29
Jul
የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ 7 ቢሊዮን ዶላር ማትረፉን አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሰጠው መግለጫ በተያዘው በጀት ዓመት 7.02 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል። የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ ይህ ትርፍ ከባለፈው ከመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ጭማሪ አለው ብለዋል። ትርፉ በኢትዮጵያ ብር ሲሰላ 402 ቢሊዮን ብር እንደሚሆን ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል። ስራ አስፈጻሚው እንደገለጹት አየርመንገዱ 577,746 የበረራ ሰአቶችን ማስመዝገቡን እና ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ19 በመቶ ጭማሪ አለው። በበጀት አመቱ 17.1 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገዱን የገለጸው አየር መንገዱ ከእነዚህ ውስጥ 13.4 ሚሊዮን የሚሆኑት አለምአቀፍ መንገደኞች ሲሆኑ 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑን ደግሞ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ናቸው ብሏል።…