12
Aug
መንግስት በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ፍትህ እንዲያገኙ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ጠይቋል። ማህበሩ የጋዜጠኞቹ የፍርድ ሂደትም ከፖለቲካ አተያይ በፀዳ መንገድ እንዲሆን ጥሪውን ያቀርባል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር አዲስ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በአዲ አበባ ቃሊቲና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤቶች በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም ስለ ማረሚያ ቤት አያያዝ እና አጠቃላይ የፍትህ ሂደቱ ያለበትን ሁኔታ ከጋዜጠኞቹ ጋር እንደተወያዩ ማህበሩ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡ ጋዜጠኞቹ በማረሚያ ቤቶቹ አያያዝ በኩል ቅሬታ ባይኖራቸውም በፖሊስ ቁጥጥር ስር በተያዙበት ወቅት የተያዙበት መንገድም ሆነ ከተያዙ በኃላ ያለው የፍርድ ቤት ሂደት አግባብነት እንደሚጎድለው ተናግረዋል፡፡ በሁለቱም ማረሚያ ቤቶች ከአንድ ዓመት በላይ ሳይፈረድባቸው የታሰሩ ጋዜጠኞች መኖራቸውን ማኅበሩ እንዳረጋገጠ አስታውቋል። ስለሆነም…