CPJ

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ከሚያስሩ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተተች

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ከሚያስሩ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተተች

በመላው አፍሪካ 67 ጋዜጠኞች በስራቸው ምክንያት ብቻ መታሰራቸውን አለም አቀፉ የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (ሲፒጄ) ሪፖርት ያስረዳል። የተመዘገበው እስር በአፍሪካ በነጻ ሀሳብን የመግለጽ መብት ፣ የመረጃ ነጻነት እና ሌሎችም መብቶች እያሽቆለቆሉ እንደሚገኙ ማሳያ ነው ብሏል ሪፖርቱ ፡፡ ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ሲፒጄ እስከ ታህሳስ 1 ቀን ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ 361 ጋዜጠኞች መታሰራቸውን የገለጸ ሲሆን በአፍሪካ የተመዘገበው ዕስር እስከዛሬ ከነበሩት በመጠኑ ሁለተኛው ነው ተብሏል። በሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ “መንግስታት በጋዜጠኞች ላይ የብሔራዊ ደህንነት፣ የፀረ-ሽብርተኝነት እና የሳይበር ወንጀል ህጎችን በመሳሪያነት በመጠቀም ጋዜጠኞችን ለማሳደድ እና ለማሰር እያዋሉት እንደሚገኙ” ተናግረዋል፡፡ አስተባባሪው እነዚህ አዝማሚያዎች በአፍሪካ ብቻ የተገደቡ ባይሆኑም በአህጉሪቱ በእንደዚህ አይነት ህጎች ክስ የሚመሰረትባቸው…
Read More
ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በዘፈቀደ የሚታሰሩባት ሀገር መሆኗን ሲፒጂ አስታወቀ

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በዘፈቀደ የሚታሰሩባት ሀገር መሆኗን ሲፒጂ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኞችን በዘፈቀደ ከማሰር ሊቆጠቡ ይገባል ሲል የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ አሳሰበ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ በሶማሌ ክልል የታሰረውን ጋዜጠኛ ሙህያዲን መሀመድ አብዱላሂን  አስመልክቶ ትናንት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኞችን በዘፈቀደ ከማሰር ሊቆጠቡ ይገባል ብሏል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከአንድ ወር ገደማ በፊት የታሰረውን ጋዜጠኛ ሙህያዲን መሀመድ አብዱላሂን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ጠይቋል። ሙክሲየዲን ሾው፤ በሚል የፌስ ቡክ ገፁ ላይ ዘገባዎችን እና አስተያየቶችን የሚጽፈው ሙህያዲን፤ በኢትዮጵያ  የሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ፤ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋሉን ኮሚቴው አመልክቷል። በመጋቢት  4 ቀን  ሙህያዲን የኢትዮጵያን የጥላቻ ንግግር እና የሀሰት መረጃ ህግን በመጣስ እና የሀሰት ዜና…
Read More
መንግሥት ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን ከእስር እንዲለቅ ሲፒጂ ጠየቀ

መንግሥት ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን ከእስር እንዲለቅ ሲፒጂ ጠየቀ

የኢትዮ ኒውስ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም የጸጥታ ክልሎች አራት ኪሎ በሚገኘው ከቢሮው አካባቢ እንዳሰሩት የስራ ባልደረባው እና ባለቤቱ ተናግረዋል። የጋዜጠኞች መሽት ተሟጋች የሆነው ሲፒጂ ባወጣው ሪፖርት ጋዜጠኛ በላይ ከታሰረ ሶስት ሳምንት እንዳለፈው እና እስካሁን ፍርድ ቤትም እንዳልቀረበ አስታውቋል። የሲፒጂ ሰብሰሀራ አፍሪካ ተወካይ የሆኑት ሙቶኪ ሙሞ እንዳሉት በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የመስራት ነጻነታቸው መጎዳቱን ተናግረዋል ። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲለቅ ሲፒጂ አሳስቧል። እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት የጋዜጠኞችን እስር እንዲያቆምም ሲፒጂ ጥሪ አቅርቧል። የጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ባለቤት በላይነሽ ንጋቱ ባለቤቷ አንድ ጊዜ ከታሰረበት ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሄዳ እንደጠየቀችው የተናገረች ሲሆን በአማራ ክልል…
Read More