18
Jan
በመላው አፍሪካ 67 ጋዜጠኞች በስራቸው ምክንያት ብቻ መታሰራቸውን አለም አቀፉ የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (ሲፒጄ) ሪፖርት ያስረዳል። የተመዘገበው እስር በአፍሪካ በነጻ ሀሳብን የመግለጽ መብት ፣ የመረጃ ነጻነት እና ሌሎችም መብቶች እያሽቆለቆሉ እንደሚገኙ ማሳያ ነው ብሏል ሪፖርቱ ፡፡ ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ሲፒጄ እስከ ታህሳስ 1 ቀን ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ 361 ጋዜጠኞች መታሰራቸውን የገለጸ ሲሆን በአፍሪካ የተመዘገበው ዕስር እስከዛሬ ከነበሩት በመጠኑ ሁለተኛው ነው ተብሏል። በሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ “መንግስታት በጋዜጠኞች ላይ የብሔራዊ ደህንነት፣ የፀረ-ሽብርተኝነት እና የሳይበር ወንጀል ህጎችን በመሳሪያነት በመጠቀም ጋዜጠኞችን ለማሳደድ እና ለማሰር እያዋሉት እንደሚገኙ” ተናግረዋል፡፡ አስተባባሪው እነዚህ አዝማሚያዎች በአፍሪካ ብቻ የተገደቡ ባይሆኑም በአህጉሪቱ በእንደዚህ አይነት ህጎች ክስ የሚመሰረትባቸው…