22
Apr
በኮንትሮባንድ ንግድ የተሳተፋ ከ50 በላይ የቡና ላኪዎች እገዳ ተጣሎባቸዋል። የቡና ምርት ለኮንትሮባንድና ለተለያዩ ህገወጥ ድርጊቶች እየተጋለጠ በመሆኑ የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት እየጎዳው ይገኛል ሲል የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል። የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር እንደተናገሩት ቡናን ለአልባሌ ነገር እንዳይውል ለማድረግ በሶፍት ዌር አማካኝነት እያንዳንዱ ምርት ከመነሻ እስከ መድረሻ መድረሱን ለማረጋገጥ የሚያስችል የቁጥጥር ስራ እየተከናወነ ይገኛል። ይህም በተለይም ቡናን በአግባቡ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀው ምርቱን ለኮንትሮባንድ ንግድ የሚያውሉ አካላት ላይ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በዚህም መሰረት ቡናን ወደ ትክክለኛው መዳረሻ እንዲደርስ ባላደረጉት አካላት ላይ ከአስተዳደራዊ እርምጃ አንስቶ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል። በህገወጥ መልኩ ቡናን እየደበቁ ያሉትን በተመለከተ…