Freedomofspeech

ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመዝጋቷ ምክንያት ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማጣቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመዝጋቷ ምክንያት ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማጣቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከያዝነው ዓመት የካቲት ወር ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ባሉት አምስት ወራት በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ገደብ ጥላለች። ኢትዮጵያ የኢንተርኔት እገዳውን የጣለችው በቲክቶክ፣ ቴሌግራም፣ ፌስቡክ እና ዩቲዩብ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ነው። በኢንተርኔት እገዳው ምክንያትም ኢትዮጵያ 7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ ማጣቷን የመብቶችና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል ገልጿል፡፡ “ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶችን ተከትሎ፤ ከ2008 ወዲህ የበይነመረብ ግንኙነትን ማቋረጥ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣ ችግር ነው” ያለው ማዕከሉ፤ የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጡ የዴሞክራሲና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገት ጸር መሆኑን አመላክቷል፡፡ መንግሥት ዋና ዋና የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች በኢትዮጵያ እንዳይጎበኙ እገዳ መጣሉ ሕጋዊ መሰረት የሌለው ነው ሲልም ገልጿል፡፡ የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጥ ትኩረት ሊያገኝ ባለመቻሉም የሰብዓዊ መብቶች እሴቶችን እንዲሁም በሕገ መንግሥቱ የተጠበቁ…
Read More
ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ ታዘዘ

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ ታዘዘ

የቀድሞው የ“አል አይን ኒውስ” ጋዜጠኛ እንዲሁም “አራት ኪሎ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙሃን አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና የኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ኹለቱም በ20,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ታዟል፡፡ ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው። ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ሐሙስ ሚያዚያ 5/2015 ቂሊንጦ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ማክሲኮ ወደሚገኘው ፌደራል ፖሊስ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን የሚታወስ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፤ ሚያዚያ 4/2015 ምሽት ላይ ባህርዳር ከሚገኘው "ሆምላንድ ሆቴል" በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን መዘገባችን ይታወሳል። ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጂ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እያሰረች መሆኑን ጠቅሶ መንግሥት ያሰራቸው  ጋዜጠኞች እንዲፈታ መጠየቁ ይታወሳል።
Read More
መንግስት የጋዜጠኞችን እስር እንዲያቆም ተጠየቀ

መንግስት የጋዜጠኞችን እስር እንዲያቆም ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ብዙሀን መገናኛ ባለሙያዎች ማህበር በጋዜጠኞች እስር ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል። ማህበሩ እንዳለው ብዙሀን መገናኛ ባለሙያዎች ስህተት በሚሰሩበት ወቅት ደግሞ በህግ አግባብ መጠየቅ እንዳለባቸው እና የህግ የበላይነት መከበር እንዳለበት እንደሚያምን ገልጿል። ይሁንን " ከለውጡ በኋላ " በሀገራችን የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት እንዲረጋገጥ ማህበራችን ብዙ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ባለሙያዎች የሚሰሩበት አውድ እየጠበበ ጋዜጠኞች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ በመንግስት የፀጥታ አካላት እየተሸማቀቁ እና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ማህበሩ በመግለጫው ላይ ጠቁሟል። የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር መስራችና የስራ አስፈፃሚ አባል እንዲሁም የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውን ጨምሮ አራጋው ሲሳይ ፣ ገነት አስማማው ፣ ጌትነት አሻግሬ ፣ በየነ ወልዴና ቴዎድሮስ አስፋው…
Read More