30
Sep
በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተመድ ጉባዔ ጎን ለጎን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ሞሊ ፊ ከውይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ኃይል የበዛበት የመንግሥት ምላሽና ንፁኃን ላይ ያነጣጠረ የታጣቂዎች ጥቃት እንዲቆም አሳስበዋል። ረዳት ሚኒስትሯ ከሁለት ዓመታት በፊት የተካሄደውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተሳካ ሁኔታ እንዲፈጸም፣ ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በመሆን ያለ ማቋረጥ ውትወታ እናደርጋለንም ብለዋል። በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ያለውን ግጭት በተመለከተ ያለንን ሥጋት በመግለጽ እንዲቆም በግል በሚደረግ ውይይትና በይፋ በሚኖሩ መግለጫዎች እየጠየቁ መሆኑን አስታውቀዋል። ታጣቂዎች በንፁኃንና በመንግሥት መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እያደረሱ መሆኑን የገለጹት ሞሊ ፊ የመንግሥት…