google

ጎግል ፕሌይ ኢትዮጵያዊን ባለሙያዎችን መቀበል ጀመረ

ጎግል ፕሌይ ኢትዮጵያዊን ባለሙያዎችን መቀበል ጀመረ

የጎግል ፕሌይ አልሚዎች ምዝገባ ኢትዮጵያውያን አልሚዎችን መቀበል ጀምሯል። ኢትዮጵያውያን አልሚዎች በጎግል ፕሌይ ላይ ተቀባይነት ማግኘተቻው የተለያዩ መተግበሪያዎችን እያለሙ ዓለም አቀፍ ደንበኞችን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከጎግል ኩባንያ ጋር ያደረጋቸው ተደጋጋሚ ጥረቶች ለዚህ እንዳበቃቸው ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያዊያን የአይሲቲ ባለሙያዎች የGoogle Playን አለምአቀፍ ታዳሚዎች በቀጥታ በማስገኘት መተግበሪያዎቻቸው ሰፊ እይታን እንዲያገኝ እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስችላልም ተብሏል፡፡ ይህ ምዕራፍ የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ተሰጥኦ ባለቤቶች መተግበሪያዎቻቸውን በዓለም ላይ ካሉት ትላልቅ ዲጂታል መድረኮች ላይ እንዲያትሙ አዲስ እድሎችን የሚከፍት እንደሆነም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ዶ/ር እንዳሉት መንግስት የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለመገንባት በርካታ ተነሳሽነቶችን በመተግበር እየሰራ መሆኑን ገልጸው ይህ አዲስ ጅማሮ…
Read More