19
Feb
ኤርትራ በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ለቀረበባት ክስ ምላሽ ሰጥታለች። የሀገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በኤክስ ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የተነሱትን ነጥቦች አጣጥለዋል። ሙላቱ ከሁለት ቀናት በፊት አልጀዚራ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ "የኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት ለመቀስቀስ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ በምስራቅ አፍሪካ አዲስ ግጭት እንዳይከፈት ለማስቆም ጊዜው አሁን ነው" ማለታቸው ይታወሳል። "ጦርነት የኤርትራ መንግስት ዋናኛ ቢዝነስ ነው" የሚሉት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ባለፉት 30 ዓመታት በተለያዩ ድንበር ተሻጋሪ ግጭቶች መሳተፋቸውን በጽሁፋቸው አብራርተዋል። የትግራዩን ጦርነት "እንደ እድል በመጠቀም"ም ወታደሮቻቸውን ወደ ክልሉ አስገብተው "ውድመት" ማስከተላቸውን በመጥቀስ፥ ጦርነቱን ያስቆመው የፕሪቶሪያ ስምምነት ግን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ "መሰናክል" ፈጥሯል ሲሉም ያትታሉ።…