Politicalparties

ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዳያካሂዱ መከልከላቸውን ምርጫ ቦርድ አወገዘ

ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዳያካሂዱ መከልከላቸውን ምርጫ ቦርድ አወገዘ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዳያካሂዱ መከልከሉን አወገዘ። ቦርዱ ባለፈው ሳምንት ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዳያካሂዱ የተከለከሉትን ፓርቲዎች አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ቦርዱ በመግለጫው ፓርቲዎች ጉባዔ እንዳያካሄዱ የከለከሉት እነማን እንደሆኑ እንዳላወቃቸው ገልጾ ነገር ግን እገዳውን የጣሉት አካላት የህግ አስፈፃሚ ሃላፊዎች ትእዛዝ እንደሆኑ አስታውቋል። እናት ፓርቲ፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲና አዲስ የተመሰረተው ለጉራጌ አንድነትና ፍትህ (ጎጎት) ፓርቲዎች ባሳለፍነው ሳምንት የፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ እንዳያደርጉ በጸጥታ አካላት መከልከላቸውን የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ተናግረዋል። በመግለጫውም በፓርቲዎቹ ላይ የደረሰው ወከባ ከህግ አንፃር ትክክል አለመሆኑን ገልፀው ፤በቀጣይም ይህን ችግር የፈጠሩ አካላትን አጣርቶ ማቅረብ የፍትህ አካላት ስራ እንደሆነ ገልቷል። አዲስ የተመሰረተው የጎጎት ፓርቲ አመራሮችም መታሰራቸውን የተናገሩት የምርጫ…
Read More