Niger

በኒጀር የሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች የሽብር ጥቃት ደረሰባቸው

በኒጀር የሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች የሽብር ጥቃት ደረሰባቸው

አየር መንገዱ እንደገለጸው ባለፈው ሃሙስ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰው ጥቃት ሁለት የአስካይ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል። ሁለቱ አውሮፕላኖች የኢትዮጵያ አየር መንገድ አጋር የሆነው የአስካይ  አየር መንገድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካኝነት ከአውሮፕላን አከራዮች የተከራያቸው እና በኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን የተመዘገቡ ናቸው ተብሏል። በአውሮፕላኖቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመገምገም የተላከው የቴክኒክ ቡድን ጉዳቱ መጠነኛ መሆኑን እንዳረጋገጠ የገለጸው አየር መንገዱ አውሮፕላኖቹ ተጠግነው በቅርቡ ወደ አገልግሎት እንደሚገቡ አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሎሜ (ቶጎ) መቀመጫውን ካደረገው አስካይ አየር መንገድ ጋር የ40% የባለቤትነት ድርሻና የቴክኒክ አጋርነት አለው። የአስካይ አውሮፕላኖች የሽብር ጥቃት ኢላማ…
Read More
አፍሪካ ህብረት ኒጀርን ከአባልነት አገደ

አፍሪካ ህብረት ኒጀርን ከአባልነት አገደ

የአፍሪካ ህብረት ከአንድ ወር በፊት መፈንቅለ መንግስት ያደረገችው ኒጀርን ከአባልነት አግዷል። በጀነራል ቲያኒ የሚመራው የኒጀር ጦር በምርጫ ስልጣን በያዙት የኒጀር ፕሬዝዳንት ባዙም ላይ በመፈንቅለ መንግሥት ስልጣን ተቆጣጥሯል። ይህን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት ኒጀርን ከአባልነት ላልተወሰነ ጊዜ ከስልጣን ማንሳቱን አስታውቋል። የመፈንቅለ መንግስቱ መሪዎች በምርጫ ስልጣን የያዙትን ፕሬዚዳንት መሃመድ ባዙምን ከእስር እንዲፈቱ እና ወደ ቤታቸው እንዲመልሱም ህብረቱ ጥሪ አቅርቧል። የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት የምዕራብ አፍሪካ ህብረት (ኢኮዋስ) ለወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ተጠባባቂ ሃይል ለማንቀሳቀስ ያሳለፈውን ውሳኔ መመልከቱንም ሬውተርስ ዘግቧል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እንደዚህ አይነት ሃይል ማሰማራት ያለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና የደህንነት አንድምታ እንዲገመግም ጠይቋል። የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) ዲሞክራሲን…
Read More