31
Jan
በትግራይ ዜጎች ዳግመኛ ግጭት ይቀሰቀሳል በሚል ስጋት ባለፉት ሶስት ቀናት ዉስጥ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ሸመታ ላይ ናቸዉ ተብሏል፡፡ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ክንፍ የተሾሙ የተባሉ ግለሰብ በሚሊሻዎች ታጅበው ትናንት የመቐለ 104 ነጥብ 4 ኤፍኤም ሬድዮ ጣብያ ለመቆጣጠር መሞከራቸው ተከትሎ በሬድዮ ጣብያው ውዝግብ ተፈጥሮ ነበር። ታጣቂዎቹ ከዚህ ቀደም በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተሾሙትን የጣቢያው ሃላፊ አውርደው በሌላ ሰው የመተካት እንቅስቃሴ ማድረጋቸውንና የከተማዋ ፖሊስ ደርሶ ድርጊቱን ማስቆሙ ታውቋል። የወታደራዊ አመራሮቹ ውሳኔ ተከትሎ ደግሞ ግጭት እንዳይነሳ የሰጉ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ገንዘባቸው ከባንክ ማውጣት እና ሸቀጦች መግዛት ላይ ተጠምደዋል መባሉን ዶቼ ቬለ ዘግቧል። ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመቐለ…