NEBE

በኢትዮጵያ አራት ክልሎች ምርጫ መካሄድ ጀመረ

በኢትዮጵያ አራት ክልሎች ምርጫ መካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ቀሪ ምርጫ በሚደረግባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም ድጋሚ ምርጫ በሚደረግባቸው በጅግጅጋ 2 እና መስቃንና ማረቆ ምርጫ ክልሎች በዛሬው ዕለት ምርጫ እየተካሄደ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ በ6ኛው ዙር ሀገራዊ ቀሪና ድጋሚ ምርጫ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ድምፅ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል። ዛሬ እየተካሄደ ባለው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ላይም 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ መሆኑን ከምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ቀሪና ድጋሚ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች እየተካሄደ መሆኑንም ነው ቦርዱ ያስታወቀው። ቀሪና ድጋሚ ምርጫ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች አንዱ በአፋር ክልል የሲሆን፤ በክልሉ 4 ዞኖች፣ በ9 የምርጫ ክልሎች እና በ388 የምርጫ…
Read More
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች መመዝገቢያ ጊዜን አራዘመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች መመዝገቢያ ጊዜን አራዘመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ቀሪ ምርጫ በሚደረግባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም ድጋሚ ምርጫ በሚደረግባቸው በጅግጅጋ 2 እና መስቃንና ማረቆ ምርጫ ክልሎች ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም.  ምርጫ ለማከናወን የተለያዩ ዝግጅቶችን  በማድረግ ላይ ይገኛል። ቦርዱ ከሚያዝያ 21 እስከ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት የመራጮች ምዝገባ እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል። ነገር ግን የመራጮች ምዝገባ በወጣበት የጊዜ ሰሌዳ ወቅት ተደራራቢ የህዝብና የሃይማኖት በዓላት የነበሩ በመሆኑ፣ የመራጮች ምዝገባ የሚደረግባቸው አንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች በወቅቱ ባለመከፈታቸውና በምርጫ የሚወዳደሩት የፓለቲካ ፓርቲዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ የመራጮች ምዝገባ ቀን እንዲራዘም በመጠየቃቸው ቦርዱ የመራጮችን የምዝገባ ቀን እስክ ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ማራዘሙን…
Read More
ኢትዮጵያ ለምርጫ ስርዓት ማጠናከሪያ የ30 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች

ኢትዮጵያ ለምርጫ ስርዓት ማጠናከሪያ የ30 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች

ኢትዮጵያ ዘላቂ ዲሞክራሲን ለማስፈን የሚያስችላትን የምርጫ ስርአት እንድታጠናክር ለማግዝ የሚውል የ30 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የፋናንስ ድጋፍ ስምምነት ፈርማለች፡፡ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት መካካል ተፈርሟል፡፡ የበጀት ድጋፉ የምርጫ ቦርድ ተቋማዊ መዋቅርን ለማጠናከር ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ አሳታፊ ፣ተአማኒና ደረጃውን የጠበቀ ምርጫና ህዝበ ውሳኔ እንዲያካሂድ ተቋሙን ማጠናከር፣ ከሲቪክ ተቋማት በጋራ በመሆን በምርጫ ሂደት የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎን ለማሳደግ ይውላል ተብሏል፡፡ እንዲሁም የበጀት ድጋፉ በኢትዮጵያ ነፃ ፍትሀዊ እና ተአማኒ ምርጫ እንዲያከሂድ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንደሚውልም የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህ የበጀት ድጋፍ ፕሮጀክት በሚቀጥሉት አራት አመታት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን የሀገሪቱን የምርጫ ስርአት በማጠናከር ዘላቂ ዴሞክራሲን ለማስፈን አስተዋጽኦ…
Read More
ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከሀላፊነት ለቀቁ

ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከሀላፊነት ለቀቁ

ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከሀላፊነት ለቀቁ ከ2011 ዓ.ም ታህሳስ ወር ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሆነው ስራ የጀመሩት ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በጠየና ምክንያት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ሰማያዊ ማረጋገጫ ባለው የፌስቡክ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል፡፡ “ባለፉት  አራት አመት ከስድስት ወራት ሶስት ህዝበ ውሳኔዎችን እና አገራዊ ምርጫን በማካሄድ እና ፓለቲካ ፓርቲዎችን በማስተዳደር የተሰጡኝን ሃላፊነቶች ህጋዊነት ፍትሀዊነት እና ቅንነትን በተከተለ ሁኔታ ለማከናወን ስጥር ቆይቻለሁ” ብለዋል። “ሆኖም ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ ሆኖ በመገኘቱ ከ ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቦርድ ሰብሳቢነቴ በገዛ ፍቃዴ  መልቀቄን ለተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሳውቄያለሁ” ሲሉም…
Read More
ህወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሕልውናዬን የሚያከስም በመሆኑ አልቀበለውም አለ

ህወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሕልውናዬን የሚያከስም በመሆኑ አልቀበለውም አለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰሞኑ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጉዳይ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡ ቦርዱ ከዚህ በፊት ህወሓት ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጪ ምርጫ በማድረጉ፣ ወደ ትጥቅ ትግል እና አመጽ ተግባር ገብቷል በሚል ፓርቲው እንዲከስም ውሳኔ አስተላልፎ ነበር፡፡ ህወሓት ለምርጫ ቦርድ ባስገባው ማመልከቻ ጦርነቱ በሰላም ስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ እና ከሽብርተኝነት መሰረዙን ተከትሎ  በምርጫ ቦርድ የተላለፈብኝ ውሳኔ ይነሳልኝ ሲል አመልክቶ ነበር፡፡ ምርጫ ቦርድም ከዚህ በፊት በህወሓት ላይ ያስተላለፍኩት ውሳኔን መቀልበስ የምችልበት ህጋዊ አሰራር የለም ሲል ምላሽ ሰጥቶም ነበር፡፡ ይህንን ተከትሎም ህወሓት ከቀናት በፊት ምርጫ ቦርድ ያሳለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበለው ባወጣው መግለጫ አሳውቋል። የምርጫ ቦርድን ውሳኔ " አልቀበለውም " ያለው ህወሓት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር…
Read More