13
May
የአልኮል ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች ማስተዋወቅን በከፊል የሚከለክል የህግ ረቂቅ ተዘጋጅቷል የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለሰልጣን የአልኮል ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች ማስተዋወቅን በከፊል የሚከለክል የህግ ረቂቅ አዘጋጅቶ በሒደት ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል። ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት የአልኮል ምርቶችን እንደ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ባሉ መገናኛ ብዙኃን ማስተዋወቅ በህግ ማገዷ ይታወቃል። የአልኮል አምራች ተቋማት በአሁን ሰዓት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም፤ ምርታቸውን እያስተዋቁ እና ለበርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች እየደረሱ ነው ተብሏል። ከእነዚህ መካከልም የማህበራዊ ሚዲያ በብዛትና በተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እየተጠቀሙ እንደሆነ ተነግሯል። ይህንን እየተስፋፋ የመጣው በማህበራዊ ሚዲያ የአልኮል ማስታወቂያን በተቻለ መጠን ለመገደብ ታስቦ፤ የህግ ማዕቀፍ ተሰናድቶ በሒደት ላይ እንደሚኝ በኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የህግ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ፍሬሰላም ዮሴፍ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ…