Amharic

የሞስኮ ትምህርት ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት አማርኛ እና ስዋህሊ ቋንቋን ማስተማር እንደሚጀምሩ ገለጹ

የሞስኮ ትምህርት ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት አማርኛ እና ስዋህሊ ቋንቋን ማስተማር እንደሚጀምሩ ገለጹ

ሩሲያ ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ከመስከረም ወር ጀምሮ አማርኛ እና ስህዋህሊ ቋንቋዎችን በሞስኮ በሚገኙ በአራት ትምህርተ ቤቶች ማስተማር እንደምትጀምር ገልጻ ነበር። በዚህም መሰረት ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መስከረም በሞስኮ የሚገኙ ትምህ ቤቶች የአፍሪካ ቋንቋዎችን ማስተማር ይጀመራል ሲል የሞስኮ ትምህርት እና ሳይንስ ክፍል አስታውቋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ 1517 የተሰኘው የፔዳጎጂ ትምህርት ቤት ስዋህሊ ቋንቋን ሁለተኛው የውጭ ቋንቋ አድርጎ ያስተምራል ተብሏል። እንዲሁም 1522 የተሰኘው ትምህርት ቤት ደግሞ አማርኛ ቋንቋን እንደሚያስተምር ተገልጿል። ሩሲያ የአፍሪካ እና ሞስኮን ወዳጅነት ለማጠናከር በሳምንት አንድ ወይም ሁለት የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ለአፍሪካ ቋንቋዎች ማስተማሪያ እንዲውሉ ይደረጋል ብላለች። ሩሲያ በቀጣይም በምዕራብ አፍሪካ ሰፊ ተናጋሪ ያለው ዩርባ ቋንቋን ማስተማር…
Read More
ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ

ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ

ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ የዓለማችን ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ እና ብዙ ህዝብ ያላቸው ሩሲያ እና ቻይና የኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ የሆነው አማርኛ ቋንቋ ለዜጎቻቸው እንዲሰጥ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ሩሲያ ከቀጣዩ መስከረም ወር ጀምሮ በሞስኮ በሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጻለች፡፡ ትምህርቱ ከቀጣዩ መስከረም 2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል የተባለ ሲሆን በሳምንት ሁለት ክፍለ ጊዜ እንደሚሰጥ በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ገልጸዋል፡፡ ሌላኛዋ አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቿ ለማስተማር የወሰነችው ሀገር ቻይና ስትሆን ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ይሆናል ተብሏል፡፡ ለዚህ እንዲረዳም አማርኛን ለቻይናዊያን ተማሪዎች ለማስተማር የሚያግዘው መጽሀፍ በቤጂንግ…
Read More
ኢትዮጵያ ከጦርነት ውድመት ለማገገም 20 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል ተባለ

ኢትዮጵያ ከጦርነት ውድመት ለማገገም 20 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል ተባለ

ኢትዮጵያ በጦርነት ከደረሰባት ውድመት ለማገገም 20 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል ተባለ በኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በፊት ህወሀት በሀገር መከላከያ የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነበር ጦርነት የተነሳው። በዚህ ጦርነት ምክንያት 800 000 ዜጎች ህይወታቸው እንዳለፈ ሲገለጽ የግለሰቦች እና የመንግስት መሰረተ ልማቶች ወድመዋል። ጦርነቱ አሁን ላይ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የሰላም ስምምነት ተፈርሞ ጦርነቱ ቆሟል። ይህ ለሁለት ዓመት የዘለቀው ጦርነት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን እና ሌሎች ሀብቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ 20 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የፋይናንስ ሚንስቴር ገልጿል። ጦርነቱ ክፉኛ የጎዳቸው ትግራይ ፣አማራ እና አፋር ክልሎች በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ከደረሰባቸው ጉዳት እንዲያገግሙ 20 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋልም ተብሏል። ይህ የመልሶ ግንባታ በጀት ከፌደራል መንግሥት ፣ ዓለም…
Read More