17
Jul
ሀገራዊ ፓርቲ ለመሆን በስድስት ክልሎች የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብን የሚያስገድደዉ አዋጅ ፀድቋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ጉባኤ የምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል። አዋጁ ከነባሩ አዋጁ 1162/2011ዉስጥ የነበሩ 26 አንቀጾችን ያሻሻለ ሆኖ የቀረበ ነዉ ተብሏል። አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ሀገራዊ ፓርቲ ሆኖ ለመወዳደር ከ 6 ክልሎች የ60 በመቶ ድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብን የሚያስገድድ አንቀፅ ይገኝበታል። ከዚህ ቀደም ሀገራዊ ፓርቲ ለመሆን የአራት ክልሎች የድጋፍ ፊርማ የሚያስፈልግ ሲሆን ይህንን አንቀፅ ለማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት የተጨመሩ ክልሎች መኖራቸዉን ታሳቢ አድርጎ መሆኑን ምክር ቤቱ ገልጿል። በዚህ መሰረት ሀገራዊ ፓርቲ ለመመስረት በስድስት ክልሎች የድርጅት አባል ማፍራት እንዳለባቸዉ የሚያደርግ ነዉ። አንድ የምክር ቤት አባል የሀገራዊ ፓርቲ ምስረታን…