Journalists

የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኞቹ ታገቱ

የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኞቹ ታገቱ

ሚዲያው እንደገለጸው ከህገወጥ የወርቅ ማውጣት ሂደት ጋር በተያያዘ መረጃ በማሰባሰብ ላይ የነበሩ ጋዜጤኞቹ  በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል። በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ያለውን ህገወጥ የወርቅ ማዕድን የማውጣት ሂደትና የጎንዮሽ ጉዳቶቹ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ዘገባ ለመስራት ወደ ስፍራው ያቀናው የጋዜጠኞች ቡድን በታጣቂዎች ታግተዋል ሲል ተገልጿል። ሶስት ባለሙያዎችን የያዘው የጋዜጠኞች ቡድኑ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ዓ/ም ጥዋት 3 ሰዓት በአስገደ ወረዳ፣ መይሊ ከተባለው ስፍራ ወጣ ብሎ በሚገኘውን መንደር በታጣቂዎች ተይዘዋል ተብሏል። ጋዜጠኞቹ ላለፉት ሶስት ቀናት በቦታው ተገኝተው ስላለው ነገር ከአካባቢው ነዋሪዎች መረጃዎችን ሲያሰባስቡ የቆዩ ሲሆን በተለይም በመይሊ አካባቢ ማዕድናቱን ለማውጣት በጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙ የተለያዩ ጎጂ ኬሚካሎች እያደረሱት ያለውን ጉዳት በተመለከተ መረጃዎች…
Read More