10
Oct
በ2010 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ነበር ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለ20 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት ያደሱት፡፡ ሁለቱ ሀገራት የመደበኛ የስልክ አገልግሎትን ዳግም ካስጀመሩ ከሰባት ዓመታት በኋላ ተቋርጧል፡፡ ይህን ተከትሎም ከሐምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ የስልክ አገልግሎት ሲሰራ የነበረ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ማለትም ከመስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደተቋረጠ በኢትዮጵያ ከሚኖሩ ኤርትራዊያን ሰምተናል፡፡ ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራዊ ለአል-ዐይን እንዳሉት “ከማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መደበኛ ስልክ መደወል አልቻልኩም” ብለዋል፡፡ በኤርትራ ኢንተርኔት አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት ቤተሰቦቻችንን የምናገኘው በመደበኛ ስልክ ብቻ ነበር የሚሉት እኝህ አስተያየት ሰጩ አገልግሎቱ መቋረጡ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡ “ቀስ በቀስ የኢትዮጵያ እና…