05
May
ከሰሞኑ በጀነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ከባህርዳር የተነሱ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ካርቱም ኤርፖርት ላይ ጥቃት አድርሰዋል የሚል ክስ አቅርቦ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና መከላከያ ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ህዝቦች ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት አንዳንድ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት በመጣስ የሚያደርጉትን ትንኮሳ ለህዝብ ይፋ ከማድረግ መቆጠቡን አንስቷል፡፡ የሱዳን ጦር የህወሃት ቅጥረኛ ወታደሮችን በእርስ በርስ ጦርነቱ ውስጥ ማሳተፉን እና ለእነዚህ ቅጥረኛ ወታደሮች የጦር መሳሪያ እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በምዕራብ ኢትዮጵያ ትንኮሳ እንዲፈፅሙ ማድረጉን በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት…