Terrorism

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ቴዎድሮስ አስፋው በአዲስ ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ቴዎድሮስ አስፋው በአዲስ ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ

በ20 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት የተወሰነላቸው ጋዜጠኞች ፌደራል ፖሊስ በሌላ ወንጀል እንደሚጠረጥራቸው አስታውቋል፡፡ ከ15 ቀን በፊት የታሰሩት ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ታዎድሮስ አስፋው በአቶ ግርማ የሺጥላ ግድያና በሽብርተኝነት ተጠርጥረዋል። ጋዜጠኞቹ ከሰሞኑ ፍርድ ቤት ቀርበው በ20 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ቢሆንም ፌደራል ፖሊስ በአዲስ ወንጀል እንደሚጠረጥራቸው ለፍርድ ቤት ባቀረበው ማመልከቻ ጠይቋል፡፡ አዲሱ የፌደራል ፖሊስ የፍርድ ቤት ማመልከቻ እንደሚያስረዳው ጋዜጠኞቹ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጪ ሀገር የገቢ ማሰባሰቢያ መንገድ በመዘርጋት ዜጎች ለሽብር እና አመጽ እንዲነሳሱ ቀስቅሰዋል ይላል፡፡ በዚህም መሰረት ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ተጠርጣሪዎቹ ለተጨማሪ 15 ቀናት ታስረው እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡ ከፌደራል ፖሊስ ምርመራ ቢሮ ማመልከቻ የቀረበለት የልደታ…
Read More
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የህወሀትን ከሽብር መዝገብ መሰረዝን ተቃወሙ

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የህወሀትን ከሽብር መዝገብ መሰረዝን ተቃወሙ

የትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባት (ህወሀት) በትግራይ ክልል ያለውን የሀገር መከላከያ ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ ነበር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተጀመረው። ለሁለት ዓመት የዘለቀው ይህ ጦርነት ከ800 ሺህ በላይ ዜጎችን እና ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ የንብረት ውድመት አድርሷል። በፌደራል መንግሥት እና ህወሀት መካከል የተደረገው ይህ ጦርነት ባሳለፍነው ህዳር በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት ተፈርሟል። ይህን ስምምነት ተከትሎም ጦርነቱ የቆመ ሲሆን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግሥት በመመስረት ላይ ይገኛል። እንዲሁም ህወሀት በግንቦት 2021 ላይ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ተፈርጆ ነበር። ይህ ህግ አውጪ ምክር ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ህወሀትን ከሽብር መዝገብ ላይ ሰርዟል። የኢትዮጵያ ማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ እና የአማራ…
Read More
ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅት ዝርዝር ውስጥ ተሰረዘ

ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅት ዝርዝር ውስጥ ተሰረዘ

ሕወሀት በሽብርተኝነት ከተፈረጀ ከ22 ወራት በኋላ ውሳኔው ተሽሯል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል። ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል። ለሰሜኑ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ ለመስጠት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል የሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል። በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረትም በፌደራል መንግስት እና በህወሓት በኩል ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። ስምምነቱ የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ እና የሰብዓዊ እርዳታ ለተጎጂዎች እንዲቀርብ አድርጓል። ህወሓትም ታጣቂዎቹን ወደ ካምፕ በመሰብሰብ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን…
Read More