03
May
ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ 29 ጋዜጠኞች በታሰሩባት ኢትዮጵያ፤ የፕሬስ ነጻነት “ጉልህ ጥቃት” እንዳጋጠመው ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና የደቡባዊ አፍሪካ ሚዲያ ኢንስቲትዩት አስታወቁ። ባለስልጣናት የፕሬስ ነጻነትን ማፈን በሚፈልጉባቸው በምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት፤ በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እየጨመረ መምጣቱንም ተቋማቱ ገልጸዋል። ሁለቱ ተቋማት ይህን ያሉት ዛሬ ረቡዕ ሚያዝያ 25፤ 2015 ታስቦ የሚውለውን የዓለም የፕሬስ ነጻነትን በማስመልከት በጋራ ባወጡት ዳሰሳ ነው። ዳሰሳው ኢትዮጵያን ጨምሮ በ10 የአፍሪካ ሀገራት ያለውን የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን እና በጋዜጠኞች ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን በማሳያነት በማንሳት ዳሰሳ አድርጓል። በዚሁ ዳሰሳ፤ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በመለጠቅ ስሟ የተጠቀሰው ኢትዮጵያ ነች።…