08
Apr
ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በመከታተል እና ሪፖርቶችን በማውጣት የሚታወቀው ኔት ብሎክስ የ2023 ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ ተቋም ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ ከኢንተርኔት በመዝጋት ገቢ ካጡ ሀገራት መካከል ከሩሲያ በመቀጠል ከፍተኛ ገቢ ያጣች ሀገር ተብላለች፡፡ ሩሲያ 113 ሚሊዮን ዜጎቿን ከኢንተርኔት ውጪ በማድረጓ አራት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ስታጣ ኢትዮጵያ ደግሞ 30 ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ ተደርገዋል፡፡ ሆን ተብሎ በመንግስት እንደተወሰደ የተገለጸው ይህ ኢንተርኔት ማቋረጥ ኢትዮጵያ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አሳጥቷታል ተብሏል፡፡ ሀገራት ኢንተርኔት አገልግሎቶችን የሚያቋርጡት በሶስት ምክንያት ነው የተባለ ሲሆን ተቃውሞዎችን ለማፈን፣ የሀሳብ ነጻነትን ለመገደብ እና የምርጫ ስራዎች እንዳይታወኩ በሚል እንደሆነም ተገልጿል፡፡ 25 የዓለማችን ሀገራት ኢንተርኔት አቋርጠዋል የተባለ ሲሆን…