15
Feb
የጅቡቲ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ። የ59 ዓመቱ ዲፕሎማት ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ኮሚሽኑን እንዲመሩ የተመረጡት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሔድ በጀመረው የአፍሪካ ኅብረት ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ነው። አሊ ሞሐመድ ይሱፍ ላለፉት ሥምንት ዓመታት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋኪ ማኅማትን ይተካሉ። ይሱፍ የተመረጡት የኬንያው ጉምቱ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካር የቀድሞ የኤኮኖሚ እና የፋይናንስ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን አሸንፈው ነው። የአፍሪካ ኅብረት 38ኛ ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ሲጀመር የአንጎላው ፕሬዝደንት ዮዋዎ ሎሬንሶ የዓመቱን የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርነት ከሞሪታኒያው ፕሬዝደንት ሞሐመድ ዑልድ ተረክበዋል።