Journalistinethiopia

አዲሱ የኢትዮጵያ ሚዲያ ህግ ማሻሻያ ከሚዲያ እና ህግ ባለሙያዎች ማህበራት ተቃውሞ ገጠመው

አዲሱ የኢትዮጵያ ሚዲያ ህግ ማሻሻያ ከሚዲያ እና ህግ ባለሙያዎች ማህበራት ተቃውሞ ገጠመው

የሚዲያ ህግ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ሁሉን ያሳተፈ ውይይት በአስቸኳይ እንዲደረግበት  ተጠይቋል፡፡ ከአንድ ወር በፊት በስራ ላይ ያለው የሚዲያ ህግ እንዲሻሻል ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ይታወሳል፡፡ ይህ ረቂቅ አዋጅ በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይት ሳይደረግበት ወደ ቋሚ ኮሚቴ መመራቱ ትክክል እንዳልሆነ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የጋዜጠኞች፣ ህግ እና ሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ማህበራት ተችተዋል፡፡ 14 የጋዜጠኞች፣ ህግ እና ሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ማህበራት በጋራ ባወጡት መግለጫ የሚዲያ ህግ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የሕዝብንም ሆነ የባለድርሻ አካላትን ድምፅ በተገቢ ያላካተተ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡ የጋዜጠኞች ማህበራት እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶቹ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሁለት ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ…
Read More
ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በዘፈቀደ የሚታሰሩባት ሀገር መሆኗን ሲፒጂ አስታወቀ

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በዘፈቀደ የሚታሰሩባት ሀገር መሆኗን ሲፒጂ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኞችን በዘፈቀደ ከማሰር ሊቆጠቡ ይገባል ሲል የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ አሳሰበ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ በሶማሌ ክልል የታሰረውን ጋዜጠኛ ሙህያዲን መሀመድ አብዱላሂን  አስመልክቶ ትናንት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኞችን በዘፈቀደ ከማሰር ሊቆጠቡ ይገባል ብሏል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከአንድ ወር ገደማ በፊት የታሰረውን ጋዜጠኛ ሙህያዲን መሀመድ አብዱላሂን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ጠይቋል። ሙክሲየዲን ሾው፤ በሚል የፌስ ቡክ ገፁ ላይ ዘገባዎችን እና አስተያየቶችን የሚጽፈው ሙህያዲን፤ በኢትዮጵያ  የሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ፤ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋሉን ኮሚቴው አመልክቷል። በመጋቢት  4 ቀን  ሙህያዲን የኢትዮጵያን የጥላቻ ንግግር እና የሀሰት መረጃ ህግን በመጣስ እና የሀሰት ዜና…
Read More
በኢትዮጵያ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች የረሀብ አድማ ጀመሩ

በኢትዮጵያ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች የረሀብ አድማ ጀመሩ

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች እና ምሁራን የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። መንግሥትን በኃይል ለመጣል አሲረዋል በሚል የሽብርተኝነት ክስ ቀርቦባቸው በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እና ምሁራን የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን የእስረኞቹ ቤተሰቦች ገለጹ። ተጠርጣሪዎቹ የረሃብ አድማውን የጀመሩት ከትላንት ጀምሮ ሲሆን፤ አድማው ለሦስት ተከታታይ ቀን የሚቆይ እንንደሆነ ተገልጿል። የረሃብ አድማው ላይ ከሚገኙት እስረኞች መካከል ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሳሳይ፣ መምህርት መስከረም አበራ፣ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ እና ሌሎች የሽብር ክስ የቀረበባቸው ታሳሪዎች ይገኙበታል። የአድማው ምክንያት ከእነሱ እስር በተጨማሪ በምንም ጉዳይ ላይ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች በብዛት የሚታሰሩበትን ሁኔታ ለመቃወም ነውም ተብሏል። የፌደራል መንግሥት ጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ…
Read More
ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ቴዎድሮስ አስፋው በአዲስ ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ቴዎድሮስ አስፋው በአዲስ ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ

በ20 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት የተወሰነላቸው ጋዜጠኞች ፌደራል ፖሊስ በሌላ ወንጀል እንደሚጠረጥራቸው አስታውቋል፡፡ ከ15 ቀን በፊት የታሰሩት ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ታዎድሮስ አስፋው በአቶ ግርማ የሺጥላ ግድያና በሽብርተኝነት ተጠርጥረዋል። ጋዜጠኞቹ ከሰሞኑ ፍርድ ቤት ቀርበው በ20 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ቢሆንም ፌደራል ፖሊስ በአዲስ ወንጀል እንደሚጠረጥራቸው ለፍርድ ቤት ባቀረበው ማመልከቻ ጠይቋል፡፡ አዲሱ የፌደራል ፖሊስ የፍርድ ቤት ማመልከቻ እንደሚያስረዳው ጋዜጠኞቹ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጪ ሀገር የገቢ ማሰባሰቢያ መንገድ በመዘርጋት ዜጎች ለሽብር እና አመጽ እንዲነሳሱ ቀስቅሰዋል ይላል፡፡ በዚህም መሰረት ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ተጠርጣሪዎቹ ለተጨማሪ 15 ቀናት ታስረው እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡ ከፌደራል ፖሊስ ምርመራ ቢሮ ማመልከቻ የቀረበለት የልደታ…
Read More
ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ ታዘዘ

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ ታዘዘ

የቀድሞው የ“አል አይን ኒውስ” ጋዜጠኛ እንዲሁም “አራት ኪሎ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙሃን አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና የኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ኹለቱም በ20,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ታዟል፡፡ ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው። ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ሐሙስ ሚያዚያ 5/2015 ቂሊንጦ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ማክሲኮ ወደሚገኘው ፌደራል ፖሊስ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን የሚታወስ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፤ ሚያዚያ 4/2015 ምሽት ላይ ባህርዳር ከሚገኘው "ሆምላንድ ሆቴል" በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን መዘገባችን ይታወሳል። ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጂ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እያሰረች መሆኑን ጠቅሶ መንግሥት ያሰራቸው  ጋዜጠኞች እንዲፈታ መጠየቁ ይታወሳል።
Read More