Election2026

ምርጫ ቦርድ 22 ምርጫ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን ገለጸ

ምርጫ ቦርድ 22 ምርጫ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን ገለጸ

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮችን ምዝገባ እንዲያከናውኑ ከተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች መካከል 22ቱ ህገወጥ ድርጊት በመፈጸማቸው ምክንያት መዘጋታቸውን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ለ45 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁን አስመልክቶ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ሀይሉ በሰጡት መግለጫ የመራጮች ምዝገባ 50 ሚሊዮን ማለፉን ተናግረዋል፡፡ የተዘጉት የምርጫ ጣቢያዎች ተመሳሳይ መራጭ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያ ላይ ተመሳሳይ ፊርማ የተገኙባቸውም አሉ ብሏል።  ቦርዱ መስራት የሚጠበቅባቸውን ስራ ወደ ጎን በመተው ህግን ያላከበረ አሰራር መከተላቸውንም አመልክቷል። በተመሳሳይ እንዲህ ዓይነት ድርጊት ላይ የተሳተፉ የምርጫ አስፈፃሚዎችም ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል። ቦርዱ እርምጃ እንደወሰደ ቢገልጽም በምን ያህሎቹ ላይ እንደወሰደ ግን ያለው ነገር የለም።  ቦርዱ ከዚህ ቀደም በደመወዝ እና በተለያዩ ጉዳዮች…
Read More
ምርጫ ቦርድ ዜጎችን አስገድዶ የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ መደረጉን ወቀሰ

ምርጫ ቦርድ ዜጎችን አስገድዶ የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ መደረጉን ወቀሰ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፊታችን ግንቦት ሊካሄድ ስለታሰበው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት አካል የሆነው የምርጫ ምዝገባ ሂደት ላይ እየደረሱ ያሉ ተገቢ ያልሆኑ ተጽዕኖዎች እና ጣልቃ ገብነቶችን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። ቦርዱ በመግለጫው እንደጠቀሰው በክልል መንግሥታት እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ስር ባሉ አስፈጻሚዎች አማካኝነት ቤት ለቤት በመሄድ " ተመዝገቡ " የሚል ቅስቀሳ እየተደረገ መሆኑን ደርሼበታለሁ ብሏል። የምርጫ ካርድ መውሰድን እንደ ግዴታ በመቁጠር ጫና መፍጠር፣ የመራጭነት ምዝገባን ከማህበራዊ አገልግሎቶች ጋር ማያያዝ፣ እንዲሁም " የመራጭነት ካርድ ካልወሰዳችሁ ደመወዛችሁ ይቆረጣል " በማለት በሠራተኞች ላይ ተጽዕኖ የማሳደርና ከሥራ እንደሚያሰናብቱ በመግለጽ የማስፈራራት ድርጊቶች እየተፈጸሙ እንደሆነም ቦርዱ አስታውቋል። ማንኛውም አካል በየቤቱ በመሄድ "ተመዝገቡ" ማለት ወይም በየመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞችን…
Read More
የብልጽግና ፓርቲ ከነጋዴው ማህበረሰብ በአስገዳጅነት ገንዘብ መሰብሰቡን እንዲያቆም ተጠየቀ

የብልጽግና ፓርቲ ከነጋዴው ማህበረሰብ በአስገዳጅነት ገንዘብ መሰብሰቡን እንዲያቆም ተጠየቀ

ለሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በምርጫው የሚሳተፍ ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ ፓርቲዎች በምርጫው ላይ ጉልህ ተሳትፎ ለማድረግ የድርሻቸውን ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ። ከዝግጅቶቻቸው መካከልም ዋነኛው ለምርጫው የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ እና ሀብት ከአባላቶቻቸው እና ከደጋፊዎቻቸው በተቀመጠው የህግ አግባብ መሰረት ማሰባሰብ አንዱ መሆኑን ኢዜማ ገልጿል። ይህ የገንዘብ እና ቁሳቁስ ማሰባሰብ ሂደት የአገሪቱን የፋይናንስ አሰራር ስረዓት እንዲሁም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓለቲካ ፓርቲዎች የሀብት አሰባሰብን በተመለከተ ያስቀመጣቸውን ጥብቅ የህግ ድንጋጌዎች ባከበረ መልኩ መሆን እንዳለበትም ፓርቲው አስታውቋል። ኢዜማ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ብልፅግና ፓርቲ የህግ ድንጋጌዎች በጣሰ መልኩ በማንአለብኝነት መንፈስ ከፍተኛ ገንዘብ አባል ካልሆኑ ነጋዴዎች እና ባለሀብቶች በግዳጅ እያሰባሰበ እንደሆነ ደርሼበታለሁ ብሏል። "16 ሚሊዮን አባል አለኝ የሚለው ብልፅግና…
Read More
ራያ እና ወልቃይት አካባቢ ከትግራይ ክልል ውጪ ሆነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድ ተወሰነ

ራያ እና ወልቃይት አካባቢ ከትግራይ ክልል ውጪ ሆነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድ ተወሰነ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱባቸው አካባቢዎች ምርጫ እንዲካሄው ውስኗል ተብሏል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ የካቲት 16፣ 2018 ባወጣው መግለጫ ከዚህ በፊት በትግራይ ክልል ስር ሆነው ምርጫ ሲካሄድባቸው የነበሩ ምርጫ ክልሎች ከክልሉ መንግስት ውጪ ሆነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድባቸው መወሰኑን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሰው ገልጿል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቻ ይካሄድባቸዋል ተብለው በቦርዱ መግለጫ ላይ የተጠቀሱት ምርጫ ክልሎች ሁመራ፣ አዲረመጽ፣ ኮረምኦፍላ ፣ ጠለምት እና ራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች እንደሆኑም ቦርዱ አስታውቋል፡፡ ቦርዱ አክሎም የክልል ምክር ቤት ምርጫ በአካባቢዎቹ ላይ የተነሳባው የይገባኛል ውዝግብ ጥያቄ በህገ መንግስት ውሳኔ መሰረት ሲፈታ እንደሚካሄድ ቦርዱ አስታውቋል።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር በበኩሉ…
Read More
የምርጫ ቦርድ አዲስ አሰራር ተፅዕኖ እንደሚፈጥርባቸዉ ፓርቲዎች አስታወቁ

የምርጫ ቦርድ አዲስ አሰራር ተፅዕኖ እንደሚፈጥርባቸዉ ፓርቲዎች አስታወቁ

ስምንት የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ የዘረጋው አዲስ አሰራር በቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ ተጽዕኖ እንደሚፈጥርባቸው አስታውቀዋል። የቦርዱን አዲስ አሰራር የተቃወሙ ፓርቲዎች የህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ  ፓርቲ (ህብር ኢትዮጵያ)፣ መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ( ባልደራስ) ትብብር ለኢትዮጵያ  አንድነት ፓርቲ፣ለኢትዮጵያ አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ)፣የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ)፣የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) ፓርቲዎች ናቸው። በዚህ በጋራ መግለጫቸው የሀገሪቱ አቅም ባልፈቀደበትና እንደ ሀገር  ግንዛቤ በሌለበት ቴክኖሎጂካል አሰራር  ለመስፈርትነት መጠቀም አግባብነት የለውም ብለዋል። አካል ጉዳተኞች ከሁለት ሆስፒታሎች ማስረጃ እንዲያቀርቡ ግዴታ መቀመጡ፣ የአገሪቱን ገጠር አካባቢዎች ያላገናዘበና ሆስፒታሎች በሌሉበት ማስረጃ  መጠየቅ የአካል ጉዳተኞች ነባራዊ ሁኔታ የሚዳሰስና የሚታይ ሆኖ ሳለ ማስረጃ መጠየቁ በራሱ…
Read More
የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 24 እንዲሆን ቀረበ

የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 24 እንዲሆን ቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ፤ በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለማድረግ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል። የምርጫ ውጤት ለህዝብ ማሳወቂያ ቀን ደግሞ ሰኔ 3 ቀን እንደሚሆንም ቦርዱ አስታውቋል። ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ የሚገኘው ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ በምርጫው የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አድርጓል። ከ60 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች በተሳተፉበት በዚህ ውይይት ላይ በምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ላይ የጦፈ ውይይት መደረጉ ተገልጿል። መገናኛ ብዙሃን ባልተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ፤ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳን ለፓርቲዎች ለውይይት አቅርቧል። ለውይይት በቀረበው የጊዜ ሰሌዳው መሰረትም ህዳር ወር ውስጥ በምርጫ መወዳደር የሚፈልጉ…
Read More
አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ብልጽግና ፓርቲን ለማሸነፍ ህብረት ፈጠሩ

አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ብልጽግና ፓርቲን ለማሸነፍ ህብረት ፈጠሩ

ፓርቲዎቹ "ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት" የተሰኘ የቅንጅት ፖርቲ መመስረታቸውን ገልጸዋል። ላለፉት ሥስት ዓመታት በትብብር በጋራ ሲሠሩ የቆዩት አምስት የፖለቲካ ድርጅቶች ቅንጅት መመሥረታቸውን በዛሬው ዕለት አስታውቀዋል። የቅንጅቱ ስያሜም "ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት" መሆኑን በዛሬው የመስራች ጉባኤ ላይ ተገልጿል። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ እናት ፖርቲ ፣የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፖርቲ (ኢሕአፓ)፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እና አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ናቸው ቅንጅት መመሥረታቸውን አስታውቀዋል። ቅንጅቱንም እንዲመሩ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዝዳንት አቶ አብርሀም ጌጡ ተመርጠዋል። "ለእናት ፖርቲ ትልቅ ቀን ነው" ያሉት የፖርቲው ፕሬዝዳንት ሰይፈስላሴ አያሌው (ዶ/ር)፤ "ኢትዮጵያ 50 ዓመታት የተበታተነ የፖለቲካ ጎራ መከራ እየወረደበት ላለው ፖለቲካ መፍትሄ የሚሰጥ ቅንጅት ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በተናጥል የሚመጣ…
Read More
ኢትዮጵያ የምርጫና ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ህጓን አሻሻለች

ኢትዮጵያ የምርጫና ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ህጓን አሻሻለች

ሀገራዊ ፓርቲ ለመሆን በስድስት ክልሎች የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብን የሚያስገድደዉ አዋጅ ፀድቋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ጉባኤ የምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል። አዋጁ ከነባሩ አዋጁ 1162/2011ዉስጥ የነበሩ 26 አንቀጾችን ያሻሻለ ሆኖ የቀረበ ነዉ ተብሏል። አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ሀገራዊ ፓርቲ ሆኖ ለመወዳደር ከ 6 ክልሎች የ60 በመቶ ድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብን የሚያስገድድ አንቀፅ ይገኝበታል። ከዚህ ቀደም ሀገራዊ ፓርቲ ለመሆን የአራት ክልሎች የድጋፍ ፊርማ የሚያስፈልግ ሲሆን ይህንን አንቀፅ ለማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት የተጨመሩ ክልሎች መኖራቸዉን ታሳቢ አድርጎ መሆኑን ምክር ቤቱ ገልጿል። በዚህ መሰረት ሀገራዊ ፓርቲ ለመመስረት በስድስት ክልሎች የድርጅት አባል ማፍራት እንዳለባቸዉ የሚያደርግ ነዉ። አንድ የምክር ቤት አባል የሀገራዊ ፓርቲ ምስረታን…
Read More