02
Apr
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፊታችን ግንቦት ሊካሄድ ስለታሰበው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት አካል የሆነው የምርጫ ምዝገባ ሂደት ላይ እየደረሱ ያሉ ተገቢ ያልሆኑ ተጽዕኖዎች እና ጣልቃ ገብነቶችን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። ቦርዱ በመግለጫው እንደጠቀሰው በክልል መንግሥታት እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ስር ባሉ አስፈጻሚዎች አማካኝነት ቤት ለቤት በመሄድ " ተመዝገቡ " የሚል ቅስቀሳ እየተደረገ መሆኑን ደርሼበታለሁ ብሏል። የምርጫ ካርድ መውሰድን እንደ ግዴታ በመቁጠር ጫና መፍጠር፣ የመራጭነት ምዝገባን ከማህበራዊ አገልግሎቶች ጋር ማያያዝ፣ እንዲሁም " የመራጭነት ካርድ ካልወሰዳችሁ ደመወዛችሁ ይቆረጣል " በማለት በሠራተኞች ላይ ተጽዕኖ የማሳደርና ከሥራ እንደሚያሰናብቱ በመግለጽ የማስፈራራት ድርጊቶች እየተፈጸሙ እንደሆነም ቦርዱ አስታውቋል። ማንኛውም አካል በየቤቱ በመሄድ "ተመዝገቡ" ማለት ወይም በየመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞችን…