16
Oct
የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ሽያጩን በይፋ አስጀምሯል፡፡ 100 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ሀብት ያለው ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊዮን ብር አክስዮኑን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡ አንዱን የድርጅቱን አክስዮን ዋጋ በ300 ብር እንደሚሸጥ ያስታወቀው ኢትዮ ቴሌኮም አንድ ግለሰብ መግዛት የሚችለው 33 አክስዮን ወይም 9 ሺህ 900 ብር ነው ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮ ቴሌኮም 3 ሺህ 333 አክስዮኖቹን ለሽጭ ያቀረበ ሲሆን 30 ቢሊዮን ብር ከአክስዮን ሽያጭ ለማግኘት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜጎች አክስዮን መግዛት ይችላሉ የተባለ ሲሆን ተቋማት ግን አክሲዮንን መግዛት እንደማይችሉ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል፡፡ የአክሲዮን ሽያጩ ከዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይጠናቀቃልም…