጋኑ አርጋ፤ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ በተለይም በአማራ ክልል ስላለው የሰብዓዊ ሁኔታ ለተወካዮቹ ገለጻ አድርገዋል። በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት አጠቃላይ የሰብአዊ ሁኔታን ለማሻሻል እና ከእርዳታ ድርጅቶች ጋር በመሆን ምግብን ጨምሮ የእርዳታ አቅርቦትን ለማፋጠን ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው የአማራ ክልል ወደ ቀድሞ ሁኔታው እየተመለሰ መሆኑን በማንሳት፤ በአብዛኛዎቹ ቦታዎች አዲስ የክልል አስተዳደር ተቋቁሞ ተቋርጠው የነበሩ መሠረታዊ አገልግሎቶችም ዳግም መጀመራቸውን አስረድተዋል። አምባሳደር ምስጋኑ አያይዘውም፤ አፋጣኝ የሰብአዊ እርዳታ በሚያስፈልጉባቸው አካባቢዎች ያለውን ኹኔታ በተለይም የምግብ አቅርቦትን የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች በፍጥነት እንዲከታተሉ…
Read More
የሞስኮ ትምህርት ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት አማርኛ እና ስዋህሊ ቋንቋን ማስተማር እንደሚጀምሩ ገለጹ

የሞስኮ ትምህርት ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት አማርኛ እና ስዋህሊ ቋንቋን ማስተማር እንደሚጀምሩ ገለጹ

ሩሲያ ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ከመስከረም ወር ጀምሮ አማርኛ እና ስህዋህሊ ቋንቋዎችን በሞስኮ በሚገኙ በአራት ትምህርተ ቤቶች ማስተማር እንደምትጀምር ገልጻ ነበር። በዚህም መሰረት ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መስከረም በሞስኮ የሚገኙ ትምህ ቤቶች የአፍሪካ ቋንቋዎችን ማስተማር ይጀመራል ሲል የሞስኮ ትምህርት እና ሳይንስ ክፍል አስታውቋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ 1517 የተሰኘው የፔዳጎጂ ትምህርት ቤት ስዋህሊ ቋንቋን ሁለተኛው የውጭ ቋንቋ አድርጎ ያስተምራል ተብሏል። እንዲሁም 1522 የተሰኘው ትምህርት ቤት ደግሞ አማርኛ ቋንቋን እንደሚያስተምር ተገልጿል። ሩሲያ የአፍሪካ እና ሞስኮን ወዳጅነት ለማጠናከር በሳምንት አንድ ወይም ሁለት የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ለአፍሪካ ቋንቋዎች ማስተማሪያ እንዲውሉ ይደረጋል ብላለች። ሩሲያ በቀጣይም በምዕራብ አፍሪካ ሰፊ ተናጋሪ ያለው ዩርባ ቋንቋን ማስተማር…
Read More
ኢትዮጵያ የሲንጋፖር ኩባንያን ወደ ሀገሯ እንዲመጣ ጋበዘች

ኢትዮጵያ የሲንጋፖር ኩባንያን ወደ ሀገሯ እንዲመጣ ጋበዘች

የሲንጋፖር የወደብ ባለስልጣን በኢትዮጵያ በሎጀስቲክስ ኢንቨስትመንት እንዲሰማራ ጥሪ ቀረበ ዓለም አቀፍ የእስያ ኩባንያዎችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ እና ኢንቨስት እንዲያደርጉ ለማሳመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሲንጋፖርን በመጎብኘት ላይ ናቸው፡፡ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ጋር በመሆን ሲንጋፖር የሚገኘውን የሲንጋፖር የወደብ ባለስልጣን ጎብኝተዋል። ሁለቱ የኢንቨስትመንት አመራሮች ከሲንጋፖር ወደብ ባለስልጣን ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱም የሲንጋፖር የወደብ ባለስልጣን በኢትዮጵያ በሎጀስቲክስ ኢንቨስትመንት እንዲሰማራ ጠይቀዋል። የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ፣ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ከፍተኛ ፍላጎት ገልፀው ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት የሚሰማራበትንና ልምድ የሚያካፍልበት መንገድ እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በበኩላቸው ፈጣን…
Read More
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትምህርት ሚኒስትሩን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር አድርገው ሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹመቱን የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲቋቋም በ1294/23 የራስ ገዝ አዋጅ በረቀቀው መሠረት እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 23ኛው መደበኛ ስብሰባ የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን ተከትሎ ነው። በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ እንዲፈጽሙ እንዲሁም የሰው ሀብት እና የፋይናንስ አስተዳደር ነፃነትን በማረጋገጥ በሀገሪቱ የማኅበራዊ እና…
Read More
በደብረማርቆስ ከተማ በአራት ቀናት ውስጥ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በደብረማርቆስ ከተማ በአራት ቀናት ውስጥ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ደብረማረቆስ ከአርብ ነሐሴ 19/2015 እስከ ሰኞ ነሐሴ 22/2015 ድረስ በመከላከያ ሠራዊትና እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ ውጊያ፤ ከመቶ በላይ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ ተገልጿል። ሥማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የደብረማርቆስ ስፔሻላይዝድ ሆሰፒታል ሐኪም በከተማዋ ቦሌ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ከመቶ በላይ ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል ። የሟቾቹ አስክሬን ከኹለት ቀን በላይ ሳይነሳ መንገድ ላይ ወድቆ መታየቱንም ነዋሪዎች እና ሀኪሞች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። "በቦታው የወደቁትን አስከሬኖች፤ አንዳንድ ሰዎች ሙስሊሙንም ክርስቲያኑንም ኹሉንም እያነሱ ማሪያም ቤተክርስቲያን ውስጥ እና በአካባቢ ቀብረዋቸዋል፡፡ ነገር ግን ሰኞ ድረስ ያልተቀበሩም ነበሩ።" ሲሉ ነዋሪዎቹ ጠቅሰዋል፡፡ በከተማው ለሦስት ቀናት በተደረገው ውጊያ ቆስለው ወደ ሆስፒታል የሄዱ ጥቂት ሰዎች ቢኖሩም፤ የትራንሰፖርት እና…
Read More
ዳሸን ባንክ ከሁለት የአውሮፓ ባንኮች 40 ሚሊዮን ዶላር ብድር አገኘ

ዳሸን ባንክ ከሁለት የአውሮፓ ባንኮች 40 ሚሊዮን ዶላር ብድር አገኘ

ዳሸን ባንክ ከእንግሊዝ እና ኔዘርላንድ ባንኮች 40 ሚሊዮን ዶላር ብድር አገኘ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት (ቢ አይ አይ) እና የኔዘርላንድ የሥራ ፈጠራና ልማት ባንክ የሆነው (ኤፍ ኤም ኦ) እያንዳንዳቸው 20 ሚሊየን ዶላር በድምሩ 40 ሚሊየን ዶላር ብድር ለዳሸን ባንክ ማቅረባቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ የብድር አቅርቦቱ ኢትዮጵያ ለውጪ ገበያ የምታቀርበውን የግብርና ምርት ለማሳደግ እና በእጅጉ አስፈላጊ የሆነውን የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት ለማሻሻል እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡ ቢ አይ አይ እና ኤፍኤምኦ ለዳሸን ባንክ ያቀረቡት ገንዘብ በኢትዮጵያ 80 በመቶ የህብረተሰብ ክፍል በተሰማራበት፣ ለጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት 39 በመቶ ድርሻ ላለው እና ለወጪ ንግዱ 90 በመቶ አስተዋጽኦ ለሚያበረክተው የግብርና ዘርፍ ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖረውም ታምኖበታል፡፡ የቀረበው ብድር ባንኩ…
Read More
ኢትዮጵያ በቡዳፔስት ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ላይ ስድስተኛ ሆና አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ በቡዳፔስት ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ላይ ስድስተኛ ሆና አጠናቀቀች

ወደ ቡዳፔስት አቅንቶ የነበረው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ወደ አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ከነሀሴ 13 ቀን እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም በሀንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ሲካሄድ የቆየው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ተጠናቋል። በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 195 የዓለማችን ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን ሜዳሊያ ማግኘት የቻሉ ሀገራት ግን 46 ብቻ ናቸው ተብሏል። ከማጣሪያ ውድድሮች ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ 2 ሺህ 100 አትሌቶች በተሳፉበት በዚህ ውድድር ላይ 50 አትሌቶች የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው ሲያስገኙ 48 የብር እንዲሁም 50 የነሀስ ሜዳሊያዎችን ተወዳዳሪዎቹ ለሀገራቸው አስገኝተዋል፡፡ ውድድሩን 400 ሺህ ተመልካቾች በአካል ስታዲየም ገብተው ታድመውታል የተባለ ሲሆን ሀንጋሪ ደማቅ እና አይረሴ ውድድር ማዘጋጀቷ ተገልጿል። በዓለም አቀፉ…
Read More
የዓለም ባንክ ለኢትዮ-ጅቡቲ መንገድ 730 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ

የዓለም ባንክ ለኢትዮ-ጅቡቲ መንገድ 730 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ

የገንዘብ ሚኒስቴርና የዓለም ባንክ ለአፍሪካ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ኮሪደር ፕሮጀክት (በኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር ፕሮጀክት) የ730 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት መፈራረማቸው ይፋ ተደርጓል። ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያን 90 በመቶ የባህር ንግድን የሚይዘው ስትራቴጂካዊው ከአዲስ አበባ-ጅቡቲ ኮሪደር ጋር በተሳሰረ መልኩ የኢትዮጵያን የሎጅስቲክስና የትስስር አቅም እንደሚያጎለብት ተጠቁሟል። በስምምነቱ መሰረት ለሜኦሶ-ድሬዳዋ መንገድ ግንባታ የፋይናንስ ድጋፍ የሚደረግ ሲሆን፤ ግንባታው የትራንስፖርት አቅምና ብቃት የሚጨምር መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። መንገዱ በሚገነባባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች የጤና፣ ውሃና ትምህርት አገልግሎት ተደራሽነት ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶች ድጋፍ እንደሚደረግም ተመላክቷል። ፕሮጀክቱ የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሺዬቲቭ አካልና የቀጣናዊ ትብብር ማዕቀፍ እንደሆነ ያመለከተው ሚኒስቴሩ፤ ማዕቀፉ አካባቢውን በመሰረተ ልማት የማስተሳሰር ፋይዳም እንዳለው ተጠቅሷል። ስምምነቱን የተፈራረሙትም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ…
Read More
ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበሙን በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ ተከለከለ

ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበሙን በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ ተከለከለ

በኦሮሚኛ እና አማርኛ የሙዚቃ ስራዎቹ የሚታወቀው ድምፃዊ አቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም ለቋል። "እንዳባቴ እወድሻለሁ" በሚል ለገበያ ያቀረበው ይህ የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም በገበያ ላይ በመሸጥ ላይ መሆኑን አስታውቋል። ድምጻዊው በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳለው ምክኒያቱ ባልተገለጸበት ሁኔታ አልበሜ በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ መከልከሉን ገልጿል። "እንደ አባቴ እወድሻለሁ" የተሰኘዉ አልበም በማህበራዊ መገናኛ መንገዶች ላይ በይፋ የተለቀቀ ቢሆንም በአዲስ አበባ ሲዲዉን የሚያዞሩ ወጣቶች መሸጥ እንዳይችሉ በፖሊስ መከልከላቸውንም ጠቅሷል። በትናንትናው እለት ሲዲዉን ለመሸጥ የወጡ ወጣቶች ከተከለከሉ በኋላም ድምፃዊዉ ክልከላዉ ለምን እንደተላለፈ አላዉቅም ብሏል። ድምፃዊዉ "ሁሉም ሰዉ ለኔ እኩል ነዉ ፤ በእኩልነት በአብሮነት ፣ በአንድነት የማምን ሰዉ ነኝ ያንን ሀሳብ ነዉ በአልበሜ ላይ ለማንጸባረቅ የሞከርኩት" ብሏል።…
Read More
አዲስ አበባ ቀጣዩን የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር እንድታካሂድ ተመረጠች

አዲስ አበባ ቀጣዩን የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር እንድታካሂድ ተመረጠች

የህዳሴው ግድብ የቴክኒክ ባለሙያዎች የሶስትዮሽ ድርድር ባለፉት ሁለት ቀናት በግብጽ ካይሮ መካሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪው አባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በተለያዩ ምክንያቶች መቋረጡ ይታወሳል። ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የሶስትዮሽ ድርድር  ሲያካሂዱ ቆይተዋል። በሱዳን እና በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋት ለሶስትዮሽ ድርድር አለመቀጠል እና የግብጽ ተለዋዋጭ አቋም ማሳየት ለድርድሩ አለመሳካት ዋነኞቹ ምክንያቶች ነበሩ። ከአንድ ወር በፊት በግብጽ ካይሮ በሱዳን ለተከሰተው ጦርነት እልባት ለመፈለግ በሚል በተካሄደው የጎረቤት ሀገራት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እግረ መንገዳቸውን ከፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ  አልሲሲ ጋር መክረዋል። ሁለቱ መሪዎች ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከልም…
Read More
የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በግብጽ ተጀመረ

የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በግብጽ ተጀመረ

ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪው አባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በተለያዩ ምክንያቶች መቋረጡ ይታወሳል። በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ሲካሄድ የቆየው ይህ የሶስትዮሽ ድርድር በኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳን መካከል ሲካሄድ ቆይቷል። በሱዳን እና በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋት ለሶስትዮሽ ድርድር አለመቀጠል እና የግብጽ ተለዋዋጭ አቋም ማሳየት ለድርድሩ አለመሳካት ዋነኞቹ ምክንያቶች ነበሩ። ከአንድ ወር በፊት በግብጽ ካይሮ በሱዳን ለተከሰተውን ጦርነት እልባት ለመፈለግ በሚል በተካሄደው የጎረቤት ሀገራት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እግረ መንገዳቸውን ከፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር መክረዋል። ሁለቱ መሪዎች ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከልም የህዳሴው ግድብ ጉዳይ ዋነኛው ሲሆን በሶስት ወራት ውስጥ ዳግም ድርድር…
Read More
ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን የወርቅና የብር ሜዳሊያ አገኘች

ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን የወርቅና የብር ሜዳሊያ አገኘች

በሀንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ሰባተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬ በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌት አማኔ በሪሶ አትሌት ጎቲቶም ገብረ ስላሴ የወርቅ እና ብር ሜዳሊያዎችን አግኝታለች፡፡ ሞሮካዊቷ አትሌት ፋጥማ ጋርዳዲ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳሊያ ልታገኝባቸው የምትችልባቸው ቀሪ ውድድሮች ያሉ ሲሆን አሁን ላይ በሁለት ወርቅ፣ በአራት ብር እና በሁለት ነሀስ በደምሩ በስምንት ሜዳሊያዎች ከዓለም በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ አሜሪካ በስምንት የወርቅ፣ ስፔን በአራት ወርቅ እንዲሁም ጃማይካ በሶስት የወርቅ ሜዳሊያ ከአንደኛ እስከ ሶተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬ እና ነገ በሚካሄዱ የወንዶች ማራቶን፣ በሴቶች እና ወንዶች አምስት ሺህ ሜትር ውድድሮች ላይ የምትሳተፍ…
Read More
በኢትዮጵያ ከ4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ ከ4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገለጸ

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም (IOM) ከባለፈው ሕዳር እስከ ሰኔ ወር ድረስ በ3 ሺሕ 300 መጠለያ ጣቢያዎች ሰበሰብኩት ባለው መረጃ፤ በኢትዮጵያ ከ11 ክልሎች ከ4 ነጥብ 38 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል ብሏል፡፡ ከነዚህ ተፈናቃዮች 66 በመቶ የሚሆኑት በግጭት ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ቀሪዎቹ በድርቅ እና በማህበራዊ ችግሮች ምክንያት መፈናቀላቸው ተገልጿል፡፡ሶማሌ ክልል በድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መገኛ መሆኑ ሲገለጽ፤ ትግራይ፣ አማራ ፣ኦሮሚያ እና አፋር ክልሎች በግጭት የተፈናቀሉ ዜጎች ያሉባቸው አካባቢዎች ናቸው ተብሏል፡፡ በተመሳሳይ በ10 ክልሎች ተፈናቃዮችን ለመመለስ በተደረገ ጥናት 3 ነጥብ 24 ሚሊዮን ተፈናቃዮች ወደ ቦታቸው መመለስ ይችላሉ በሚል መለየታቸውም ተገልጿል፡፡ተቋሙ አክሎም በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተፈናቃዮች የተመለሱባቸው…
Read More
ከኬንያ ላሙ ወደብ ሞያሌ- አዲስ አበባ የባቡር መስመር ሊገነባ እንደሆነ ተገለጸ

ከኬንያ ላሙ ወደብ ሞያሌ- አዲስ አበባ የባቡር መስመር ሊገነባ እንደሆነ ተገለጸ

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛትን የባቡር መስመር በ14 ቢሊዮን ዶላር ልትዘረጋ መሆኑን አስታውቃለች፡፡ ኬንያ የምትዘረጋው ይህ ፈጣን የባቡር መስመር በኤሌክትሪክ የሚሰራ ሲሆን፤ መነሻውን ከህንድ ውቅያኖስ ላሙ ወደብ በማድረግ ኢትዮጵያን እና ደቡብ ሱዳንን እንደሚያገናኝ ብሉምበርግ ዘግቧል። በዓይነቱ ልዩ ነው የተባለው ይህ የባቡር መስመር በፈረንጆቹ 2025 ሥራ እንደሚጀመር እና 3 ሺሕ ከሎ ሜትር እንደሚረዝም ታውቋል፡፡ የባቡር መስመሩ መነሻውን ከህንድ ውቅያኖስ አድርጎ፣ በኬንያዋ ማዕከላዊ ከተማ ኦሲዮሎን በኩል፣ ናይሮቢን እና አዲስ አበባን በማገናኘት የመጨረሻም መዳረሻውን ደቡብ ሱዳን ጁባ እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡ ይህ ፈጣን የባቡር መስመር “ኢትዮጵያ በአሰብ እና ምጽዋ እንዲሁም ጅቡቲ ወደቦች ላይ ያላትን ጥገኝነት የሚቀንስ ነው” የተባለ ሲሆን፤ ሌሎች በርካታ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች…
Read More
አሸዋ ቴክኖሎጂ  ተጨማሪ የአክስዮን ሽያጭ ጀመረ

አሸዋ ቴክኖሎጂ ተጨማሪ የአክስዮን ሽያጭ ጀመረ

አክስዮን ገዢዎች  በ500 ሺ ብር  አክስዮን በስድስት አመት ውስጥ ከስድስት ሚልየን ብር በላይ እንደሚያገኙ ተገልጿል። አሸዋ ቴክኖሎጂ በሰው ሃብት አስተዳደር ፣ በሂሳብ መዝገብ አያያዝ  እና የቢዝነስ  ክንውኖችን ማቀላጠፊያ ሶፍትዌሮችን በማበልጸግ ወደ ስራ የገባ አገር በቀል ድርጅት ነው። የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዳንኤል በቀለ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ግለሰቦች እና ድርጅቶች አክስዮን  ገዝተው ትርፍ የሚጋሩበትን ለሶስት ወራት የሚቆይ የአክስዮን ሽያጭ መጀመሩን ተናግረዋል። የአንድ አክስዮን ዋጋ 2 ሺህ 500 ብር እየሸጠ ያለው አሸዋ ቴክኖሎጂ  ትንሹ አክስዮን 500 ሺህ ብር ሲሆን  ትልቁ አክስዮን ደግሞ 100 ሚልየን ብር እንደሆነ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተጠቅሷል። የአክስዮን ገዢዎች የገዙትን አክስዮን መጠን 50 በመቶውን ቅድሚያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል የተባለ ሲሆን ቀሪ የአክስዮን ድርሻዎችን ደግሞ…
Read More
የብሪክስ መሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ መካሄድ ጀመረ

የብሪክስ መሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ መካሄድ ጀመረ

ከ15 ዓመት በፊት በብራዚል፣ ሩሲያ፣ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የተመሰረተው ብሪክስ የዘንድሮውን ጉባኤ በጆሀንስበርግ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ፒንግ፣ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ተገኝተዋል፡፡ ሩሲያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጊ ላቭሮቭ የተወከለች ሲሆን ፕሬዝዳንት ፑቲን በበይነ መረብ ታግዘው ንግግር አድርገዋል፡፡ የጉባአው አዘጋጅ ደቡብ አፍሪካ ለ60 ሀገራት ግብዣ ያቀረቡ ሲሆን ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በጉባኤው ላይ እንዲገኙ መጋበዛቸውን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ40 በላይ የዓለማችን ሀገራት የብሪክስ አባል ለመሆን ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ሳውዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ የተባበሩት አረብ አምሬት፣ ግብጽ፣ አልጀሪያ እና ሌሎችም ሀገራት ብሪክስን ለመቀላቀል በይፋ…
Read More
በአማራ ክልል ከ50 በላይ ወረዳዎች ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ከ50 በላይ ወረዳዎች ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ባለዉ ጦርነት ምክንያት ክልሉ ከመንግሥት መዋቅር ውጪ ናቸው የተባሉ ወረዳዎች ይፋ ሆነዋል። መንግስት ከቁጥጥር ውጪ የሆኑ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳድር የባንክ ሂሳቦችን እንዳይንቀሳቀሱ እገዳ ጥሏል። ከሰሜን ሸዋ ወረዳዎች ውስጥ ሚዳ ወረሞ፣ መርሃቤቴ፣ አለም ከተማ ፣እነዋሪ፣ መንዝ ቀያ፣ መንዝ ላሎ፣ መንዝ፣ ማማ፣ መንዝ ሞላሌ ከተማ አስተዳድር፣ መንዝ ጌራ፣ ሲያደብር እና ዋዩ፣ እንሳሮ ፣ሞረትና ጅሩ ወረዳዎች ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ናቸው ተብሏል። ከሰሜን ወሎ ወረዳዎች ደግሞ ግዳን ወረዳ ፣እስታይሽ፣ ቡግና እና ሙጃ ወረዳዎች እንዲሁም ከደቡብ ወሎ ደፍሞ ወግዲ ወረዳ፣ ከለላ፣ መካነሰላም ፣ቦረና ፣ አማራ ሳይንት እና ዋድላ ደላንታ ወረዳዎች ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ናቸው የተባለ ሲሆን የመንግስት ተቋማት የባንክ ሂሳብ እንዳይንቀሳቀሱ እገዳ…
Read More
አፍሪካ ህብረት ኒጀርን ከአባልነት አገደ

አፍሪካ ህብረት ኒጀርን ከአባልነት አገደ

የአፍሪካ ህብረት ከአንድ ወር በፊት መፈንቅለ መንግስት ያደረገችው ኒጀርን ከአባልነት አግዷል። በጀነራል ቲያኒ የሚመራው የኒጀር ጦር በምርጫ ስልጣን በያዙት የኒጀር ፕሬዝዳንት ባዙም ላይ በመፈንቅለ መንግሥት ስልጣን ተቆጣጥሯል። ይህን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት ኒጀርን ከአባልነት ላልተወሰነ ጊዜ ከስልጣን ማንሳቱን አስታውቋል። የመፈንቅለ መንግስቱ መሪዎች በምርጫ ስልጣን የያዙትን ፕሬዚዳንት መሃመድ ባዙምን ከእስር እንዲፈቱ እና ወደ ቤታቸው እንዲመልሱም ህብረቱ ጥሪ አቅርቧል። የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት የምዕራብ አፍሪካ ህብረት (ኢኮዋስ) ለወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ተጠባባቂ ሃይል ለማንቀሳቀስ ያሳለፈውን ውሳኔ መመልከቱንም ሬውተርስ ዘግቧል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እንደዚህ አይነት ሃይል ማሰማራት ያለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና የደህንነት አንድምታ እንዲገመግም ጠይቋል። የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) ዲሞክራሲን…
Read More
ኢትዮጵያ ከሀገር ውስጥ ጎብኚዎች 61 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከሀገር ውስጥ ጎብኚዎች 61 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ

በ2015 በጀት ዓመት ከሀገር ውስጥ ጎብኚዎች 61 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽንና የሕዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ አለማየሁ ጌታቸው እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ በተለይም አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን ከማልማት እንዲሁም ነባሮችን ከማደስ እና ከመጠገን አንጻር ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተዋል፡፡ የጮቄ ተራራ እና ወንጪ የኢኮ ቱሪዝም መዳረሻዎች በዓለም ቱሪዝም ድርጅት እውቅና እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉንም አስታውሰዋል። በተለያዩ አካባቢዎች ተጨማሪ የኢኮ ቱሪዝም መዳረሻ ሊሆኑ የሚችሉ ቦታዎችን በጥናት የመለየት እና መረጃ የማሰባሰብ ስራ መከናወኑን ጠቅሰዋል፡፡ በበጀት ዓመቱም በርካታ ቁጥር ካላቸው የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች 61 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ነው አቶ አለማየሁ…
Read More
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፕላን ጥገና ፈቃድ ሰጠች

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፕላን ጥገና ፈቃድ ሰጠች

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፕላን ጥገና ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ ባለስልጣኑ ዋን ኤም. አር.ኦ (One M.R.O) ለተሰኘ የግል ተቋም በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነውን አውሮፕላን ጥገና ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ በ2013 ዓ.ም የቢዝነስ ፈቃድ አውጥቶ የተቋቋመው ዋን ኤም. አር.ኦ የጥገና ፈቃድ ሰርትፊኬት ለማግኘት የበቃው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያዘጋጃቸውን አምስት ዓለም አቀፍ መስፈርቶች አሟልቷል በሚል ነው፡፡ ለተቋሙ የተሰጠው የጥገና ፈቃድ ቦይነግ 737 ክላሲክና ቦይንግ 737 ኔክስት ጄኔሬሽን የተባሉ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን መጠገን ያስችለዋል ተብሏል፡፡ ዋን ኤም.አር ኦ. የጥራት ማረጋገጫና ደህንነት ማናጀር አቶ አንዱአለም ስለሺ ፤ ድርጅታቸው በአሁን ሰዓት ናይጄሪያ ላይ መሰረት አድርጎ በምዕራብ አፍሪካ ለሚገኙ የግል ኦፐሬተሮች የጥገና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ድርጅታቸው በቀጣይም በኢትዮጵያ…
Read More
የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ አተረፈ

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ አተረፈ

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በተያዘው ዓመት ውስጥ 42 ቢሊየን ብር ገቢ አግኝቻለሁ ያለ ሲሆን ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቋል። ተቋሙ በ2016 በጀት ዓመት ደግሞ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን አመልክቷል። የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) እንዳሉት ኮቪድ 19፣ የዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት፣ የሀገር ውስጥ ፀጥታ ችግርና ሌሎች ችግሮች በድርጅቱ ስራዎች ላይ ተፅዕኖ ነበራቸው። በበጀት ዓመቱ ከውጭ ወደ አገር ውስጥ ከተጓጓዘው 7 ነጥብ 4 ሚሊየን ቶን እቃ ውስጥ 34 በመቶውን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ማጓጓዙን ገልጸዋል። በመርከብ የወጪ ጭነትና ጥቅል ጭነት አገልግሎት በእቅዱ ልክ መፈፀሙን ጠቅሰው፣ በብረት ማጓጓዝ ረገድ ግን ዝቅተኛ…
Read More
እስራኤል የኢትዮጵያን ሁኔታ የሚከታተል የጦር መሪ ሾመች

እስራኤል የኢትዮጵያን ሁኔታ የሚከታተል የጦር መሪ ሾመች

ብርጋዴር ጀነራል ሀርል ክንፎ በኢትዮጵያ ያሉ ቤተ እስራኤላዊያንን ጉዳይ እንዲከታተሉ መሾማቸው ተገልጿል። እንደ ጀሩሳሌም ፖስት ዘገባ ከሆነ የእስራኤል መንግሥት በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላዊያን የሚያነሱትን ቅሬታ የሚከታተልና የመፍትሔ ሀሳብ የሚያቀርብ ወታደራዊ መሪ መሾሙ ተገልጿል። ጀነራሉ የእስራኤል አሊያስ እና የውህደት ሚኒስቴር በኩል እንደተሾሙ የተገለጹ ሲሆን ኢትዮጵያን በተመለከተ የእስራኤልን ወቅታዊ የስደት ፖሊሲ የሚገመግም ቡድን እንዲያዋቅሩም ተጨማሪ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል ተብሏል። ከአገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ይሁንታ በመጠባበቅ ላይ ያሉት ጀነራሉ የጥናት ቡድኑ በአዲስ አበባ እና በጎንደር ወደ እስራኤል ለማቅናት በሚጠባበቁ ቤተ እስራኤላውያንን መርዳት ዋነኛ ስራቸው እንደሚሆንም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል። ብርጋዴር ጄኔራል ሃርል ከዚህ ቀደም በእስራኤል ቁልፍ የስልጣን ቦታዎች ላይ ተመድበው ማገልገላቸው ተገልጿል። ባሳለፍነው ሳምንት ቤተ…
Read More
ዳሸን ባንክ ደንበኞቹ ከየትኛውም ሀገር ሆነው ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ አስጀመረ

ዳሸን ባንክ ደንበኞቹ ከየትኛውም ሀገር ሆነው ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ አስጀመረ

ዳሸን ባንክ እና ማስተር ካርድ በጋራ በመተባበር "ቨርቹዋል የቅድመ ክፍያ ካርድ" የተሰኘ አገልግሎት በይፉ አስተዋውቀዋል፡፡ ካርዱ ከተለደው እና በሥም ከሚታተመው የፕላስቲክ ካርድ የተለየ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ደንበኞች ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሆነው ገንዘባቸውን መጠቀምና ማንቀሳቀስ የሚችሉበት አማራጭ ነው ተብሏል። የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ እንዳሉት "ዳሸን ባንክ ይህን በአይነቱ የተለየ ካርድ ማስተዋወቁ፤ ባንኩ ለደንበኞቹ ቀላል፣ ምቹና አስተማማኝ የፋይናስ አገልግሎቶችን ይበልጥ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል" ብለዋል፡፡ ዳሽን ባንክ ከዚህ ቀደም "የውጪ ምንዛሬ ሂሳብ" ላላቸው ደንበኞቹ ብቻ የሚያገለግል ካርድ በሥራ ላይ ማዋሉን ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ አዲስ የተዋወቀው “ቨርቹዋል የቅድመ ክፍያ ካርድ” በአጠቃላይ ለአለም ዓቀፍ ተጓዦች ታስቦና ከፍተኛ የደህንነት መጠበቂያ ተደርጎለት በአማራጭነት…
Read More
አፍሪካ ህብረት በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ እንዳሳሰበው ገለጸ

አፍሪካ ህብረት በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ እንዳሳሰበው ገለጸ

የአፍሪካ ህብረት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ አማራ ክልል ያለው ሁኔታ እንዳሳሰበው አስታውቋል። ህብረቱ በመገለጫው አክሎም የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀማት ጉዳቱን እየተከታተሉት እንደሆነም ገልጿል። ሊቀመንበሩ አክለውም በአማራ ክልል ያለውን ወታደራዊ ፍጥጫ በቅርበት እየተከታተሉት መሆኑንም አስታውቋል። አፍሪካ ህብረት ለኢትዮጵያ ህገመንግስታዊ ስርዓት፣ ሉዓላዊነት እና አንድነት ድጋፍ እንደሚያደርግም ህብረቱ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። ሁሉም የግጭቱ ተሳታፊ አካላት ንጹሀንን ከጉዳት እንዲጠብቁ እና ግጭት እንዲያቆሙ ያሳሰቡት ሊቀመንበሩ ወደ ውይይት እንዲመጡ እና ችግራቸውን እንዲፈቱም አስጠንቅቋል። ሙሳ ፋኪ አክለውም አፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ለሚደረጉ ውይይቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። የፌደራል መንግስት ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ላይ የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ አደራጃለሁ በማለቱ በአማራ ክልል ተቃውሞ ገጥሞታል። ይህን ተከትሎም…
Read More
የአፍሪካ ምግብ ዋስትና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ፈተና እንደገጠመው ተገለጸ

የአፍሪካ ምግብ ዋስትና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ፈተና እንደገጠመው ተገለጸ

19ኛው የአፍሪካ አካባቢ ጥበቃ ሚንስትሮች ጉባኤ የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት እድሎችን መጠቀም እና ትብብርን ማጎልበት" በሚል ሀሳብ በአዲስ አቡባ ተካሂዷል። በዚህ ጉባኤ ላይ አፍሪካ አካባቢ ጥበቃ ሚንስትሮች፣ የዘንድሮው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዓመታዊ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አዘጋጅ ሀገር ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ሱልጣን አልጃቢር ተገኝተዋል። እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎች፣ ተመራማሪዎች እና ተቋማት መሪዎች እንደተገኙ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካን የምግብ ዋስትና እየፈተነ ነው ብለዋል። አቶ ደመቀ አክለውም ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳትን ለመከላከል እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ አረንጓዴ አሻራ ስትራቴጂ ነድፋ እየተገበረች መሆኗንም ጠቅሰዋል። የኮፕ28 አለም አቀፍ አየር…
Read More
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን ለመጎብኘት አዲስ አበባ ገቡ

የተባበሩት አረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን ለመጎብኘት አዲስ አበባ ገቡ

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል። ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከተለያዩ የመንግስት የስራ ኃፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል። ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም የአቡዳቢ አልጋ ወራሽ በነበሩበት ወቅት በ2018 በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው ነበር። ሁለቱ ሀገራት የጠበቀ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት ሲሆኑ በተለይም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ዱባይ እና አቡዳቢ በማምራት በመስራት ላይ ናቸው፡፡ እንዲሁም ሁለቱ ሀገራት በሰው ሀብት ልማት፣ በንግድ…
Read More
ኢትዮጵያ በ34 ሚሊዮን ዶላር አዲስ ተሽከርካሪዎችን ልትገዛ መሆኗን አስታወቀች

ኢትዮጵያ በ34 ሚሊዮን ዶላር አዲስ ተሽከርካሪዎችን ልትገዛ መሆኗን አስታወቀች

የቻይና ሶስት ኩባንያዎች 312 ተሽከርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ለመሸጥ ተስማሙ የቻይናዎቹ ዞሆንግቶን ሻንዚ እና ሻንጋይ የተሰኙ የአውቶሞቲቭ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ያወጣችውን ዓለም አቀፍ ጨረታዎችን አሸንፈዋል ተብሏል። ኢትዮጵያ ለተሽከርካሪዎቹ ግዢ 34 ሚሊዮን ዶላር በጀት መመደቧ ተገልጿል። የመንግስት ግዥ አገልግሎት በገንዘብ ሚኒስቴር ጠያቂነት ለፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች እና ለመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ጨረታ አውጥቶ ነበር። ሊገዙ የታሰቡት ተሽከርካሪዎች ብዛታቸው 312 ሲሆኑ በኤሌክትሪክና በነዳጅ የሚሰሩ እንደሆኑም ተገልጿል። ለተሽከርካሪዎች ግዢ 34 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ወጪ ይደረጋል የተባለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 33ቱ የኤሌክትሪክ ሚኒባስ ናቸው ተብሏል። የቻይናው ዞሆንግቶን የተሰኘው ኩባንያ 47 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሚኒባሶችን በሶስት ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ ለማስረከብ ጨረታውን እንዳሸነፈ ተገልጿል።…
Read More
የሳፋሪኮሙ ኤምፔሳ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ስራ ጀመረ

የሳፋሪኮሙ ኤምፔሳ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ስራ ጀመረ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት የሆነው ኤምፔሳ (M-PESA) ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ፍቃድ ካገኘ ከሦስት ወራት በኋላ ስራ መጀመሩን አስታወውቋል። ኩባንያው ባለፉት ሦስት ወራት አስፈላጊ የሲስተም ፍተሻዎችን እና የቴክኒክ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱንም ገልጿል። ኩባንያው ከዚህ በተጨማሪም ከባንኮች ጋር አብሮ ለመስራት የአጋርነት ስምምነቶች ከመፈራረም ጀምሮ ወኪሎችን መመልመሉን እና ማሰልጠኑንም አስታውቋል። አገልግሎቱን ለማግኘትም የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞች የሆኑ ሁሉ የኤምፔሳ አገልግሎትን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል። ደንበኞች የአንድሮይድ (Android) እና የአይኦኤስ (IOS) ስልክ ተጠቃሚዎች በሳፋሪኮም መስመራቸው *733# ላይ በመደወል የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተገልጿል። የኤምፔሳ መተግበሪያ በ5 ቋንቋዎች የተዘጋጀ እና የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ከፕሌይስቶር በማውረድ መጠቀም የሚችሉት ሲሆን፤ የአይኦኤስ (IOS) ተጠቃሚ ደንበኞቻችን ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በአፕስቶር…
Read More
የጠቅላይ ሚንስትሩ የቀድሞ አማካሪ በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ በሀይል እንደማይፈታ ተናገሩ

የጠቅላይ ሚንስትሩ የቀድሞ አማካሪ በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ በሀይል እንደማይፈታ ተናገሩ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሁለት ሳምንት በፊት በሚንስትሮች ምክር ቤት የተወሰነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አጽድቋል። ከምክር ቤቱ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት የቀድሞው የጠቅላይ ሚንስትሩ የደህንነት አማካሪ፣ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር እና የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለምክር ቤቱ አባላት ንግግር አድርገዋል። አቶ ገዱ ከሌሎች የምክር ቤቱ አባላት ለየት ባለ መልኩ በአማራ ክልል ስላለው ሁኔታ ባደረጉት ንግግር ከምክር ቤቱ አባላት ተቃውሞ ገጥሟቸው ተቋርጧል። አቶ ገዶ ንግግራቸው እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ባደረጉት ንግግር " ብልጽግና መራሹ መንግሥት ራሱ የፖለቲካ ችግር እየፈጠረ ነው" ብለዋል። "ፓርቲው የፈጠረውን የፖለቲካ ችግር ለመፍታት የሚሞክረው ከፖለቲካዊ መፍትሄ ይልቅ ወታደራዊ መፍትሄ ሆኗል" የሚሉት አቶ ገዱ ብልጽግና ባለፉት አምስት ዓመታት በርካታ…
Read More
የጸጥታ ሀይሎች በአማራ ክልል ሰላማዊ ዜጎችን መግደላቸው ተገለጸ

የጸጥታ ሀይሎች በአማራ ክልል ሰላማዊ ዜጎችን መግደላቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ሰላማዊ ዜጎች ከፍርድ ቤት ውጪ በአደባባዮች ላይ መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ መግለጫ አውጥታል። ኮሚሽኑ በሪፖርቱ በአማራ ክልል ጎንደርና ሸዋሮቢት በርካታ አካባቢዎች ከፍርድ ቤት ትዕዛዘው ውጪ ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች መገደላቸውን የሚያመላክቱ መረጃዎች እንደደረሱት ገልጻል። ተፋላሚ ሀይሎች ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ግጭቶችን እንዲያቆሙ፣ ለሰላማዊ ንግግር ስፍራ እንዲያመቻቹና ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ኮሚሽኑ አክኖም በአማራ ክልል ያለው ግጭት በሰብዓዊ መብቶች ላይ እያሳደረ ያለውን ተፅዕኖ እየተከታተለ መሆኑን ገልጾ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመደንገጉ በፊትና በኋላ ከአዲስ አበባና ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መረጃዎችን እከተቀበለ እንደሆነም አስታውቋል። በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች…
Read More
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የስድስት ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አጸደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የስድስት ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አጸደቀ

የተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የውሳኔ ሀሳብን በአብላጫ ድምጽ በ16 ተቃውሞ እና በ12 ድምጽ ተአቅቦ ማጽደቁ ተገልጿል። የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአማራ ክልል እና እንደ አስፈላጊነቱ በሌሎችም ቦታዎች ተግባራዊ ይሆናል የተባለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጽደቁን ምክር ቤቱ በፌስቡክ ገጹ  አስታውቋል። የሚንስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል በትጥቅ የተደገፈ እንቅስቃሴ መኖሩን እና ይህንንም በመደበኛው የህግ ስርአት መቆጣጠር የማይቻልበት ሁኔታ መፈጠሩን በመግለጽ ነበር ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የወሰነው። ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቦርድ አባላትን እና ሰብሳቢዎችንም መርጧል። በአማራ ክልል፣ በፌደራል መንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተፈጠው ግጭት ንጹሃን ሰዎች እንዲገደሉ ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት…
Read More
ጦርነት እና እግር ኳስ በኢትዮጵያ….

ጦርነት እና እግር ኳስ በኢትዮጵያ….

ቢኒያም ተክለወይኒ እባላለሁ። ትውልዴ ሽረ ነው። ከጦርነቱ በፊት የፕሪሚየር ሊጉ ተካፋይ የሆነው የስሑል ሽረ ዋና ቡድን ተጨዋች ነበርኩ ። ሊብሮ ነኝ ። አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ ዋና አሰልጣኛችን ነበር ። ኳስ እወዳለሁ ። ደጉ ደበበን አደንቃለሁ ። እንደ እርሱ የመሆን ምኞት ነበረኝ ። ተቀራኒ ሆነን ተጫውተናልም:: በኳስ ጨዋታ መከላከልን እወዳለሁ ። አዳነ ሳላ አማኑኤልን ጨምሮ ከብዙ ጎበዝ አጥቂዎች ተፋጥጫለሁ ። ሁሉንም ገትሬ አቁሜያለሁ ። ቡድኔ ጎል እንዳይቆጠርበት በአግባቡ መምራት መከላከል ከስሑል ሽረ ጋር በፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን መሆን የዘወትር ህልሜ ነበር ። ከሽረ ውጭ ሌላ ክለብ አላውቅም ። በኳስ ጨዋታ መንገዴ የእራሴንም የቤተሰቦቼንም ህይወት መቀየር ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተመርጦ መጫወት የሌት ተቀን…
Read More
እስራኤል ከአማራ ክልል 200 ዜጎቿን ከኢትዮጵያ አጓጓዘች

እስራኤል ከአማራ ክልል 200 ዜጎቿን ከኢትዮጵያ አጓጓዘች

እስራኤል ከአማራ ክልል 200 የሚሆኑ ዜጎቿንና አይሁዳውያንን ማስወጣቷን አስታወቀች። የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርና የጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት በጋራ ባወጡት መግለጫ በክልሉ በተነሳው ግጭት 174 እስራኤላዊያንና ወደ ሀገሪቱ ለመግባት ብቁ የሆኑ ቤተ-እስራኤላዊያን ከጎንደር እንዲወጡ ተደርጓል። ሌሎች 30 የሚሆኑ ዜጎች ደግሞ ከባህር ዳር መውጣታቸው ተነግሯል።  በአራት በረራዎች ከአማራ ክልል እንዲወጡ የተደረጉት ዜጎች አዲስ አበባ ደርሰዋል ተብሏል። ከአዲስ አበባም ወደ እስራኤል ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኢላይ ኮን እስራኤላዊያኑ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እስኪወስኑ ድረስ በአዲስ አበባ እንደሚቆዩ ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ መቆየትም እንደሚችሉም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ እስራኤል ዜጎቿን የትም ይሁኑ የት ጥበቃ እንደምታደርግላቸው መናገራቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኸን ዘግቧል። ጠቅላይ ሚንስትሩ "አጭር፣ ኮሽታ…
Read More
አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በአማራ ክልል ያለው አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገለጹ

አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በአማራ ክልል ያለው አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገለጹ

የተለያዩ አገራት በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ኹከትና የዜጎች ሞት እንዳሳሰባቸው ገለጹ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑክን ጨምሮ የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች ሰሞኑን በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ኹከት፣ የዜጎች ሞትና አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ በኢትዮጵያን እና የኦስትሪያ፣ የቤልጂየም፣ የቼክ ሪፖብሊክ፣ የዴንማርክ ፣ የፊንላንድ፣ የፈረንሳይ፣ የጀርን፣ የሃንጋሪ፣ የአየርላንድ ፣ የኢጣሊያ፣ የሉክሰምበርግ፣ የማልታ፣ የኔዘርላንድስ፣ የሮማኒያ፣ የፖላንድ፣ የፖርቱጋል፣ የስሎቬንያ፣ የስፔን እና የስዊድን ኤምባሲዎች የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክተው የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም በክልሉ የተቀሰቀሰው ኹከት፣ የዜጎች ሞትና አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው የገለጹ ሲሆን፤ ኹሉም ወገኖች ሲቪሎችን እንዲጠብቁ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ህዝቦች የተሟላ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀጣይነት ያለው ሰብአዊ ተደራሽነት እንዲረጋገጥ፣ የውጪ ዜጎች ከግጭቱ አካባቢ ለቅቀው እንዲወጡ እና ደህንነቱ በተጠበቀ…
Read More
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአማራ ክልል አምቡላንሶቹ ከጥቃት እንዲጠበቁለት ጠየቀ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአማራ ክልል አምቡላንሶቹ ከጥቃት እንዲጠበቁለት ጠየቀ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአማራ ክልል በተከሰተው ጦርነት እና ድጋፍ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል። የማህበሩ ዋና ጸሀፊ አቶ ጌታቸው ተአ እንዳሉት በአማራ ክልል በተከሰተው ጦርነት የቆሰሉ ሰዎች፣ የተጠፋፉ እና ሌሎች ጉዳቶች የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ። በዚህም መሰረት የህክምና እና ሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ለመርዳት ቀይ መስቀል ማህበር ተሽከርካሪዎቹን በማንቀሳቀስ ላይ በመሆኑ ተፋላሚ ወገኖች ከጥቃት እንዲጠብቁት ማህበሩ ጥሪ አቅርቧል። በቀይ መስቀል ተሽከርካሪዎች የጦር መሳሪያ፣ ወታደሮችን እና ታጣቂዎችን ማጓጓዝ ክልክል መሆኑን የገለጸው ማህበሩ ዓላማችን ተጎጂዎችን መርዳት በመሆኑ ህብረተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግላቸውም ጥሪ አቅርቧል። አሁን ላይ የቆሰሉ ሰዎችን ለመርዳት በክልሉ የደም እጥረት እና የህክምና ቁሳቁስ እጥረት በማጋጠሙ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ በጎ…
Read More
በአዲስ አበባ ግብረሰዶም ይፈምባቸዋል የተባሉ መዝናኛ ቤቶች ታሸጉ

በአዲስ አበባ ግብረሰዶም ይፈምባቸዋል የተባሉ መዝናኛ ቤቶች ታሸጉ

አዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በከተማዋ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚፈጸምባቸው ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል። ፖሊስ እርምጃውን እየወሰደባቸው ያሉት ሆቴሎች፣ ባሮችና ሬስቶራንቶች ሲሆኑ ከአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር እንደሆነ ገልጿል። የተመሳሳይ ጾታ መዝናና ቤቶች ከነባሩ የሀገሪቷ ባህል፣ ወግ፣ የአኗኗር ስርዓት እና ኃይማኖቶች ባፈነገጠ መልኩ ወንጀሎች ይፈጸምባቸው ነበርም ተብላል። ፖሊስ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚያስፈጽሙ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ፔንሲዮኖችና መሰል የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ከህብረተሰቡ ጥቆማ እንደደረሰውም አስታውቋል ። የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የግብረ-ሰዶም ተግባር መፈጸምና ማስፈጸም በኢትዮጵያ በሥራ ላይ ባሉ ሕጎች የተከለከለ ናቸው ብሏል። ፖሊስ የተመሳሳይ ጾታ መዝናኛ ቤቶች ባለቤቶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየታጣራባቸው እንደሆነም አስታውቋል።
Read More
ወደ አሜሪካ ካቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ሁለት ሰዎች መጥፋታቸው ተገለጸ

ወደ አሜሪካ ካቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ሁለት ሰዎች መጥፋታቸው ተገለጸ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቅርቡ ወደ አሜሪካ አቅንቶ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን አድርጎ ተመልሷል። ፌዴሬሽኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአሜሪካ ቆይታን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ብሔራዊ ቡድኑ በአሜሪካ ቆይታው አላማውን እንዳሳካ የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ባህሩ ጥላሁን በመግለጫው ላይ ተናግረዋል። የዲሲ ዩናይትድ ድርሻ ያላቸው አቶ እዮብ ማሞ ከፌዴሬሽኑ ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችል ሁኔታ ላይ በቅርቡ ከስምምነት እንደሚደርሱም አቶ ባህሩ ገልጸዋል። ለዚህም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በቅርቡ ወደ አሜሪካ በማቅናት ስምምነቱን ይፈፅማሉም ብለዋል። ከዲሲ ዩናይትድ ጋር የሚደረገው ስምምነት ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾች በዲሲ ዩናይትድ የመጫወት እድልን እንዲያገኙ እንደሚያስችል አቶ ባህሩ አክለዋል። ይሁንና የቡድኑ የትጥቅ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አውግቼ እና የፊዚዮቴራፒ ባለሙያው…
Read More
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2016 ውድድር መርሀ ግብር ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2016 ውድድር መርሀ ግብር ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2016 የውድድር ዓመት የጨዋታ እጣ ድልድልበአዲስ አበባ ይፋ ሆኗል። በዚህ መሰረት ሀምበርቾ ዱራሜ ከድሬዳዋ ከተማ የመክፈቻ ውድድር ጨዋታውን የሚያደርጉ ሲሆን ሻሸመኔ ከተማ ከወላይታ ዲቻ፣ ሀዋሳ ከተማ ከፋሲል ከተማ የፊታችን መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ. ም ያደርጋሉ። እንዲሁም አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኢትዮጵያ መድህን ከከባህርዳር፣ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዲያ ሆሳዕና ከመቻ የፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎችን ይጫወታሉም ተብሏል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ካምፓኒ ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ በዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት ለተወዳዳሪ ክለቦች መልካም የውድድር ዓመት እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል። በ2015 የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ስያሜ መብትን ቤትኪንግ ይዞ እንደነበር የገለጹት ስራ አስኪያጁ የ2016 የሊግ…
Read More
አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በበርካታ ቴአትሮች ፣ ፊልሞች እና የቴሌቭዥን ድራማዎች ላይ በተዋናይነት በመሳተፍ እውቅናን ያተረፈው አርቲስት አብነት ዳግም በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ አርቲስት አብነት ለረዥም ጊዜ በከባድ የስኳር በሽታ ታምሞ የቆየ ሲሆን፤ ትናንት ሕመሙ በርትቶበት ወደ ጤና ጣቢያ ቢወሰድም ሕይወቱን ማዳን ሳይቻል በመቅረቱ ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል፡፡ አርቲስት አብነት አሉላ አባነጋ፣ የቼዝ ዓለም፣ ዳኛው፣ እስረኛው ንጉስ እና ነቅዕ ቴአትሮች ላይ ተውኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አያስቅም፣ አንድ እድል፣ ላምባዲና፣ ሰበበኛ፣ ባንቺ የመጣ፣ ቁልፉን ስጭኝ፣ የነገርኩሽ እለት፣ ፍቅር እስከ መቃብር እና አትሸኟትም ወይ በተሰኙ ፊልሞች ላይ በመተወን አድናቆትን አግኝቷል። ስንቅ ፣መለከት፣ ትርታ እና ለወደዱት ደግሞ የተሳተፈባቸው ቲቪ ድራማዎች ሲሆኑ፤ በግሉም የቅብብሎሽ ድራማን ደርሷል።
Read More
በጎንደር እና ባህርዳር ያሉ ከአንድ ሺህ በላይ ሱዳናዊያን ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ

በጎንደር እና ባህርዳር ያሉ ከአንድ ሺህ በላይ ሱዳናዊያን ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ

በአማራ ክልል በተለይም ከአንድ ሳምንት በፊት አንስቶ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወሳል፡፡ በሱዳን በተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት የተሻለ ደህንነት ፍለጋ በሚል በተማ አድርገው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሱዳናዊያን ዜጎች ችግር ውስጥ መግባታቸውን ለአልዐይን ተናግረዋል፡፡ በተለይም በጎንደር እና በባህርዳር ባሉ ሆቴሎች የቆዩ ሱዳናዊያን በምግብ እጥረት፣ ደህንነት እና ትራንስፖርት ችግር  ገጥሞናልም ብለዋል፡፡ ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ በላይ እንደሚሆኑ የነገሩን እነዚህ ሱዳናዊያን መንገደኞች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከዚያም ወደ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎች ሀገራት የመጓዝ አቅድን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ተናግረዋል፡፡ ሱዳናዊያኑ በተለይም ከጎንደር እና ብህርዳር ከተሞች ውስጥ ባሉ ሆቴሎች ከተጠለሉት በተጨማሪም በመተማ በኩል አድርገው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ከገቡ በኋላ…
Read More
በኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎች ፈንድተው 23 ህጻናት መገደላቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎች ፈንድተው 23 ህጻናት መገደላቸው ተገለጸ

በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመት የነበረው ጦርነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተፈረመ ስምምነት መሰረት ማብቃቱ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እንዳለው ሲቪል ሰዎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ፣ በእርሻ ፣ በውሃ መቅጃ እና በገበያ ቦታዎች እንዲሁም የትምህርት ወይም የጤና ተቋማትን የመሳሰሉ የዕለት ተዕለት መሠረታዊ ሕይወት ወደሚከወኑባቸው ሥፍራዎች በሚወስዱ መንገዶች አካባቢ የተቀበሩ ፈንጂዎች ፣ የተጣሉ ቦምቦች ፣ የከባድ መሣሪያ ቅሪቶች እና በቀላል ንክኪ የሚፈነዱ ሌሎች መሣሪያዎች በሰዎች ሕይወት ፣ አካልና ንብረት ላይ ጉዳት እያደረሱ ይገኛል ብላል። ኮሚሽኑ ይህን በተመለከተ ባደረገው ክትትል በአፋር ክልል ፣ ካሳጊታ ከተማ በአንድ መኖሪያ አካባቢ በድንገት በፈነዳው የሞርታር ጥይት ምክንያት 4 ሰዎች ወዲያው ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን በከፍተኛ ደረጃ የአካል ጉዳት…
Read More
በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ጦርነት ለአመታት የተጠራቀመ ብሶት ውጤት እንደሆነ ተገለጸ

በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ጦርነት ለአመታት የተጠራቀመ ብሶት ውጤት እንደሆነ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ጦርነቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት ድንገት የተከሰተ ሳይሆን መንግሥት ሃላፊነቱን በተገቢው ሁኔታ ባለመወጣቱ የተከማቹ ሀገራዊ የፖለቲካ ትኩሳቶች የግለታቸው ጫፍ ላይ ሲደርሱ የተፈጠረ ነው ብሏል። ፓርቲው በመግለጫው ይህ ለዓመታት የታመቀው ብሶት፣ የመጠቃት ስሜት እና ተስፋ መቁረጥ ገደፉን አልፎ ክልሉን አሁን ላለበት ሁኔታ ዳርጎታል ሲልም አመልክቷል፡፡ የዚህ ቀውስ መሠረታዊ ምክንያት በብልፅግና ውስጥ ያለው የጋራ ራዕይ መጥፋት፣ በየክልሉ እርስ በእርስ በመጓተት ላይ ያሉ ካድሬዎች የሚመሩት የመንግሥት የአስተዳደር ድክመትና በደል እንደኾነ ሊታወቅ ይገባል ሲልም ገልጾታል። ችግሩን ለማባባስ ፅንፈኛ የዘውጌ ፖለቲካ አስተሳስብን የሚያቀነቅኑ ታጣቂ ኃይሎች በጠራራ ፀሀይ ሰዎችን በመግደል ሽብርና ፍርሃት በመንዛት እንዲሁም ከግል ትርፋቸው ውጪ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አማራ ክልል የሚያደርጋቸውን በረራዎች ሰረዘ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አማራ ክልል የሚያደርጋቸውን በረራዎች ሰረዘ

አየር መንገዱ በድረገጹ እንዳስታወቀው ወደ ደሴ፣ ጎንደር፣ባህርዳር እና ላሊበላ የሚያደርገውን በረራ ሰርዣለሁ ብሏል፡፡ የተሰረዙት በረራዎች ነገ እና ከነገ በስቲያ ሊያደርጋቸው የነበሩ በረራዎች እንደሆኑ ገልጾ አየር መንገዱ ወደ ተጠቀሱት አካባቢዎች ለመጓዝ ትኬት የቆረጡ ደንበኞች በረራዎቹ እንደተመለሱ አስተናግዳለሁም ብሏል፡፡ ወደሥፍራው ለመጓዝ ትኬት የቆረጡ መንገደኞች ትኬታቸው ለአንድ ዓመት ያህል የሚያገለግል መሆኑን አውቃችሁ ወደፊት በፈለጋችሁት ቀን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ መቀየር ትችላላችሁም ብሏል፡፡ ገንዘቡን መመለስ እንፈልጋለን ለሚሉ ደንበኞችም ገንዘብ መመለስ እንደሚቻል ገልጾ በአቅራቢያችሁ ባሉ የአየር መንገዱ ቲኬት ቢሮዎች በመሄድ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻልም አስታውቋል፡፡ ይሁንና አየር መንገዱ በምን በረራዎቹን እንደሰረዘ ያልገለጸ ሲሆን በአማራ ክልል እየተካሄዱ ባለው ጦርነት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል…
Read More
ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም በአማራ ክልል ያለው አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገለጹ

ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም በአማራ ክልል ያለው አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገለጹ

ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም በአማራ ክልል ያለው አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገለጹ። የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሉት በአማራ ክልል ያለው አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ሁለተኛው ሰፊ የህዝብ ብዛት ያለው የአማራ ክልል ዋና ዋና መተላለፊያ መንገዶች መዘጋት የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎችን ያደናቅፋል ሲሉም ዶክተር ቴድሮስ ተናግረዋል። በክልሉ የኢንተርኔት መዘጋት የኮሙንኬሽን ስራውን አስቸጋሪ እንዳደረገውም ዳይሬክተሩ አክለዋል። ግጭቶች በህዝብ ጤና ላይ ወዲያውኑ ጉዳት ያደርሳሉ ያሉት ዶክተር ቴድሮስ ለተራዘመ የጤና እክሎች ይዳርጋሉም ብለዋል። በመሆኑም በአማራ ክልል የጤና መሰረተ ልማቶች ከጉዳት እንዲጠበቁ፣ የዓለም ጤና ድርጅት እና አጋሮች ስራቸውን እንደሚቀጥሉም ዶክተር ቴድሮስ አሳስበዋል። በተያያዘ ዜና በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት፤ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተጀመሩ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 26 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ እና ኤርባስ ጋር ድርድር ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 26 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ እና ኤርባስ ጋር ድርድር ጀመረ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ካዘዛቸው 26 አውሮፕላኖች ውስጥ ስምንቱን በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚረከብ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ገልጸዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው አየር መንገዱ ተጨማሪ 26 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግና ከኤርባስ ከተሰኙ ግዙፍ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያዎች ድርድር በማድረግ ላይ እንደሆነ ጠቁመዋል። አየር መንገድ በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ስምንት አውሮፕላኖችን እንደሚረከብ አስታውቋል። ከተገዙት አውሮፕላኖች መካከል አየር መንገዱ ስምንት የመንገደኛ አውሮፕላኖች በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚረከብም ነው የገለጹት። ቀሪዎቹ የመንገደኞች አውሮፕላኖች በቀጣይ ጊዜያት እንደሚገቡ ገልጸው፤ አየር መንገዱ ሌሎች ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ለማስገባት እቅድ እንዳለው ተናግረዋል። ጎን ለጎንም አየር መንገዱ በሰኔ ወር ከቦይንግ ኩባንያ ሊረከባቸው ግዥ የፈጸመባቸው ኹለት አውሮፕላኖችም በመጪው መስከረምና ጥቅምት ወራት እንደሚገቡ…
Read More
አሜሪካ በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት እንዳሳሰባት ገለጸች

አሜሪካ በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት እንዳሳሰባት ገለጸች

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በስልክ ተወያይተዋል። ብሊንከን በዚሁ ውቅት በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ ለቀጠናው ሰላምና ደህንነት ስጋት የሚፈጥር ነው ብለዋል። ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የእርዳታ እህል በፍትሃዊ መንገድ በሚቀርብበት መንገድ ላይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር መክረዋል። በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያሉ ልዩነቶችንም በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት አሜሪካ ሙሉ ድጋፍ እንደምታደርግ ብሊንከን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነግረዋቸዋል ተብሏል። በአማራ ክልል በሀገር መከላከያ እና ፋኖ መካከል ካሳለፍነው ሚያዝያ ጀምሮ ግጭት ውስጥ ገብተዋል። ግጭቱ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን የክልሉ መንግሥት ጉዳዩ ከአቅሜ በላይ ነው ሲል የፌደራል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ጠይቋል። በክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ መባባሱን ተከትሎ የኢትዮጵያ…
Read More
በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች በቡድን መደባደባቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች በቡድን መደባደባቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች በቡድን መደባደባቸው ተገለጸ በጎንደር ዩኒቨርስቲ የ12ተኛ ክፍል ፈተና ፈታኝ እና ሁለት ፖሊሶች መገደላቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል የ12ኛ ክፍል ፈተናን ለመፈተን ከአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ወደ ዩንቨርሲቲ የመጡ ተማሪዎች በቡድን መደባደባቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ላይ እንዳሉት በትምህር ቤቶቻቸው በመቧደን ተደባድበዋል ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የዶርም በር፣ ሎከር እና ሌሎች አካላዊ ጉዳት ደርሷል ብለዋል፡፡ ፖሊስ ክስተቱን እያጣራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ 87 ተማሪዎች ተይዘው ምርመራ በመካሄድ ላይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለም ከአዲስ አበባ ውጪ በጎንደር እና በጋምቤላ የ12ኛ ክፍል ፈተና በተወሰነ ደረጃ መስተጓጎሉ ተገልጿል፡፡ በጎንደር በተከሰተው ግጭት ምክንያት 16 ሺህ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደሴ፣ ጎንደር፣ እና ላሊበላ በረራውን ሰረዘ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደሴ፣ ጎንደር፣ እና ላሊበላ በረራውን ሰረዘ

አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ባሰራጨው መረጃ ወደ ደሴ፣ ጎንደር፣ እና ላሊበላ የሚያደርገውን በረራ ሰርዣለሁ ብሏል፡፡ የተሰረዙት በረራዎች ነገ እና ከነገ በስቲያ ሊያደርጋቸው የነበሩ በረራዎች እንደሆኑ ገልጾ አየር መንገዱ ወደ ተጠቀሱት አካባቢዎች ለመጓዝ ትኬት የቆረጡ ደንበኞች በረራዎቹ እንደተመለሱ አስተናግዳለሁም ብሏል፡፡ ይሁንና አየር መንገዱ በምን በረራዎቹን እንደሰረዘ ያልገለጸ ሲሆን በአማራ ክልል እየተካሄዱ ባለው ጦርነት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል፡፡ በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛ የህግ ማስከበር ስርአት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መጠየቁ ይታወሳል። በአማራ ክልል በርካታ ከተሞች…
Read More
በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ

በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የጠቅላይ ሚንስቴር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የሕዝብን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በቀረበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 /2015 ላይ ነው፡፡ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚታየውን በትጥቅ የተደገፈ ህገወጥ እንቅስቃሴ በመደበኛ የህግ ማስክበር ስርዓት ለመቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ደረጃ የተሸጋገረ በመሆኑ፤ ይህ እንቅስቃሴ የክልሉን ነዋሪ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ያወከ እና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ፤ የሕዝብን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም ህግ እና ስርዓት ለማስከበር የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ እንቅስቃሴው በሃገር ደህንነት እና በህዝብ ሰላም…
Read More
የአማራ ክልል የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በይፋ ጠየቀ

የአማራ ክልል የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በይፋ ጠየቀ

በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛ የህግ ማስከበር ስርአት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠየቀ። በክልሉ የተከሰተው የሰላም መደፍረስ ከፍተኛ ሰብአዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እያደረሰ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል። የተከሰተውን የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ለማዋል እስካሁን በክልሉና በፌደራል የፀጥታ ሃይሎች በኩል በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል። ሆኖም በክልሉ ያለው የፀጥታ መደፍረስና ጥቃት በንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት በአስቸኳይ ለማስቆም የፌደራል መንግስት ከመደበኛው የህግ ማስከበር ስርአት ባሻገር በኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሰረት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በአፋጣኝ እንዲተገበር ነው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የጠየቀው። ክልሉ ወደ ቀደመ መረጋጋቱ እንዲመለስ ዜጎች ሰላማቸው ተመልሶ አርሶአደሩ…
Read More
በአማራ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋረጠ

በአማራ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋረጠ

በአማራ ክልል በርካታ ከተሞች በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በሁለቱ አካላት መካከል ውጊያ መጀመሩን ተከትሎ በአማራ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ከነዋሪዎች አረጋግጠናል፡፡ በክልሉ ኢንተርኔት ለምን እንደተቋረጠ ኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት እስካሁን ያሉት ነገር የለም፡፡ ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በቴሌግራም ላይ እገዳ የጣለች ሲሆን መተግበሪያው በቪፒኤን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት መባባሱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ እና ጎንደር የሚያደርጋቸውን በረራዎች መሰረዙ ይታወሳል፡፡ የስፔን፣ ፖላንድ እና በርካታ ሀገራት ኢምባሲዎች ዜጎቻቸው ወደ አማራ ክልል እንዳይጓዙ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡ ከወራት በፊት በኦሮሚያ ክልል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አጋጥሟት የነበረዉን የመከፋፈል ድርጊትና የጳጳሳት ሹመነትን…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ እና ጎንደር የነበረውን በረራ ሰረዘ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ እና ጎንደር የነበረውን በረራ ሰረዘ

በአማራ ክልል በርካታ ከተሞች በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ከተጀመረ ሳምንታትን ያስቆጠረ ሲሆን ንጹሃን የጉዳት ሰለባ እየሆኑ እንደሆነም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ተናግረዋል፡፡ አቶ ክርስቲያን አክለውም የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስተዳድር በአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በህዝብ ላይ ተኩስ ከፍቷል ብለዋል፡፡ የግጭቱ መነሻ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ለምን ይፈርሳል በሚል እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን የቀድሞ ልዩ ሀይል አባላት እና የፋኖ ታጣቂዎች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ውጊያ ውስጥ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ የፋኖ ታጣቂዎች ቀስ በቀስ ወረዳዎችን እና ከተሞችን እየተቆጣጠሩ መምጣታቸውን ተከትሎ በታጣቂዎቹ…
Read More
የአፍሪካ ልማት ፈንድ ለኢትዮጵያና 84 ሚሊየን ዶላር ሰጠ

የአፍሪካ ልማት ፈንድ ለኢትዮጵያና 84 ሚሊየን ዶላር ሰጠ

ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ፈንድ ለስንዴ ምርትና ምርታማነት ማሻሻያ የሚውል የ84 ነጥብ ሶስት  ሚሊየን ዶላር (4. 5 ቢሊየን ብር) የልማት ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ከልማት ደጋፋ ውስጥ 54 ሚሊየን ዶላር ከአፍሪካ ልማት ፈንድ፣ 20 ሚሊየን ዶላር ከኔዘርላንድ መንግሰት፣ እንዲሁም 10 ነጥብ ሶስት ሚሊየን ዶላር ደግሞ ሌሎች ድርጅቶች ሰጥተዋል። የልማት ድጋፋ በአነስተኛ እርሻ የስንዴ አምራች ገበሬዎችን ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል የሚውል ሲሆን ይህን ዕውን ለማድረግ እንዲቻል ድጋፉ ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የስንዴ ምርት ለማምረት ፣ የገበያ መሰረተ ልማቶችንና ትስስርን ለማሳደግ እንዲሁም በዘርፋ ያሉ ፕሮጀክቶችን ለማስተዳደር የሚውል ነው፡፡ የልማት ድጋፋን ስምምነት በኢትዮጵያ መንግስትን በኩል የገንዘብ ሚነስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እንዲሁም የአፍሪካ ልማት ፈንድን በመወከል ዶ/ር አብዱል…
Read More
ቤተ ክርስቲያኗ በትግራይ ክልል ያሉ የአራት ሊቀ ጳጳስን ክህነት አነሳች

ቤተ ክርስቲያኗ በትግራይ ክልል ያሉ የአራት ሊቀ ጳጳስን ክህነት አነሳች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትግራይ ክልል የተሰጠው ኤጲስ ቆጵሳት ሹመት ህገወጥ መሆኑን አስታውቃለች። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተፈጠረው ወቅታዊ የዶግማ፣ የቀኖናና የአስተዳደራዊ ጥሰቶችን አስመልክቶ ውሳኔዎች አሳልፌያለሁ ብሏል። ቤተ ክርስቲያኗ አክላም ከፍተኛውን ሐዋርያዊ ተልእኮ እንዲወጡ አደራ በተሰጣቸው ሊቃነ ጳጳሳት በማኅበረሰብ ዕድገትና አስተዳደር ውስጥ ከሕዝብ ጋር በቆመች፣ ከፖለቲካ በጸዳች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ መንፈሳዊና ሕዝባዊት ተቋምነቷን በመካድ ከፍተኛ የሆነ ሕገ ወጥ ድርጊትና ተቋምን የመናድ እንደሁም መዋቅሯን የማፍረስ ተግባር ተከናውኖብኛል ብላለች። ሐምሌ 16 እና 23 ቀን 2015 ዓ/ም በክልል ትግራይ በማእከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ገዳም ውስጥ የተፈጸመውን ሕገወጥ የሆነ አስነዋሪ፤ የቀኖና ቤተ…
Read More
ጣልያናዊው ጂያንሉጂ ቡፎን ጓንቱን ሰቀለ

ጣልያናዊው ጂያንሉጂ ቡፎን ጓንቱን ሰቀለ

ጣልያናዊው ጂያንሉጂ ቡፎን ጓንቱን ሰቀለ የጣልያን ብሔራዊ ቡድን እና ጁቬንቱስ ታሪካዊ ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ቡፎን በ 45 ዓመቱ ከውድድር ራሱን እንዳገለለ አስታውቋል። ጂያንሉጂ ቡፎን በጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ቤት አስራ ሰባት አመታትን ያሳለፈ ሲሆን በክለቡ 685 ጨዋታዎች በማድረግ በክለቡ ታሪክ ብዙ ጨዋታ ያደረገ ሁለተኛው ተጨዋች ነው። ሀያ ስምንት አመታትን በተጨዋችነት ያሳለፈው የ45 ዓመቱ ጂያንሉጂ ቡፎን ከጣልያን ብሔራዊ ቡድን ጋር በ2006 የዓለም ዋንጫን አሸንፏል። ለጣልያን ብሔራዊ ቡድን 176 ጨዋታዎችን ያደረገው ቡፎን ለብሔራዊ ቡድኑ ብዙ ጨዋታዎችን በማድረግ ታሪካዊ ተጫዋች ነው። ተጫዋቹ ከጁቬንቱስ በተጨማሪ ወደ ፓሪስ በማቅናት በፒኤስጂ እግር ኳስ ክለብ ውስጥ ለአንድ ዓመት በግብ ጠባቂነት አገልግሏል።
Read More
በትግራይ ክልል ከ200 በላይ የሚሆኑ ፖሊሶች ከስራ ታገዱ

በትግራይ ክልል ከ200 በላይ የሚሆኑ ፖሊሶች ከስራ ታገዱ

በትግራይ የሚገኙ የፖሊስ አባላት ከብልፅግና ፓርቲ ደሞዝ ስትቀበሉ ነበር በሚል እና የትጥቅ ትግሉን አልተቀላቀላቹም በማለት ከስራ እና ከደሞዝ እንዲታገዱ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡ እነዚህ ቅሬታ አቅራቢዎች እስከ 30 ዓመት ድረስ በተለያዩ የትግራይ አካባቢ ተመድበው በፖሊስነት ስራ ላይ ተሰማርተው የቆዩ የቀድሞ የትግራይ ፖሊስ አባላት፥ ከስራ እና ደመወዝ ውጭ እንዲሆኑ የተደረጉት ከጦርነቱ ጅማሮ በኃላ ባለው ጊዜ መሆኑ ነግረውናል።  እንደ ፖሊሶቹ ገለፃ በ2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ መከላከያ ትግራይን ሲቆጣጠር አቋቁሞት በነበረው ግዚያዊ አስተዳደር ጋር አብራችሁ ሰርታችኋል የመንግስትን ደሞዝም ተቀብላችኋል በሚል መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በ2013 ዓ.ም በርሃ የነበረው የህውሀት ምክር ቤት በዶ/ር ድብረፅዮን ፊርማ በተረጋገጠ ደብዳቤ ነባሩን የፖሊስ አባል በመሰረዝ አዲስ ማቋቋሙን በመግለፅ ከህግ ውጪ ያለ ስራ እንዲቀመጡና…
Read More
ኢትዮጵያ ለአደይ አበባ ስታድየም አዲስ የግንባታ ጨረታ ልታወጣ ነው

ኢትዮጵያ ለአደይ አበባ ስታድየም አዲስ የግንባታ ጨረታ ልታወጣ ነው

ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ የቆየውን የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ በአዲሱ በጀት ዓመት እንደገና ለማስጀመር በጀት መያዙን ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ገልጿል ። የባህል እና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ በ48 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባውና 62ሺ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታን ለማስቀጠል በ2016 ዓ.ም በጀት የተያዘለት በመሆኑ በቅርቡ ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቶ ግንባታው ይጀመራል። የብሔራዊ ስታዲየሙ ግንባታ በቻይናው ኩባንያ ይካሄድ እንደነበረ አስታውሰው፤ ግንባታው በኮቪድ-19 ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱን ገልፀዋል። በኋላም የግንባታ ተቋራጩ ለሥራው ያቀረበው የዋጋ ማስተካከያ ከገበያ በላይ የተጋነነ በመሆኑ መንግሥት ከያዘው በጀት ጋር ሊመጣጠን አልቻለም። በዚህም ከግንባታ ተቋራጩ ጋር ያለው ውል እንዲቋረጥ መደረጉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።…
Read More
ሩሲያ ለአፍሪካ ገበያ በግብጽ የላዳ መኪና ፋብሪካ ልትገነባ መሆኗን ገለጸች

ሩሲያ ለአፍሪካ ገበያ በግብጽ የላዳ መኪና ፋብሪካ ልትገነባ መሆኗን ገለጸች

የሩሲያ ምርት የሆነው ላዳ መኪና በኢትዮጵያ እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተመራጭ ነበሩ። ለዓመታት ገበያውን ተቆጣጥረውት የቆዩት የሩሲያ ላዳ መኪኖች ቀስ በቀስ ከዓለም እና አፍሪካ ገበያዎች እየጠፉ መጥተዋል። ኩባንያው ምርቶቹን ወደ አፍሪካ ገበያዎች ማቅረብ ያቆመው ከቀዝቃዛው ጦርነት ጋር በተያያዘ የሩሲያ ተጽዕኖ እየቀነሰ በመምጣቱ እና በገበያ ውድድር ምክንያት እንደሆነ ድርጅቱ ገልጿል። ሩሲያ ወደ አፍሪካ ገበያዎች ዳግም የመመለስ ፍላጎት ማሳየቷን ተከትሎ ኩባንያው ከወራት በፊት በኢትዮጵያ እና ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ምቹ ሁኔታዎችን ተመልክቶ ተመልሷል። የኩባንያው ሀላፊዎች በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገውም ነበር። ይሁንና በፒተርስግበርግ ከየማ እየተካሄደ ባለው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ መካሄዱን ተከትሎ ኩባንያው ዋና ሙቀመጫውን ግብጽ ለማድረግ መወሰኑን…
Read More
ኢትዮጵያ ከቡና የምታገኘው ገቢ የ90 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳየ

ኢትዮጵያ ከቡና የምታገኘው ገቢ የ90 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳየ

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት ከተላከ ቡና 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች። ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው የቡና ምርት መጠን ከዓመት ዓመት ማሽቆልቆሉን የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ገልጿል፡፡ የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ግዛት ወርቁ ኢትዮጵያ በ2014 ዓ. ም ለዓለም ገበያ ያቀረበችው የቡና መጠን 302 ሺሕ ቶን ነበር። በዘንድሮው ማለትም በ2015 ዓመት ግን 240 ሺሕ ቶን ብቻ ቡና ለዓለም ገበያ ማቅረቧን የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር አስታውቋል። ወደ ውጪ ሀገራት የተላከው ቡና ከባለፈው ዓመት ለዓለም ገበያ ከቀረበው የቡና ምርት ጋር ሲንጻጸር በ62 ሺሕ ቶን ቅናሽ አሳይቷል ተብላል። ሥራ አስኪያጁ አክለውም፤ ኢትዮጵያ በዘንድሮው ዓመት ለዓለም ገበያ ካቀረበችው ቡና 1 ነጥብ 33 ቢሊዮን ዶላር…
Read More
ዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

ዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

ኢትዮጵያና የአለም ባንክ ለሰው ሀብት ልማት አገልግሎት የሚውል የ400 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት በበይነ መረብ በተካሄደ ሥነ-ስርዓት ተፈራርመዋል፡፡ በስምምነቱ ከተፈረመው 400 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 350 ሚሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ ሲሆን 50 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ብድር መሆኑ ታውቋል፡፡ የፋይናንስ ድጋፉ ለሰው ሀብት ልማት ማለትም የትምህርትን ጥራትንና ውጤታማነትን ለማሻሻልና የስርዓተ ምግብን አገልግሎት ለማጎልበት የሚውል ሲሆን፤ ከአገልግሎቱም በመላ አገሪቱ የሚገኙ ልጃገረዶችና ታዳጊ ወጣቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የሰው ሀብት ልማት አገልግሎቱ በግጭትና ድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን የሚያካትት ሲሆን፤ የማህበራዊ አገልግሎቶች አሰጣጥን ለማጠናከርና ተጠያቂነትን ለማስፈንም አስተዋጽዖ እንዳለው ተነግሯል፡፡ የፋይናንስ ድጋፉ ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋጋጥ የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ በተመረጡ ወረዳዎች የስርዓተ ምግብ አገልግሎትን…
Read More
ናይጄሪያ አውስትራሊያን በማሸነፍ በዓለም ዋንጫው ቆይታዋን አለመለመች

ናይጄሪያ አውስትራሊያን በማሸነፍ በዓለም ዋንጫው ቆይታዋን አለመለመች

ናይጄሪያ አውስትራሊያን በማሸነፍ በዓለም ዋንጫ ውድድር ያላትን ቆይታ አለምልማለች። በአውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የፊፋ ሴቶች ዓለም ዋንጫ ከተጀመረ ስምንተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል። አፍሪካ በዚህ ውድድር በናይጀሪያ፣ ዛምቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሞሮኮ ተወክላለች። ናይጀሪያ በዛሬው ዕለት ከአውስትራሊያ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ ከመመራት ተነስታ 3ለ2 ማሸነፍ ችላለች። ናይጀሪያ ማሸነፏን ተከትሎ ምድቧን በአራት ነጥብ መምራት የጀመረች ሲሆን ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ አንድ ነጥብ ብቻ በቂዋ ይሆናል። አፍሪካን በዚህ ውድድር የወከሉት ሌሎቹ ብሔራዊ ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድላቸው የመነመነ ሲሆን ሞሮኮ አስቀድማ ከውድድሩ ተሰናብታለች። የሴቶች ዓለም ዋንጫ ውድድር እስከ ነሀሴ 20 ቀን 2023 ውስጥ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ይካሄዳል። ከዚህ በፊት የሴቶች…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 90 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቀደ

ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 90 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቀደ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ የተቋሙን የ2016 በጀት ዓመት እቅድን ይፋ አድርገዋል። ስራ አስፈጻሚዋ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በተያዘው በጀት ዓመት ከአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎቶች 90 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል ብለዋል። ድርጅቱ በ2016 በጀት ዓመት 13 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት የተቋሙን አጠቃላይ ደንበኞች ቁጥር ወደ 92 ሚሊዮን የማድረስ ውጥን መያዙንም ሀላፊዋ አክለዋል። የቴሌብር ደንበኞችን ወደ 44 ነጥብ 1 ሚሊዮን፣ የሞባይል ድምጽ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ቁጥር 75 ሚሊዮን እንዲሁን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ወደ 41 ሚሊዮን ማድረስም የተቋሙ ሌላኛው ግብ ነው ተብሏል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎቶች የመጠቀም ምጣኔን ወደ 71 በመቶ ለማድረስ መታቀዱን ወይዘሪት ፍሬህይወት ገልጸዋል። የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን ከማስፋፋት…
Read More
በአዲስ አበባ 100 ሺህ ቤቶችን በአንድ ዓመት ውስጥ ለመገንባት ስምምነት ተፈረመ

በአዲስ አበባ 100 ሺህ ቤቶችን በአንድ ዓመት ውስጥ ለመገንባት ስምምነት ተፈረመ

የቤቶቹ ግንባታ በ68 የሪል ኢስቴት አልሚዎች እንደሚገነባ የተገለጸ ሲሆን መንግሥት መሬት በነጻ ለማቅረብ ተስማምቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግሥትና በግል አጋርነት ፕሮጀክት አማካይነት በመረጣቸው ሪል ስቴት አልሚዎች፣ ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ወጪ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሊካሄድ ነው ተብሏል። በዚህ ፕሮግራም ሥር እንዲሳተፉ 68 ሪል ስቴት አልሚዎችን የመረጠ ሲሆን፤ አልሚዎቹም በተቀመጠው 70/30 አጋርነት መሠረት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ተጣምረው ግንባታውን ለማካሄድ ውል መግባታቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ከእነዚህም አልሚዎች ውስጥ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ኦቪድ ግሩፕ፣ ፍሊንትስቶን ሆምስ፣ እንይ ኮንስትራክሽን፣ ጊፍት ሪል ስቴትና ሌሎችም ይገኙበታል። የከተማ አስተዳደሩ የቤቶቹን ግንባታ ለማካሄድ የሚያስፈልገውን መሬት ከሊዝ ነፃ ማቅረብና መሠረተ ልማቶችን የማሟላት ኃላፊነት አለበት ተብሏል። የሪል ስቴድ ድርጅቶች…
Read More
ኢትዮጵያ በቴሌግራም መተግበሪያ ላይ ዳግም እገዳ ጣለች

ኢትዮጵያ በቴሌግራም መተግበሪያ ላይ ዳግም እገዳ ጣለች

በኢትዮጵያ የቴሌግራም መተግበሪያ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ከዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 19 ቀን 2015ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ እየሰራ አይደለም። ገደቡ የተጣለዉ ዛሬ ከሚጀመረዉ የ 2015 ዓ.ም የ 12ኛ ክፍል ፈተና ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ይሁንና መንግሥት ለምን በቴሌግራም ላይ እገዳ እንደጣለ እስካሁን መረጃ ያልሰጠ ሲሆን መተግበሪያው በቪፒኤን እየሰራ ይገኛል። ከወራት በፊት በኦሮሚያ ክልል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አጋጥሟት የነበረዉን የመከፋፈል ድርጊትና የጳጳሳት ሹመነትን በሚመለከት በተለያዩ አካባቢዎች የተነሳዉን ተቋዉሞ ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እግዱ ተጥሎ ለአምስት ወራት መቆየቱ ይታወሳል። በዚህም መሰረት እንደ ፌስቡክ ፣ ቲክቶክ ፣ ቴሌግራም ፣ ኢንስታግራም ፣ ዩቲዩብ እና ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ሰዎች VPN ( virtual private network )…
Read More
ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ሀገራት ከተላከ የአህያ ስጋ 300 ሺህ ዶላር ማግኘቷን ገለጸች

ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ሀገራት ከተላከ የአህያ ስጋ 300 ሺህ ዶላር ማግኘቷን ገለጸች

ቻይና ዋነኛዋ የኢትዮጵያ አህያ ስጋ የተላከባት ሀገር ስትሆን ፍላጎቱ እያደገ እንደሆነም ተገልጿል። በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ የአህያ ስጋን ወደ ሆንግኮንግ በመላክ 3 መቶ ሺህ ዶላር ገቢ ማግኘቷን የእንስሳት ልማት ኢንስትቲዩት አስታውቋል፡፡ በኢንስትቲዩቱ ምክትል ዋና  ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ሳህሉ ሙሉ እንደተናገሩት፣ ከአህያ ስጋ ውጪ የአህያ ቆዳን እንደ ቻይና ያሉ ሃገራት ለመድሃኒትነት በስፋት ሲጠቀሙበት የሚስተዋል በመሆኑ የስጋ ምርቱን ወደ ሆንግኮንግ እንዲላክ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ገቢው  የተገኘውም በተጠናቀቀው በጀት አመት 140 ቶን የአህያ ስጋ ምርትን ወደ ውጪ ገበያ በመላክ እንደሆነ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ በበጀት አመቱ 600 ቶን የአህያ ስጋን ወደ ውጪ ለመላክ አስቀድሞ ታቅዶ እንደነበር ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡ በአህያ ስጋ የወጪ ንግድ  ዙሪያ የቄራ ድርጅቶች…
Read More
እስራኤል ሁለት ሺህ ቤተ እስራኤላዊያንን ከኢትዮጵያ ልትወስድ መሆኗን ገለጸች

እስራኤል ሁለት ሺህ ቤተ እስራኤላዊያንን ከኢትዮጵያ ልትወስድ መሆኗን ገለጸች

የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያኹ ለመንግስታቸዉ ከኢትዮጵያዉያን ቤተ እስራኤላውያን ማህበረሰብ ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ማጠናከር ባለባቸዉ ጉዳዮች ላይ ያቀረቡት እቅድ ጸድቋል። በዚህ እቅድ መሰረትም 2 ሺህ ቤተእስራኤላውያንን ወደ ቴልአቪቭ ለመዉሰድ ማቀዳቸዉን ጀረሰላም ፖስት ዘግቧል። እ.ኤ.አ በ 2015 የእስራኤል መንግስት 9 ሺህ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን እስራኤል መግባት የሚፈልጉ ቤተ እስራኤላውያንን ጥያቄ ከተቀበለ በኋላ ባገጠመዉ የበጀት እጥረት ማጓጓዝ ሳይችል መቅረቱ ተዘግቧል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀረበ የተባለዉ እቅድ ኢትዮጵያዊ ቤተ እስራኤላዊያንን ለማጓጓዝ 66 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተይዞለታልም ተብሏል። የሀገሪቱ መንግስት በእስራል ከሚገኙ ከ 160 ሺህ በላይ ቤተ እስራኤላውያን ዜጎች ጋር ያለዉን ግንኙነት  በማጠናከር በተለይም ወደ ሀገሪቱ የጦር ሀይል ለማካተት እቅድ እንዳለዉ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል። በተጨማሪም በእስራኤላውያን…
Read More
በጋምቤላ በተከሰተ የብሔር ግጭት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በጋምቤላ በተከሰተ የብሔር ግጭት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በጋምቤላ ክልል በአኙዋክ እና ኑዌር ብሔረሰቦች መካከል በተፈጠረዉ ግጭት እስካሁን ቁጥራቸዉ ከ30 በላይ የሆኑ ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ተናግረዋል። አቶ ኡገቱ ፤ ግጭቱ ግንቦት 13 ላይ አኙዋ እና ሊየር በሰተኙ በሁለት መንደሮች መካከል የተነሳ መሆኑን ገልጸዋል ። ግጭቱ በኋላም ወደ ብሔር ግጭት እየሰፋ የመጣ መሆኑን የተናገሩት ሀላፊው ግጭቱ በተከሰተበት ወቅትም የክልሉ መንግስት ኮማንድ ፖስት በማቋቋም ከፌዴራል የጸጥታ አካላት ጋር ሁኔታዉን ለማረጋጋት እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል። የሟቾች ቁጥር 30 ደርሷል ቢባልም በጸጥታ ግብረ ሀይሉ የተረጋገጠ አይደለም ብለዋል። ሆኖም በግጭቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከዚህ ከፍ ሊል እንደሚችል ግን ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በግጭቱ በኢታንግ ልዩ ወረዳ 4…
Read More
ሰላምዊት ዳዊት የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሀላፊ ሆነው ተሾሙ

ሰላምዊት ዳዊት የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሀላፊ ሆነው ተሾሙ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ሰላማዊት ዳዊትን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሀላፊ አድርገው ሾሙ። የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ሶስት ከፍተኛ አመራሮች ከሀላፊነት መነሳታቸው ተገልጿል። ፓስፖርት እና መሰል የዜግነት አገልግሎቶችን ለመስጠት የተቋቋመው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ተቋም ቅሬታዎች ሲቀርቡበት ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ላለፉት አንድ ዓመት ከመንፈቅ የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎትን በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ብሩህተስፋ ሙልጌታን፣ በምክትል ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የነበሩት ፍራኦል ጣፋ እና ታምሩ ግንበቶን ከኅላፊነት አንስተዋል። የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ህዝብ ግንኙነት እና ኮሙንኬሽን ሀላፊ ወይዘሮ ማስታዋል ገዳ ለአልዓይን እንዳሉት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ከሰኔ 12 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ መሾማቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ደርሶናል ብለዋል። እንዲሁም…
Read More
ድምጻዊ እጅጋየሁ ሽባባው እና የመቄዶኒያ መስራቹ የክብር ዶክትሬት ተሸለሙ

ድምጻዊ እጅጋየሁ ሽባባው እና የመቄዶኒያ መስራቹ የክብር ዶክትሬት ተሸለሙ

20 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል። በመውጫ ፈተና ምክንያት የደበዘዘው የዘንድሮው የዩንቨርሲቲዎች ፈተና የተመራቂ ተማሪዎች ቁጥርም ቀንሷል፡፡ ተማሪዎቻቸውን ካስመረቁ ዩኒቨርስቲዎች መካከል አዲስ አበባ፣ ወለጋ፣ ደብረብርሃን፣ አርባምንጭ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ እና ሰመራ፣ ወልቂጤ እንዲሁም  እንጅባራ ዩኒቨርስቲዎች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ መርሐ ግብር ያስተማራቸውን 8 ሺህ 642 ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራቹ እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡ እንዲሁም እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ለዝነኛዋ ሙዚቀኛ እጅጋየሁ ሽባባው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ መስጠቱንም አስታውቋል፡፡ ድምጻዊቷ በህመም እና በስራ ምክንያት በአካል አለመገኘቷ የተገለጸ ሲሆን እናቷ በአካል ተገኝተው የክብር ድግሪውን ተቀብለዋል፡፡ ዩንቨርሲቲዎች ባልተለመደ መልኩ ባንድ ቀን ለማስመረቅ የተገደዱት ግቢዎቻቸውን ለ2015 የ12ኛ…
Read More
ኢትዮጵያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት ጠየቀች

ኢትዮጵያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት ጠየቀች

የኢትዮጵያ መንግስት ለሁለተኛው አገር በቀል የኢኮኖሚ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር ጠይቋል፡፡ ብድሩ እና እርዳታው የተጠየቀው የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ፣ ዓለም ባንክና ኢትዮጵያ ያለባትን የውጭ ዕዳ መልሶ ከማሸጋሸግ ለማግኘት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ለሪፖርተር እንዳሉት ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከአሜሪካ፣ ፈረንሣይና ሌሎች ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት መልካም መሆኑ ብድሩ ሊገኝ ይችላል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲስተካከል ጠይቃለች ያሉት አማካሪው ብድሩ ድርድር ከተደረገበት በኋላ ይለቀቃል የሚል ተስፋ መኖሩንም ጠቅሰዋል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረስ ኢትዮጵያ ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ እ.ኤ.አ. በጁላይ ወር መጨረሻ ላይ ያነሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ፣ ይህም ገንዘቡን ለማግኘት ጥሩ እርምጃ ይሆናልም ተብሏል፡፡ 12 ቢሊዮን…
Read More
ኢትዮጵያ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ጠየቀች

ኢትዮጵያ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ጠየቀች

ኢትዮጵያ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም ግማሽ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ገለጸች የቀድሞው ተዋጊዎችን የተሃድሶ ስልጠና ሰጥቶ ወደ ህብረተሰቡ ለመቀላቀል ከ554 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽነሩ ይህን የተናገሩት ኮሚሽኑ የቀድሞው ተዋጊዎችን መልሶ በዘላቂነት በማቋቋም ረገድ የመገናኛ ብዙሃን ሚናና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ባካሄደው ውይይት ላይ ነው፡፡ የኮሚሽኑ ጽ/ቤት ሃላፊ ገመዳ አለሚ በበኩላቸው ይህ  የገንዘብ መጠን በመነሻነት የታቀደ እንደነበረ የጠቀሱት ኮሚሽነሩ አሁን ላይ ግን ከተጠቀሰው ከፍ ማለቱን ተናግረዋል ። በኢትዮጵያ 372 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች እንዳሉ የተሀድሶ ማዕከል እና የሀገር መከላከያ ሚንስቴር በጋራ ያጠኑት ጥናት ያስረዳል። የተመዘገበው አሐዝ ይህ ቢሆንም ቁጥር ሊያሻቅብ…
Read More
በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ጋዜጠኞች የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቆ ሆኖ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ተወሰነ

በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ጋዜጠኞች የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቆ ሆኖ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ተወሰነ

አራት የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች እና ሌሎች 19 ተከሳሾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረጓል። በሽብር ወንጀል የተከሰሱ አራት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ሌሎች 19 ተከሳሾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ፤ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ። የተከሳሾችን በቁጥጥር ስር መዋል በተመለከተ የጸጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ያወጣውን መግለጫ በድረ ገጻቸው የጫኑ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎቻቸውን እንዲያወርዱም ፍርድ ቤቱ አዝዟል። ይህን ትዕዛዝ የሰጠው ሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓ.ም የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ችሎት ነው። ችሎቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጎ ትዕዛዞችን በሰጠበት ቅጽበት ተከሳሾች በጭብጨባ የታጀበ መፈክር አሰምተዋል። የተከሳሾቹ መፈክር እና ጭብጨባ፤ የችሎት ውሎ…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም 76 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም 76 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

ቴሌብር የ680 ቢሊዮን ብር ግብይት መፈጸሙን ኢትዮ ቴሌኮም ገልጿል። የኢትዮ ቴሌሎም ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸምን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። ስራ አስፈጻሚዋ በመግለጫቸው እንዳሉት ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 76 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ ማግኘቱን ተናግረዋል። ከተገኘው አጠቃላይ ገቢ ውስጥም 44 በመቶው ከድምጽ ጥቅል ሲገኝ 23 በመቶው ከኢንተርኔት አገልግሎት መገኘቱን ስራ አስፈጻሚዋ አክለዋል። ተቋሙ ከውጭ ምንዛሬ አገልግሎቶች 164 ሚሊዮን ዶላር አግኝቷል ያሉት ፍሬህይወት የ4G ቴሌሎም አገልግሎት ያገኙ ከተሞች ቁጥርም ወደ 164 ከፍ ማለቱን ገልጸዋል። በአጠቃላይ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 72 ሚሊዮን ደርሷል የተባለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 34 ነጥብ 3 ሚሊዮን ያህሉ የቴሌብር ደንበኞች ናቸውም ብለዋል። በ2015 ዓ. ም…
Read More
የሴቶች ዓለም ዋንጫ ነገ ይጀመራል

የሴቶች ዓለም ዋንጫ ነገ ይጀመራል

እንደ ወንዶች የዓለም ዋንጫ ሁሉ በየ አራት አመቱ የሚካሄደው የሴቶች እግር ኳስ ዓለም ዋንጫ ነገ ይጀመራል። አውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ በጋራ የሚያስተናገዱት የ2023 የፊፋ ሴቶች ዓለም ዋንጫ አዘጋጆቹ አውስትራልያ እና ኒውዝላንድ የመክፈቻ ውድድር ጨዋታን ያደርጋሉ። ውድድሩ ከፈረንጆቹ ሀምሌ 20 እስከ ነሀሴ 20 ቀን 2023 ውስጥ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ይካሄዳል ተብሏብ። ከዚህ በፊት የሴቶች ዓለም ዋንጫ በ24 ብሔራዊ ቡድኖች አማካኝነት ይካሄድ የነበረ ሲሆን በዘንድሮው ግን ፊፋ የተሳታፊ ሀገራትን ቁጥር ወደ 32 ከፍ አድርጎታል። አፍሪካ በዚህ ውድድር ላይ በአራት ሀገራት የሚወከሉ ሲሆን ናይጀሪያ ፣ ዛምቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሞሮኮ ተሳታፊ ሀገራት ናቸው። የናይጀሪያዋ አሲሳት ኦሾላ በውድድሩ ትደምቃለች ተብሎ ከወዲሁ ትኩረት የተሰጣት ተጫዋች…
Read More
ኢትዮጵያ ለቤተሰብ እቅድ አገልግሎት የ36 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች

ኢትዮጵያ ለቤተሰብ እቅድ አገልግሎት የ36 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች

በጀቱ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል። የ36 ሚሊዮን በጀት ስምምነቱ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ የቤተሰብ ዕቅድን ተደራሽ ለማድረግ ይውላል ተብላል። በኢትዮጵያ 22 በመቶ ሴቶች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተደራሽ ያልሆነላቸው ሲሆን በጀቱ ከዚህ አንጻር ተጨማሪ ሴቶችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል። በበጀት ስምምነቱ ላይ የተገኙት የጤና ጥበቃ ሚንስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሉት የቤተሰብ እቅድ አገልግሎቱን ተደራሽነት ለማጠናከር እንቅፋት ከሆኑ ችግሮች መካከል አገልግሎቱ በነፃ የሚሰጥና ወጭው በአብዛኛው  በለጋሽ አካላት የሚሸፈን በመሆኑና ከለጋሽ አካላት የሚገኘው ድጋፍ እየቀነሰ መምጣቱ ነው ብለዋል። እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ የዋጋ ንረት በመኖሩ ለግብዓት የሚያስፈልግ የበጀት ዕጥረት ማጋጠሙን የጠቆሙት ሚንስትሯ ችግሩን በመቅረፍ አቅርቦቱን እንዳይቆራረጥ ለማድረግ  በመደበኛነት ከሚመደበው በጀት…
Read More
በኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ስራዎችን የሰሩ ሰዎች ተሸለሙ

በኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ስራዎችን የሰሩ ሰዎች ተሸለሙ

በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በርካታ የበጎ አድራጎት ስራ የሰሩ ሰዎችን ማመስገን እና ለስራቸው እውቅና መስጠት አላማው ያደረገ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ማስተር አብነት ፣ ወንድም ካሊድ ፣ሚኪያስ ለገሰ እና ዘካሪያስ ኪሮስ በኢትዮጵያ ዘር፣ ቀለም እና ሀይማኖት ሳይገድባቸው የተቸገሩ ወገኖችን ለዓመታት እየረዱ መሆናቸው በመድረኩ ላይ ተጠቅሷል። ግለሰቦቹ ለሰሩት በጎ ስራ በሽማግሌዎች ምርቃት ታጅበው የምስጋና እና የእውቅና መርሀግብር ተካሂዷል። በአዲስ አበባ ስቴይ ኢዚ ሆቴል በተካሄደው በዚህ ፕሮግራም ላይ የመንግስት አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል። ምስጋና እና እውቅና ከተሰጣቸው ሰዎች መካከልም በአዲስ አበባ በበጎ ስራቸው  የተቸገሩ ሰዎች እንዲረዱ እና ህክምና  እንዲያገኙ በማድረግ የሚታወቁት ሚኪያስ ለገሰ ( የሰሊሆም የአዕምሮ መርጃ ማዕከል)…
Read More
ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 567 ሚሊዮን ችግኞችን ተከለች

ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 567 ሚሊዮን ችግኞችን ተከለች

ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 567 ሚሊዮን ችግኞችን ተከለች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ "በአንድ ቀን 567 ሚሊዮን ችግኞች ተተክሏል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው እለት 567 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል። በአንድ ቀን 500ሺ ችግኝ የመትከል ዘመቻ አማካኝነት በሀገሪቱ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ችግኝ ሲተክሉ የሚያሳዩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ተለቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የችግኝ ተከላው" ለኢትዮጵያ ትልቅ ስኬት" ነው ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በዚህ አመት ብቻ ከካርቦን ሽያጭ 52 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቷን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የችግኝ ተከላው ስራ በዚሁ ከቀጠለ ከካርቦን ሽያጭ የምታገኘው ገቢ በእጥፍ እንደሚጨምር ገልጸዋል። ይሁንና በአንድ ጀምበር ተተከለ የተባለው የችግኝ መጠን በትክክል ስለመተከሉ በገለልታኛ አካል አልተረጋገጠም።
Read More
ቦይንግ ኩባንያ ከቲንክ ያንግ ጋር በመተባበር ለ60 ኢትዮጵያዊያን ስልጠና ሰጠ

ቦይንግ ኩባንያ ከቲንክ ያንግ ጋር በመተባበር ለ60 ኢትዮጵያዊያን ስልጠና ሰጠ

ለአራት ቀናት የተሰጠው ይህ ስልጠና ከቲንክ ያንግ እና ከአሜሪካው የአቪዬሽን ቦይንግ ኩባንያ ጋር በመተባበር ነው። ስልጠናው ከ20 ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ለ60 ተማሪዎች በአዲስ አበባ ተሰጥቷል። ከሰባት ዓመት በላይ ጀምሮ እድሜ ላላቸው የተሰጠው ይህ ስልጠና ታዳጊዎች ከቴክኖሎጂ ጋር እየተዋወቁ እንዲያድጉ በማሰብ የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል። ለታዳጊዎቹ የተሰጠው የስልጠና አይነት ዌብሳይት ማበልጸግ፣ ሮቦቲንግ፣ ኮዲንግ እና አርቲፊሻል እንተለጀንስ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። ዓለም አቀፉ የአቪዬሽን ተቋም ቦይንግ የስልጠናው አካል ሲሆን የበጀት ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል። በቦይንግ ኩባንያ የመካከለኛው ምስራቅ፣ አፍሪካ እና ተርኪየ ፕሬዝዳንት የሆኑት ኩልጅት ጋታ ስልጠናው የቦይንግ ማህበራዊ ሀላፊነት አንዱ አካል ነው ብለዋል። "የኢትዮጵያ መንግሥት ድጅታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የያዘውን እቅድ ለመደገፍ ወደ ኢትዮጵያ መጥተናል ያሉት"…
Read More
ኢትዮጵያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የጣለችውን ገደብ አነሳች

ኢትዮጵያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የጣለችውን ገደብ አነሳች

በኢትዮጽያ ለወራት ያህል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ተነስቷል። በኢትዮጵያ ከየካቲት ወር መጀመሪያ አንስቶ በኢንተርኔት አገልግሎቶች ማለትም በፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ቴሌግራም እና ቲክቶክ ላይ ገደብ መጣሉ ይታወሳል። በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ገደብ መጣሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ በርካታ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች መንግሥት ገደቡን እንዲያነሳ ሲጠየቅ ቆይቷል። በኢንተርኔት እገዳው ምክንያትም ኢትዮጵያ 7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ ማጣቷን የመብቶችና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል ገልጿል፡፡ “ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶችን ተከትሎ፤ ከ2008 ወዲህ የበይነመረብ ግንኙነትን ማቋረጥ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣ ችግር ነው” ያለው ማዕከሉ፤ የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጡ የዴሞክራሲና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገት ጸር መሆኑን አመላክቷል፡፡ መንግሥት ዋና ዋና የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች በኢትዮጵያ እንዳይጎበኙ እገዳ መጣሉ ሕጋዊ መሰረት…
Read More
ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለማችን ቀዳሚ ተከፋይ ስፖርተኛ ሆነ

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለማችን ቀዳሚ ተከፋይ ስፖርተኛ ሆነ

የአልናስር አጥቂ የሆነው ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልድ የ2023 ከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኛ ሆኖ ተመዝግቧል። እንደ ፎርብስ ዘገባ ከሆነ የአምስት ጊዜ ባሎንዶር ተሸላሚው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በተያዘው ዓመት ብቻ 136 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል። የዓለም ዋንጫ አሸናፊው አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ በ2022 ዓመት 130 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ተከፍሎታል። ክርስቲያኖ ካገኘው የ136 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ውስጥ 90 ሚሊዮን ዶላሩን ከሜዳ ውጪ ማለትም ከማስታወቂያ እና ስፖንሰር ስራዎች ማግኘቱ ተገልጿል። በማንችስተር ዩናይትድን ባለ መግባባት ወደ ሳውዲ አረቢያው አልናስር ያመራው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ደመወዙ እጥፍ እንዳደገለትም ተገልጿል። በአጠቃላይ በስፖርቱ ዘርፍ ሊዮኔል ሜሲ እና ክሊያን ምባፔ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ በመቀጠል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዱረጃን ይዘዋል። የቅርጫት ኳስ ኮኮቡ ለቦርን 119 ሚሊዮን…
Read More
አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት እንዲሰጣት ተወሰነ

አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት እንዲሰጣት ተወሰነ

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሊሰጣት መወሰኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሐምሌ 13/2015 እንደሚያስመርቅ የገለጹት ፕሬዘዳንቱ፤ በዕለቱ ለተወዳጇ አርቲስት እጅጋየው ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ድምፃዊት፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ተዋናይት የሆነችው ሁለገቧ አርቲስት ጂጂ፣ የአገሯን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነጥበብ የአዊን ህዝብ ቋንቋ እና ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ የክብር ዶክትሬቱ እንደሚበረከትላት ነው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት መግለጻቸውን ከዩንቨርስቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ለጂጂ የሚሰጠውን የክብር ዶክትሬት እና የተማሪዎቹን የምርቃት ሥነስርዓት በማስመልከት ረቡዕ ማለትም ሐምሌ 12/2015 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ለመገናኛ ብዙሀን ዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጥም ፕሬዘዳንቱ ገልጸዋል። ከሰሞኑ ለ15ተኛ ጊዜ በተካሄደዉ የአማራ…
Read More
ኢትዮጵያ ኤርትራዊያንን ከማፈናቀል እንድትታቀብ ተመድ ጠየቀ

ኢትዮጵያ ኤርትራዊያንን ከማፈናቀል እንድትታቀብ ተመድ ጠየቀ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢትዮጵያ በሰኔ ወር መጨረሻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያንን አፈናቀላለች ሲል ገልጿል፡፡ ተመድ ኢትዮጵያ  የኤርትራ ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን፤ የስደተኞችን ሕግን በመጣስ እንዲሁም ክስ ሳይኖርባቸው በዘፈቀደ የማሰር እና የማፈናቀል ተግባሯን በአስቸኳይ እንደታቆም ነው ያሳሰበው። ድርጅቱ ወደ ሌላ አገር ጥገኝነት ጠይቀው የገቡ ስደተኞችን በጅምላ ማባረርና በዘፈቀደ ማሰር በዓለም አቀፍ ሕግ የተከለከለ ነው ሲልም ገልጿል፡፡ በዚህም የመንግሥታቱ ድርጅት ኢትዮጵያ እያደረገችው ያለውን ጥገኝነት ጠያቂዎችን የማሰቃየት፤ በግዳጅ የማፈናቅልና የሰብአዊ መብት ረገጣ አውግዟል። ኢትዮጵያ በሱዳን ጥገኝነት ጠይቀው ሲኖሩ የነበሩና በጦርነቱ ምክንያት ወደ አገሪቷ የገቡ ኤርትራውያን ላይ ጭካኔ የተሞላበት ኢ-ሰብአዊ አያያዝ እየተፈጸመች ነው የተባለ ሲሆን፤ ይህም ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ስምምነቶችን ሙሉ ለሙሉ የጣሰ ድርጊት…
Read More