04
May
የጣና ሀይቅ ደሴትና ገዳማት በአለም አቀፍ የቅርስ መዝገብ እንዲሰፍሩ የሚያስችለዉ ሰነድ ለዮኔስኮ ተልኳል። በአማራ ክልል የሚገኙ የመስህብ ሀብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ የባህልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪውን በማሳደግ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል። የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አበበ እምቢአለ እንደተናገሩት በክልሉ የሚገኙ በርካታ የመስህብ ቦታዎች እንደመኖራቸው የጣና ሀይቅ እና አካባቢውን በዮኔስኮ አለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። ከዚህ ቀደም የጣና ሀይቅ ደሴቶች በብዛ ህይወት ቅርስነት የተመዘገበ መሆኑን ገልፀው በአሁኑ ወቅት ይህ ስፍራ በአለም አቀፍ ቅርስነት እንዲመዘገብ ለማድረግ በተዘጋጀዉ ሰነድ ዙሪያ ማስተካከያ መደረጉን ተናግረዋል። ሰነዱን አስመልክቶ አስተያየት የመስጠትና ተጨማሪ ግብዓቶችና ማስተካከያዎችን የማዘጋጀት ስራ ሲሰራ እንደቆየ የገለፁት…