Hungerstrike

በኢትዮጵያ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች የረሀብ አድማ ጀመሩ

በኢትዮጵያ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች የረሀብ አድማ ጀመሩ

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች እና ምሁራን የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። መንግሥትን በኃይል ለመጣል አሲረዋል በሚል የሽብርተኝነት ክስ ቀርቦባቸው በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እና ምሁራን የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን የእስረኞቹ ቤተሰቦች ገለጹ። ተጠርጣሪዎቹ የረሃብ አድማውን የጀመሩት ከትላንት ጀምሮ ሲሆን፤ አድማው ለሦስት ተከታታይ ቀን የሚቆይ እንንደሆነ ተገልጿል። የረሃብ አድማው ላይ ከሚገኙት እስረኞች መካከል ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሳሳይ፣ መምህርት መስከረም አበራ፣ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ እና ሌሎች የሽብር ክስ የቀረበባቸው ታሳሪዎች ይገኙበታል። የአድማው ምክንያት ከእነሱ እስር በተጨማሪ በምንም ጉዳይ ላይ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች በብዛት የሚታሰሩበትን ሁኔታ ለመቃወም ነውም ተብሏል። የፌደራል መንግሥት ጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ…
Read More