ethiopiapolitics

በኢትዮጵያ የፓለቲካ ምህዳሩ ወደ አስቸጋሪ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑ ተገለፀ

በኢትዮጵያ የፓለቲካ ምህዳሩ ወደ አስቸጋሪ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑ ተገለፀ

በኢትዮጵያ የስነ መንግስት ታሪክ ውስጥ ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት የፓለቲካ ምዕራፍ እጅግ  አስቸጋሪ ደረጃ ላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርታ (ኢዜማ) ዋና ፀሐፊ አበበ አካሉ ገልፀዋል። አቶ አበበ አካሉ ይሄን በእናት ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዳሉት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ እየገባ ነው። በኢትዮጵያ እየተሸጋገረ የመጣውን አደገኛ የፓለቲካ ምዕራፍ በተበታተነ ትግል ውስጥ መቀልበስ እንደማይቻልም አቶ አንስተዋል። አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ ቅንጦት ነው የሚሉት አቶ አበበ ሰውነት እጅግ የረከሰበት ዘመን ላይ መድረሳቸውን አስታውሰዋል። አክለውም የአገር እሴት ሲናድ አብሮ የሚናድ አገረ መንግስት ምስረታ በመኖሩ የሀገርን ቋሚ እሴት'ና ምዕተ አመት ዘለል ተቋማት መከበር አለባቸው ብለዋል። ምንም እንኳን እንደ ፓርቲ ህገመንግስቱ እንዲቀየር…
Read More
ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዳያካሂዱ መከልከላቸውን ምርጫ ቦርድ አወገዘ

ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዳያካሂዱ መከልከላቸውን ምርጫ ቦርድ አወገዘ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዳያካሂዱ መከልከሉን አወገዘ። ቦርዱ ባለፈው ሳምንት ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዳያካሂዱ የተከለከሉትን ፓርቲዎች አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ቦርዱ በመግለጫው ፓርቲዎች ጉባዔ እንዳያካሄዱ የከለከሉት እነማን እንደሆኑ እንዳላወቃቸው ገልጾ ነገር ግን እገዳውን የጣሉት አካላት የህግ አስፈፃሚ ሃላፊዎች ትእዛዝ እንደሆኑ አስታውቋል። እናት ፓርቲ፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲና አዲስ የተመሰረተው ለጉራጌ አንድነትና ፍትህ (ጎጎት) ፓርቲዎች ባሳለፍነው ሳምንት የፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ እንዳያደርጉ በጸጥታ አካላት መከልከላቸውን የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ተናግረዋል። በመግለጫውም በፓርቲዎቹ ላይ የደረሰው ወከባ ከህግ አንፃር ትክክል አለመሆኑን ገልፀው ፤በቀጣይም ይህን ችግር የፈጠሩ አካላትን አጣርቶ ማቅረብ የፍትህ አካላት ስራ እንደሆነ ገልቷል። አዲስ የተመሰረተው የጎጎት ፓርቲ አመራሮችም መታሰራቸውን የተናገሩት የምርጫ…
Read More