Socialmedia

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የማህበራዊ ትስስር ኩባንያዎች ቢሯቸውን በአዲስ አበባ እንዲከፍቱ ጠየቀች

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የማህበራዊ ትስስር ኩባንያዎች ቢሯቸውን በአዲስ አበባ እንዲከፍቱ ጠየቀች

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እንደ ሜታ (ፌሰቡክ) ያሉ የማኅበራዊ ትስስር አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቅርጫንፍ ቢሮዎቻቸውን በኢትዮጵያ እንዲከፍቱ ጠይቋል፡፡ ባለሥልጣኑ በበይነ መረብ የሚካሄዱ የጥላቻ ንግግችን የሚመለከት የአንድ ዓመት ሪፖርቱን የተመለከተ መግለጫ ለመገናኛ ብዙኃን ሰጥቷል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን "እንደ ፌስቡክ ያሉ ድርጅቶች ከፍተኛ ተጠቃሚ ባለው ኢትዮጵያ ለማስታወቂያ ገቢ እያስገኙ አይደለም" ብሏል። ኢትዮጵያ ከ44 ሚሊዮን በላይ የበይነ ተጠቃሚዎች ያሉባት ሀገር ብትሆንም፤ እስካሁን ድረስ የማኅበራዊ ሚዲያ ፖለሲም ሆነ አዋጅ የላትም። ባለሥልጣኑ ለሦስተኛ ግዜ እንዳዘጋጀው በተገለጸው ሪፖርት ላይ፤ የጥላቻ ንግግር ከምንጊዜውም በላይ በበይነ መረብ አማካኝነት መስፋፋቱን ያሳያል ብሏል። ከጥር 2016 ዓ.ም. እስከ ጥር 2017 ዓ.ም. ያለውን የአንድ ዓመት ሪፖርት መቅረቡን ለመገናኛ ብዙኃን የገለጹት መግለጫውን…
Read More
ኢትዮጵያ የአልኮል መጠጦችን በማህበራዊ ሚዲያ እንዳይሰራጩ የሚከለክል ረቂቅ ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ የአልኮል መጠጦችን በማህበራዊ ሚዲያ እንዳይሰራጩ የሚከለክል ረቂቅ ህግ አዘጋጀች

የአልኮል ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች ማስተዋወቅን በከፊል የሚከለክል የህግ ረቂቅ ተዘጋጅቷል የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለሰልጣን የአልኮል ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች ማስተዋወቅን በከፊል የሚከለክል የህግ ረቂቅ አዘጋጅቶ በሒደት ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል። ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት የአልኮል ምርቶችን እንደ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ባሉ መገናኛ ብዙኃን ማስተዋወቅ በህግ ማገዷ ይታወቃል። የአልኮል አምራች ተቋማት በአሁን ሰዓት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም፤ ምርታቸውን እያስተዋቁ እና ለበርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች እየደረሱ ነው ተብሏል። ከእነዚህ መካከልም የማህበራዊ ሚዲያ በብዛትና በተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እየተጠቀሙ እንደሆነ ተነግሯል። ይህንን እየተስፋፋ የመጣው በማህበራዊ ሚዲያ የአልኮል ማስታወቂያን በተቻለ መጠን ለመገደብ ታስቦ፤ የህግ ማዕቀፍ ተሰናድቶ በሒደት ላይ እንደሚኝ በኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የህግ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ፍሬሰላም ዮሴፍ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ…
Read More
ኢትዮጵያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የጣለችውን ገደብ አነሳች

ኢትዮጵያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የጣለችውን ገደብ አነሳች

በኢትዮጽያ ለወራት ያህል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ተነስቷል። በኢትዮጵያ ከየካቲት ወር መጀመሪያ አንስቶ በኢንተርኔት አገልግሎቶች ማለትም በፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ቴሌግራም እና ቲክቶክ ላይ ገደብ መጣሉ ይታወሳል። በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ገደብ መጣሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ በርካታ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች መንግሥት ገደቡን እንዲያነሳ ሲጠየቅ ቆይቷል። በኢንተርኔት እገዳው ምክንያትም ኢትዮጵያ 7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ ማጣቷን የመብቶችና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል ገልጿል፡፡ “ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶችን ተከትሎ፤ ከ2008 ወዲህ የበይነመረብ ግንኙነትን ማቋረጥ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣ ችግር ነው” ያለው ማዕከሉ፤ የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጡ የዴሞክራሲና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገት ጸር መሆኑን አመላክቷል፡፡ መንግሥት ዋና ዋና የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች በኢትዮጵያ እንዳይጎበኙ እገዳ መጣሉ ሕጋዊ መሰረት…
Read More
ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመዝጋቷ ምክንያት ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማጣቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመዝጋቷ ምክንያት ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማጣቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከያዝነው ዓመት የካቲት ወር ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ባሉት አምስት ወራት በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ገደብ ጥላለች። ኢትዮጵያ የኢንተርኔት እገዳውን የጣለችው በቲክቶክ፣ ቴሌግራም፣ ፌስቡክ እና ዩቲዩብ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ነው። በኢንተርኔት እገዳው ምክንያትም ኢትዮጵያ 7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ ማጣቷን የመብቶችና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል ገልጿል፡፡ “ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶችን ተከትሎ፤ ከ2008 ወዲህ የበይነመረብ ግንኙነትን ማቋረጥ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣ ችግር ነው” ያለው ማዕከሉ፤ የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጡ የዴሞክራሲና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገት ጸር መሆኑን አመላክቷል፡፡ መንግሥት ዋና ዋና የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች በኢትዮጵያ እንዳይጎበኙ እገዳ መጣሉ ሕጋዊ መሰረት የሌለው ነው ሲልም ገልጿል፡፡ የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጥ ትኩረት ሊያገኝ ባለመቻሉም የሰብዓዊ መብቶች እሴቶችን እንዲሁም በሕገ መንግሥቱ የተጠበቁ…
Read More
መንግሥት በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ የጣለውን ገደብ እንዲያነሳ በድጋሚ ተጠየቀ

መንግሥት በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ የጣለውን ገደብ እንዲያነሳ በድጋሚ ተጠየቀ

የኢትዮጵየ መንግሥት ፌስቡክ እና ዩቲዩብን ጨምሮ በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ የጣለውን ገደብ እንዲያነሳ የጠየቀው ዓለም አቀፉ መብቶች ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ነው፡፡  አምነስቲ የማኅበራዊ መገናኛ መድረኮቹ ከተገደቡ አንድ ወር እንደሞላቸው ዛሬ ሐሙስ የካቲት 30፣ 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡  በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የአምነስቲ የምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ፍላቪያ ምዋንጎቪ፤ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ እና ዩቲዩብን ማኅበረሰቡ እንዳይጠቀም ገደብ ከጣሉ አንድ ወር እንደሞላቸው አስታውሰው፤ ይህም ‹‹የዜጎችን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽና መረጃን የማግኘት መብቶችን በግልጽ የሚጥስ ነው›› ብለዋል፡፡  በኢትዮጵያ አምነስቲ የጠቀሳቸው የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ገደበ የተጣለባቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረ ክስተት ተከትሎ ውጥረት በመስፈኑ ነበር፡፡  የመብቶች ተሟጋቹ በመግለጫው…
Read More
ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በሟቋረጧ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በሟቋረጧ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተነገረ ቶፕ 10 ቪፒኤን የቴክኖሎጂ ኩባንያ እንዳስታወቀው፣ በትግራይ ክልል የነበረውን ጦርነት ተከትሎ ለአንድ አመት ሙሉ የኢንተርኔት አገልግሎት በመዘጋቱ ሃገሪቱ 146 ሚሊዮን ዶላር ማጣቷን አስታውቋል። አሁንም ቢሆንም በመላው ሀገሪቱ ኢንተርኔት በመቋረጡ ሚሊዮን ዶላሮችን እያጣች ትገኛለች ብሏል። ኢንተርኔት ከተዘጋ ዛሬ 28ኛ ቀኑን የያዙ ሲሆን መንግሥት እስካሁን ስለጉዳዩ ያለው ነገር የለም። መንግሥት የዘጋውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲከፍት የተሉያዩ አካላት ግፊት በማድረግ ላይ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሚዲያ ምክር ቤት እና ኢሰመኮ ከሰሞኑ ኢንተርኔት እንዲለቀቅ ከጠየቁ ተቋማት መካከል ዋነኞቹ ናቸው። ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የኢንተርኔት አገልግሎት እቀባ ከሚፈጽሙ ሀገራት መካከል አንዷ እንደሆነች ኔትብሎክስ ከዚህ በፊት ባወጣው ሪፖርት ገልጿል። ቲክቶክ፣ዩቲዩብ፣ቴሌግራም…
Read More