22
Sep
በኢትዮጵያ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠውን የበይነ-መረብ ትምህርት ለማጠናከር የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ /AI) ቴክኖሎጂን ለመጠቀም የሚያስችል ሀገር አቀፍ እና ተቋማዊ ፖሊሲ በመዘጋጀት ላይ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። በሚኒስቴሩ የበይነ-መረብ ትምህርት ማጠናከር ፕሮግራም የክትትል፣ ግምገማ እና ትምህርት ዋና አማካሪ ዶክተር ጌታሁን መኮንን እንደተናገሩት፤ ቴክኖሎጂው በዘመናዊው የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ አለው። ሆኖም አጠቃቀሙ በግልጽ መመሪያ እና ደረጃ ካልተመራ ክፍተቶችን ሊፈጥር እንደሚችል ጠቁመዋል። በተለይም በተማሪዎች ምዘና ወቅት የሚቀርቡ ሥራዎች በተማሪዎቹ ጥረት የተከናወኑ መሆናቸውን ለማረጋገጥና አሉታዊ ተጽዕኖውን ለመከላከል ጥብቅ ቁጥጥር ያስፈልጋል ተብሏል። አሰራሩ ከተቋም እስከ ግለሰብ የሥነ-ምግባር ደንቦችን ተከተሎ ሥራ ላይ መዋል እንዳለበትና ቴክኖሎጂውን ጨርሶ አለመጠቀም ወይም ልቅ ማድረግ ተገቢ…