Dawitbegashaw

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ቴዎድሮስ አስፋው በአዲስ ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ቴዎድሮስ አስፋው በአዲስ ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ

በ20 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት የተወሰነላቸው ጋዜጠኞች ፌደራል ፖሊስ በሌላ ወንጀል እንደሚጠረጥራቸው አስታውቋል፡፡ ከ15 ቀን በፊት የታሰሩት ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ታዎድሮስ አስፋው በአቶ ግርማ የሺጥላ ግድያና በሽብርተኝነት ተጠርጥረዋል። ጋዜጠኞቹ ከሰሞኑ ፍርድ ቤት ቀርበው በ20 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ቢሆንም ፌደራል ፖሊስ በአዲስ ወንጀል እንደሚጠረጥራቸው ለፍርድ ቤት ባቀረበው ማመልከቻ ጠይቋል፡፡ አዲሱ የፌደራል ፖሊስ የፍርድ ቤት ማመልከቻ እንደሚያስረዳው ጋዜጠኞቹ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጪ ሀገር የገቢ ማሰባሰቢያ መንገድ በመዘርጋት ዜጎች ለሽብር እና አመጽ እንዲነሳሱ ቀስቅሰዋል ይላል፡፡ በዚህም መሰረት ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ተጠርጣሪዎቹ ለተጨማሪ 15 ቀናት ታስረው እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡ ከፌደራል ፖሊስ ምርመራ ቢሮ ማመልከቻ የቀረበለት የልደታ…
Read More
ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ ታዘዘ

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ ታዘዘ

የቀድሞው የ“አል አይን ኒውስ” ጋዜጠኛ እንዲሁም “አራት ኪሎ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙሃን አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና የኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ኹለቱም በ20,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ታዟል፡፡ ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው። ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ሐሙስ ሚያዚያ 5/2015 ቂሊንጦ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ማክሲኮ ወደሚገኘው ፌደራል ፖሊስ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን የሚታወስ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፤ ሚያዚያ 4/2015 ምሽት ላይ ባህርዳር ከሚገኘው "ሆምላንድ ሆቴል" በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን መዘገባችን ይታወሳል። ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጂ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እያሰረች መሆኑን ጠቅሶ መንግሥት ያሰራቸው  ጋዜጠኞች እንዲፈታ መጠየቁ ይታወሳል።
Read More
ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ቴዎድሮስ አስፋው ፍርድ ቤት ቀረቡ

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ቴዎድሮስ አስፋው ፍርድ ቤት ቀረቡ

ሕገመንግስቱንና ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል በማለት ተጠርጥረው ከአራት ቀናት በፊት ታስረው የነበሩት ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው። ፖሊስ ተጠርጣሪ ጋዜጠኞቹን ፍርድ ቤት አቅርቦ ጊዜ ቀጠሮ የጠየቀባቸው፣ ጋዜጠኛ ዳዊት አራት ኪሎ ሚዲያ፣ የሚባል የኦንላይን ሚዲያ ፈቃድ ሳይኖረው በመክፈት ሕገመንግስቱንና ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ፣ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨትና አንዱን ሐይማኖት ከሌላው ጋር ለማጋጨት በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ እንደደረሰበት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። በተመሳሳይ ሁኔታ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስም ኢትዮ ሰላም የሚባል የኦንላይን ሚዲያ ፈቃድ ሳይኖረው በመክፈት ሲሰራ እንደነበርና ሁለቱንም ተጠርጣሪዎች እየመረመረ መሆኑን አስረድቶ ለተጨማሪ…
Read More
ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው መታሰሩ ተገለጸ

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው መታሰሩ ተገለጸ

በበርካታ የኢትዮጵያ ብዙሃን መገናኛ ተቋማት በጋዜጠኝነት ሙያ ያገለገለው ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በጽጥታ ሀይሎች መታሰሩን የስራ ባልደረቦቹ ለኢትዮ ነጋሪ ተናግረዋል ። ጋዜጠኛ ዳዊት ከሌሎች የስራ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን አራት ኪሎ ሚዲያ የተሰኘ የድጅታል ሚዲያ አቋቁሞ በመስራት ላይ ይገኝ ነበር። ጋዜጠኛው ለስራ ወደ ባህርዳር ከተማ ባቀናበት ወቅት ዛሬ ሚያዝያ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በጸጥታ ሀይሎች ተይዞ መወሰዱን ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሙያ ባልደረቦቹ ነግረውናል። ይሁንና የአማራ ክልልም ይሁን የፌደራል መንግሥት በጋዜጠኛ ዳዊት እስር ጉዳይ እስካሁን ያሉት ነገር የለም። የሀገር መከላከያ ሰራዊት ህዝብ ግንኙነት ኮለኔል ጌትነት ስለ ጋዜጠኛው እስር እንደማያውቁ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት፣ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን፣ ኢትዮ…
Read More