12
Nov
የሚዲያ ህግ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ሁሉን ያሳተፈ ውይይት በአስቸኳይ እንዲደረግበት ተጠይቋል፡፡ ከአንድ ወር በፊት በስራ ላይ ያለው የሚዲያ ህግ እንዲሻሻል ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ይታወሳል፡፡ ይህ ረቂቅ አዋጅ በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይት ሳይደረግበት ወደ ቋሚ ኮሚቴ መመራቱ ትክክል እንዳልሆነ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የጋዜጠኞች፣ ህግ እና ሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ማህበራት ተችተዋል፡፡ 14 የጋዜጠኞች፣ ህግ እና ሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ማህበራት በጋራ ባወጡት መግለጫ የሚዲያ ህግ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የሕዝብንም ሆነ የባለድርሻ አካላትን ድምፅ በተገቢ ያላካተተ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡ የጋዜጠኞች ማህበራት እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶቹ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሁለት ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ…