መነሻ ገፅ

ሄኒከን ቢራ ፋብሪካ ከግል ድርጅቶች ቁጥር አንድ ግብር ከፋይ ኩባንያ ተባለ

ሄኒከን ቢራ ፋብሪካ ከግል ድርጅቶች ቁጥር አንድ ግብር ከፋይ ኩባንያ ተባለ

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ውስጥ 1.5 ትሪሊዮን ብር ከግብር የሰበሰበች ሲሆን ከግል ድርጅቶች ሄኒከን ቢራ ቁጥር አንድ ግብር ከፋይ ተቋም ሆኗል። ከአራት በላይ የቢራ ብራንዶችን ለኢትዮጵያ ገበያ በማምረት ላይ ያለው የጀርመኑ ሄኒከን ኩባንያ 26 ቢሊዮን ብር እንደከፈለ ተገልጿል። ሄኒከን እንደሀገር ከፍተኛ ግብር ከሚከፍሉ ተቋማት መካከል በአራተ ደረጃ ላይ ስሙ ተጠቅሷል። በዚህ በጀት ዓመት ለመንግስት 10 ከፍተኛ ግብር ከፋይ ድርጅቶች መካከል 7ቱ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ናቸው።ኢትዮ ቴሌኮም 66  ቢሊዮን ብር  በመክፈል እንደ ሀገር ቁጥር አንድ ግብር ከፋይ ተቋም ነው። ሁለተኛው ግብር ከፋይ ተቋም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆን ከፈለው 37 ቢሊዮን ብር ሲከፍል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ 31 ቢሊዮን ብር እንደከፈለ…
Read More
የቱርኩ ኬአርሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ የአሳንስር ፋብሪካ ለመክፈት ተስማማ

የቱርኩ ኬአርሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ የአሳንስር ፋብሪካ ለመክፈት ተስማማ

በኢትዮጵያ 10 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፍ የአሳንሰር ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት የሚያስችል የጋራ ኢንቨስትመንት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስምምነት ተፈርሟል። ስምምነቱን የተፈራረሙት ሀገር በቀሉ ሞናጎ ኢሊቬተር እና የቱርኩ ኬ አር ሲ ኢሊቬተር መሆናቸው ተገልጿል። ሁለቱ ኩባንያዎች ላለፉት 5 ዓመታት በዘርፉ አብረው ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ በዱከም ከተማ ማምረቻ ፋብሪካ በጋራ ለመገንባት የሚያስችላቸውን ስምምነት ፈጽመዋል። የ"ሞናጎ" ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋሁን ኢሳያስ እንዳስታወቁት፣ ፕሮጀክቱ በዋናነት በሀገሪቱ በሚገኙ ህንጻዎች ላይ የሚታየውን የአሳንሰር ጥገና እና የመለዋወጫ አቅርቦት እጥረት ለመፍታት ያለመ ነው። በጨረታ የሚገዙ አሳንሰሮች ከሽያጭ በኋላ በቂ የጥገና አገልግሎት እና የመለዋወጫ አቅርቦት ስለማያገኙ በተደጋጋሚ ብልሽት እንደሚያጋጥማቸው ተመላክቷል። አዲሱ ስምምነት ይህንን ክፍተት እንደሚሞላው የጠቆሙት…
Read More
ሰባት የክሪፕቶከረንሲ ድርጅቶች መተግበሪያ በኢትዮጵያ እንዳይሰሩ ታገዱ

ሰባት የክሪፕቶከረንሲ ድርጅቶች መተግበሪያ በኢትዮጵያ እንዳይሰሩ ታገዱ

መንግሥት፣ ለሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ሽፋን ይሠጡ የነበሩ ሰባት የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ማገዱን አስታውቋል። ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ሽፋን ይሰጡ ነበሩ የተባሉ 7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች ሙሉ በሙሉ መታገዳቸውን የመንግስት ኮሙንኬሽን ሚንስትር እናታለም መለሰ ተናግረዋል። ስማቸው ያልተጠቀሱት እና የታገዱት እነዚህን መተግበሪያዎች በመጠቅም ዜጎች ገንዘባቸውን እንዲበሉ፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንዲደረግ ሲያደርጉ እንደነበር ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የትኛውም የምናባዊ መገበያያ መንገዶች መከክልከላቸውን በተደጋጋሚ ሲናገር ቆይቷል። ከዚህ በተጨማሪም መሰረታቸውን በኢትዮጵያ ላደረጉ 36 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ጋር ሕገ-ወጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ውል የፈጸሙ አራት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ አመራሮች መታሰራቸውም ተገልጿል። እንዲሁም ምርት ልከው የውጭ ምንዛሬ ተመላሽ ያላደረጉ 29 ላኪ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ…
Read More
በኢትዮጵያ ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሙስናን አስመልክቶ ያለውን ግንዛቤ የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ፣ የመሬትና የገቢዎች ተቋማትን ጨምሮ በበርካታ ተቋማት ውስጥ ሙስና አሳሳቢ መሆኑን ማረጋገጡን አስታውቋል። የመሬት አስተዳደርና የይዞታ ምዝገባ፣ የገቢዎችና ታክስ ጽሕፈት ቤቶች፣ የኮንስትራክሽን ፈቃድ ቁጥጥር፣ የንግድና ትራንስፖርት ቢሮዎች፣ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደሮች በከፍተኛ ደረጃ ለሙስና ተጋላጭ መሆናቸው በጥናቱ ተለይቷል ብሏል፡፡ ኮሚሽኑ ለዳሰሳ ጥናት በተወሰደ ናሙና ከ60 በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ሙስና በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ተግባራት ከፍተኛ እንቅፋትና ችግር የፈጠረ አሳሳቢ ችግር መሆኑን እንደነገሩት ገልጿል፡፡ በአቋራጭ የመበልፀግ ፍላጎት፣ የሥነ ምግባር ጉድለት፣ ውስብስብና ግልጽ ያልሆኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ሒደቶችና የሕግ ማስከበር ድክመቶች ለሙስና መስፋፋት ዋነኛውንና ቀዳሚውን ድርሻ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ የጥናት ሪፖርት ያመለክታል፡፡ በጥናቱ…
Read More
ከደላሎች ውጪ ሰራተኞችን ከቀጣሪዎች ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ መተግበሪያ ተዘጋጀ

ከደላሎች ውጪ ሰራተኞችን ከቀጣሪዎች ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ መተግበሪያ ተዘጋጀ

የቤት ውስጥ ሰራተኛን ጨምሮ የግል አገልግሎት ሰራተኞች እና አሰሪዎችን የሚያገናኝ፣ ደላላን የሚተካ መተግበሪያ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። የግል አገልግሎት ቅጥር የሚባሉትን እንደ አትክልተኛ፣ የቤት ውስጥ ተንከባካቢ፣ የቤት ውስጥ አብሳይ (ሼፍ) እና ሌሎችም ዘርፎች የቅጥር ግንኙነት ከደላላ ጣልቃ-ገብነት የሚያላቅቅ መተግበሪያ እና አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ እንደሆነ ተገለጸ። ዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ኮንቬንሽን 189ን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀው ደንብ ለፍትሕ ሚኒስቴር መቅረቡን እና በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል። አንድ ዓመት አካባቢ ለሚፈጅ ጊዜ ግብዓት በማሰባሰብ እና ባለድርሻ አካላትን በማወያየት የተዘጋጀው ደንብ፣ የቤት ሠራተኞች መመዝገቢያ ሶፍትዌር ሲስተም እንዲኖረው የሚያስችል መተግበሪያ እየተዘጋጀለት እንደሆነ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ…
Read More
ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 805 ሚሊዮን ችግኞች መትከሏን አስታወቀች

ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 805 ሚሊዮን ችግኞች መትከሏን አስታወቀች

መንግሥት "የአረንጓዴ አሻራ" በሚል ፕሮግራም በአንድ ቀን 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻ ዛሬ አካሂዳለች። በዚህ ችግኝ የመትከል ዘመቻ "805 ነጥብ 3 ሚሊዮን" ችግኞችን በመትከል ታላቁን ሀገራዊ እቅድ በላቀ ስኬት ማጠናቀቋን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳውቀዋል።  በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ተሳትፈውበታል በተባለው በዚህ መርሃ ግብር ሀገሪቱ በአንድ ቀን ከዚህ በፊት ተይዞ የነበረውን የ700 ሚሊዮን ችግኝ መትከል ሪከርድን እንዳሻሻለች ተገልጿል። የመንግሥት ኮሙንኬሽን ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የተራቆቱ አካባቢዎች በልጆቿ ብርቱ እጆች እንዲታከሙ፣ እየተስፋፋ የመጣው ድርቅና በረሃማነት በዘላቂነት እንዲገታ እና በአስተማማኝ መሠረት ላይ የተገነባ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እውን እንዲሆን ግልጽና ጽኑ አቋም መያዙን ገልጿል። ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ በአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን…
Read More
የባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ከ157 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ገለጸ

የባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ከ157 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ገለጸ

በመካከለኛው ምስራቅ እና በቀይ ባህር ዙሪያ ያለው ጦርነትና ውጥረት ለስራው ፈተና እንደነበር፣ የነዳጅ እጥረትም እንደልብ ለመንቀሳቀስ መቸገርን ጨምሮ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ፈተና እንደነበሩ አስረድቷል። የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ በተመለከተ ዛሬ ከሰዓት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው ዓመቱ ለዘርፉ ፈታኝና ከባድ ጊዜ ቢሆንም በብዙ መለኪያዎች ግን የተሻለ ሊባል የሚችል ስራ የተሰራበት እንደነበር ጠቁመዋል። በበጀት ዓመቱ ተቋሙ በአጠቃላይ ከ7 ሚሊዮን በላይ ሜትሪክ ቶን ጭነት ማጓጓዝ መቻሉን የተናገሩት ሀላፊው ከዚህ ውስጥ 5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶኑ ከኮንቴይነር ውጪ የሆነ ጭነት፣ 2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶኑ ደግሞ የኮንቴይነር ጭነት እንደሆነ…
Read More
ኢትዮጵያዊያንን በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲልክ የነበረው ተጠርጣሪ በኢንተርፖል አማካኝነት ተያዘ

ኢትዮጵያዊያንን በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲልክ የነበረው ተጠርጣሪ በኢንተርፖል አማካኝነት ተያዘ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖልና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ አድነው ባሻው ውዳሞን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገልጿል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል እና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር በበርካታ የሀገራችን ወጣቶች ላይ ከባድ ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጽም የቆየውን አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ አድነው ባሻው ውዳሞን በማላዊ ሀገር በቁጥጥር ሥር እንዲውል በማድረግ ለኢትዮጵያ ተላልፎ መሰጠቱን አስታውቋል። አድነው ባሻው ውዳሞ በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለይም ከሀድያ እና ከንባታ ዞኖች በርካታ ወጣቶችን ሕይወት እንደሚያሻሽል በመሐላና በአጉል ተስፋ በማታለል በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያዘዋውር መቆየቱን ፖሊስ በሰውና በሰነድ ማስረጃ አረጋግጫለሁ ብሏል። ተጠርጣሪው ከእያንዳንዱ ተጓዥ ከ600 ሺህ እስከ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ9 ቢሊዮን በላይ ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ9 ቢሊዮን በላይ ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2025/2026 በጀት ዓመት የዓለም አቀፍ ፈተናዎችንና የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን በመቋቋም 9.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል። አየር መንገዱ በዓመቱ 20.7 ሚሊዮን ደንበኞችን በማጓጓዝ የ10 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን፣ የጭነት አቪየሽን አገልግሎቱም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ16 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ​የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ፣ በበጀት ዓመቱ አራት አዳዲስ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን በመጨመር አጠቃላይ የመዳረሻዎችን ቁጥር 150 ማድረሱን ገልጸዋል። በተጨማሪም የሀገር ውስጥ መዳረሻዎችን ከ22 ወደ 25 ከፍ በማድረግ የአየር መንገዱን ተደራሽነት ማስፋፋት ተችሏልም ብለዋል። የበረራ አቅምን ለማጠናከርም ዘጠኝ አዳዲስ አውሮፕላኖች በግዢና በኪራይ ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፣ ለኢትዮጵያ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲ ስልጠና የሚውሉ ስምንት…
Read More
የሮቦቲክ ሰርጀሪ ህክምና መስጠት የሚያስችል ማሰልጠኛ በአዲስ አበባ ተከፈተ

የሮቦቲክ ሰርጀሪ ህክምና መስጠት የሚያስችል ማሰልጠኛ በአዲስ አበባ ተከፈተ

ማሰልጠኛ ማዕከሉ የተከፈተው በቻይና እና አፍሪካ የህክምና አጋርነት አማካኝነት ሲሆን ዘመናዊ የሮቦቲክስ ሰርጀሪ ህክምናን በኢትዮጵያ እና ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማስፋፋት ያለመእንደሆነ ተገልጿል።​በቻይና እና አፍሪካ ትብብር ለአህጉሪቱ የጤና ዘርፍ ማዘመኛ የሚሆን አዲስ የህክምና አጋርነት ፕሮግራም በአዲስ አበባ ሲልከ ሮድ ጄነራል ሆስፒታል ተመርቋል። ሲልክሮድ ሆስፒታል በቻይናዊያን ከአምስት ዓመት በፊት የተቋቋመ ዘመናዊ ሆስፒታል ነው። ​በዕለቱ የሮቦቲክስ ሰርጀሪ እና የኢንዶስኮፒክ ቴክኖሎጂ ማሰልጠኛ ማዕከላት የተከፈቱ ሲሆን፣ ኘሮግራሙ አነስተኛ ቀዶ ጥገና ቴክኖሎጂን በስፋት ለማስፋፋት ያለመ ነው። ​በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ የዘመናዊ ቴክኖሎጂና የሰለጠነ የሰው ኃይል አስፈላጊነትን ገልጸው፣ የቻይና ባለሙያዎች የሚያደርጉትን የዕውቀትና ክህሎት ሽግግርን አድንቀዋል። ​የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና በኢትዮጵያ የቻይና…
Read More